Friday, June 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊእጅን የመታጠብ ትሩፋቶች

እጅን የመታጠብ ትሩፋቶች

ቀን:

በተመስገን ተጋፋው

እጅን በሳሙናና በውኃ መታጠብ የተቅማጥ፣ የመተንፈሻ አካል እንዲሁም ከእጅ ንክኪ ጋር ተያይዘው ሊተላለፉ የሚችሉ በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስችል ዋነኛ መንገድ ነው፡፡ እጅ በመታጠብ ብቻ በማደግ ላይ ባሉ አገሮች በየዓመቱ ሊከሰት የሚችለውን በሚሊዮን የሚቆጠር ሞት መከላከል ይቻላል፡፡

እናቶች እጃቸውን በሳሙናና በውኃ በአግባቡ የሚታጠቡ ከሆነ፣ የጨቅላ ሕፃናትን ሞት 44 በመቶ፣ በትምህርት ቤት የእጅ መታጠቢያ ውኃና ሳሙና አሟልቶ መጠቀም ከተቻለም በተቅማጥ በሽታ ምክንያት ከትምህርት የሚቀሩ ተማሪዎችን ቁጥር 30 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በ2007 ዓ.ም. የእጅ መታጠብን ቀን አስመልክቶ ባዘጋጀው ጽሑፍ አስፍሯል፡፡

ምግብ ከመመገብ በፊትና ከተፀዳዱ በኋላ እጅን በሳሙና የመታጠብ ልማድ ከዳበረ የተቅማጥ በሽታን 50 በመቶ እንዲሁም የመተንፈሻ አካል ሕመምን 23 በመቶ መከላከል ይቻላል፡፡

የማንኛውም ሰው እጆች በየሰኮንዶች ልዩነት ለበሽታ መንስዔ ሊሆኑ ከሚችሉ ረቂቅ ሕዋሳት ጋር ለመነካካት የሚኖራቸው ዕድል እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ፣ ሰዎች ሲፀዳዱ፣ የመጸዳጃ ቤታቸውን በር ሲከፍቱም ሆነ ሲዘጉ፣ ሲያነጥሱና አፍንጫቸውን ሲጠራርጉ፣ ዓይናቸውን ሲነካኩና ከሌሎች ሰዎች ጋር ሲጨባበጡ፣ ሲያስታምሙ እንዲሁም ሕፃናት በየሜዳው ሲጫወቱ በሚኖራቸው ንክኪ ሁሉ በእጆች ላይ የሚቀሩ የበሽታ መንስዔ ረቂቅ ሕዋሳት ቁጥር ሊገመተው ከሚችለው በላይ ነው።

በዓለም በወረርሽኝ መልክ የተከሰተው ኖቭል ኮሮና ቫይረስ የመከላከያ የመጀመሪያ መንገዱ እጅን በውኃና በሳሙና መታጠብ ነው እጅን በተደጋጋሚ በሳሙና መታጠብ እንደ ኮሮና ቫይረስ ዓይነት ተላላፊ በሽታዎችን ሥርጭት ለመግታት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው የእንግሊዝ ተመራማሪዎችገልጻሉ።

በዓለም ከተከሰተ ስምንት ወራት ያስቆጠረውና ከ16.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ያጠቃውና ከ650 ሺሕ በላይ ሰዎችን የገደለው ኮሮና ቫይረስ፣ ክትባትም ሆነ መድኃኒት ባይገኝለትም በቀላሉ በውኃና በሳሙና በመታጠብ፣ አፍና አፍንጫን በመሸፈንና የግልና አካባቢ ንፅህናን በመጠበቅ መከላከል ይቻላል።

ሆኖም እጅን በሳሙና መታጠብ፣ ማክስ ማድረግ፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ኖቭል ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ትልቁን ድርሻ ቢይዙም፣ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ይህ ተዘንግቷል፡፡

በተለይ ከአዲስ አበባ ወጣ ሲሉ ያለው ልማድ የተለየ ነው፡፡ በርካቶች አፍና አፍንጫቸውን ሸፍነው አይታዩም፡፡ ቫይረሱ ኢትዮጵያ ገባ እንደተባለ በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ይሰጡ የነበሩ የእጅ ማስታጠብና የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ አይደሉም፡፡

በየቦታው ውኃ ተሞልተው አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩ የውኃ ማጠራቀሚያ ታንከሮች አገልግሎት የማይሰጡ፣ የተሰበሩና ውኃ የሌላቸው ከመሆኑ ባለፈም እንደሚሰረቁም ይሰማል፡፡

አንዳንድ አካባቢዎች ላይም ለእጅ መታጠቢያ ውኃ የያዙ ታንከሮች ቢኖሩም፣ ሳሙና በቦታው አለመኖሩን መታዘብ ይቻላል፡፡ በተለያዩ ሥፍራዎች ተተክለው አገልግሎት እየሰጡ የነበሩ የውኃ ታንከሮች አሁን ላይ ተቀዛቅዘዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል በሳሪስ አቦ፣ በሃና ማርያም፣ በመገናኛ፣ በፒያሳ፣ በቦሌ፣ በቦሌ ሚካኤል የሚገኙ የእጅ መታጠቢያ ታንከሮች ለአገልግሎት ዝግጁ ቢሆኑም መንገደኛውም ለአፍታ ቆም ብሎ ሲታጠብ አይስተዋልም፡፡

ቀድሞ ታክሲ ሲሳፈሩ፣ ገንዘብ ሲከፍሉ እጃቸውን በሳኒታይዘር ይጠራርጉ የነበሩትን ማየት ይቻል ነበር፡፡ ሆኖም ይህ እየተዘነጋ ነው፡፡ በሽታውን ለመከላከል መድኃኒቱ እጅን በውኃና በሳሙና መታጠብና አፍና አፍንጫን መሸፈኑ ላይ ቢሆንም ችላ ተብሏል፡፡ መንግሥትም በተደጋጋሚ የኅብረተሰቡን መዘናጋት በመግለጽ ወረርሽኙ ይስፋፋል ሲል ሥጋቱን አሳውቋል፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ምክትል ሥራ አስፈጻሚና የቤቶች አስተዳደር ጸሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አባተ አበበ፣ የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ከገባ ጊዜ ጀምሮ ኮሚቴዎችን በማዋቀር ማኅበረሰቡ ግንዛቤ እንዲያገኝ መደረጉን፣ በወረዳው የሚኖሩ አብዛኛው ነዋሪዎች በዝቅተኛ የአኗኗር ሁኔታ ላይ የሚገኙ በመሆናቸው ሀብት በማሰባሰብ ቫይረሱን ለመከላከል የሚያግዙ ሳይኒታይዘሮችን፣ ፈሳሽ ሳሙናና ማስክ ድጋፍ እንደተደረገላቸው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

መቶ ሃምሳ ሁለት የሚሆኑ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማሰማራት ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች ላይ በመሄድ ራሳቸውን ከወረርሽኙ እንዲከላከሉና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መሠራቱን፣ ይኼም ትልቅ ውጤት ማምጣቱን አቶ አባተ አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ከዚህ ቀደም ይሰጡ የነበሩ የእጅ ማስታጠብ ሥራዎች አለመኖራቸው፣ በየቦታው የተቀመጡ የእጅ መታጠቢያ ውኃ የያዙ ታንከሮች ምንም ዓይነት አገልግሎት አለመስጠታቸው ትልቅ ችግር እንደፈጠረባቸው ኃላፊው ጠቁመው፣ ለዚህም በወረዳው ላይ አልፎ አልፎ የውኃ እጥረት መከሰቱን እንደ ምክንያት አንስተዋል፡፡

በማኅበረሰቡ ላይ መዘናጋት መታየቱ ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሠራጭ መንገድ  ከፍቷል ብለዋል፡፡ በባንኮች፣ በሆቴሎችና በድርጅቶች ላይ የእጅ መታጠቢያ ታንከሮች በተገቢው መንገድ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን፣ ይህም ተጠናክሮ እንዲቀጥልና በየአካባቢው የተቀመጡ የእጅ መታጠቢያ ታንከሮች አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነቱን በመወጣት ይኼን ችግር ማለፍ ይገባል ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...