Monday, June 17, 2024

ለክቡር ሚኒስትሩ የቀድሞ ሚኒስትር ስልክ ደወሉላቸው

[ክቡር ሚኒስትሩ ለምሳ ቤታቸው ሲመጡ ሚስታቸውን አገኟቸው]

 • ምነው ቢቀርብህ?
 • ምኑ?
 • ሥራው ነዋ፡፡
 • ምን ሆነሻል?
 • ለመሆኑ ትሰማለህ አይደል?
 • ምኑን?
 • የኮሮናን ዜና ነዋ፡፡
 • ምን ጥያቄ አለው?
 • አስፈሪ ሆኗል እኮ፡፡ 
 • ምን ታደርጊዋለሽ?
 • ለምን ዕረፍት አትወጣም?
 • ማን?
 • አንተ ነሃ፡፡
 • እየቀለድሽ መሆን አለብሽ?
 • የምን ቀልድ ነው እውነቴን ነው፡፡
 • ሥራዬስ?
 • ከጤንነትህ አይበልጥም፡፡
 • እሱማ ልክ ነሽ፡፡
 • መንግሥት አይደለም እንዴ ቤት ተቀመጡ እያለ ያለው?
 • አዎን፡፡
 • ታዲያ አንተ የመንግሥትን ሕግ ሳታከብር ሌላው እንዴት ያከብራል?
 • ሥራው እኮ አሳስቦኝ ነው፡፡
 • ሰውዬ አንተም ቤተሰብ እንዳለህ አትርሳ፡፡
 • ምን እያልሽ ነው?
 • ቢያንስ ለራስህ ባታስብ ለእኛ አስብልን፡፡
 • እንዴት?
 • ይኸው እኛ ከቤት መውጣት ካቆምን ወር ሆኖናል እኮ፡፡
 • አውቃለሁ፡፡
 • ስለዚህ በአንተ ጦስ እኛን እንዳታስጨርሰን፡፡
 • እኔ እኮ ከብዙ ሰዎች ጋር አልገናኝም፡፡
 • ለዚህ እኮ ነው ከቤትህ ሆነህ ሥራ የምለው፡፡
 • ምነው ይኼን ያህል ፈራሽ?
 • ሰውዬ በሕይወት ቀልድ የለም፡፡
 • ማለቴ አሁን ምን አዲስ ነገር መጣ ብዬ ነው?
 • ምን ነካህ ቁጥሩ እየጨመረ እኮ ነው፡፡
 • እ…
 • እኔ በሽታው ይይዘኛል የሚለው ሐሳብ በየቀኑ እያስጨነቀኝ ነው፡፡
 • ተረጋጊ እንጂ፡፡
 • እንዴት ነው የምረጋጋው?
 • ማለቴ መጠንቀቅ እኮ ነው መፍትሔው ብዬ ነዋ፡፡
 • አንተም ካልተጠነቀቅክ የእኔ ብቻ መጠንቀቅ ምን ይጠቅማል ብለህ ነው?
 • እኔም እኮ እጠነቀቃለሁ፡፡
 • የት አለ ጥንቃቄህ?
 • ከዚህ በላይ ምን ላድርግ?
 • ቤት ሆነህ ሥራ አልኩህ፡፡
 • አልችልማ፡፡
 • ዕረፍት ውጣ በቃ?
 • እሱንም ማድረግ አልችልም፡፡
 • ለምን?
 • የእኔ ሥራ ዕረፍት የሚሰጥ አይደለማ፡፡
 • እንግዲያው አንድ ነገር አድርግ፡፡
 • ምን?
 • ሥራህን ልቀቅ!

[ለክቡር ሚኒስትሩ ደላላ ወዳጃቸው ስልክ ደወለላቸው]

 • እየጨመረ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምኑ?
 • ቁጥሩ ነዋ፡፡
 • ኧረ እስቲ ተወኝ፡፡
 • ምነው?
 • እኔ ራሱ እየጨመረብኝ ነው፡፡
 • ምኑ ነው የጨመረብዎት?
 • ፍርኃቱ ነዋ፡፡
 • መጠንቀቁ ነው የሚያዋጣው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ተጠንቅቀህ ትችለዋለህ ብለህ ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር ዛሬ ላማክርዎት ያሰብኩት ጉዳይ ምናልባት ይጠቅመዎታል፡፡
 • ምንድነው?
 • ማለቴ ሁልጊዜ ስለኮሮና ከማሰብ ሌላ ነገር ላይ ማተኮር ጥሩ ነው፡፡
 • ሌላ ምን ነገር ላይ?
 • ለምሳሌ መሬት፡፡
 • እንዴት?
 • ክቡር ሚኒስትር ሁሉም ሰው ተዘናግቷል፡፡
 • በሽታው ላይ ነው የተዘናጋው?
 • ኧረ መሬቱ ላይ ነው እንጂ፡፡
 • እ…
 • ክቡር ሚኒስትር አሁን ሆ ብለን መነሳት አለብን፡፡
 • ኮሮና ላይ?
 • ምን ነካዎት ክቡር ሚኒስትር መሬቱ ላይ ነው እንጂ፡፡
 • ለምን?
 • የሰው ሁሉ ሐሳብ ኮሮና ነዋ፡፡
 • እ…
 • ስለዚህ ይኼን አጋጣሚ ተጠቅመን መቸብቸብ ነው፡፡
 • ወይ ጣጣ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር በርካታ ገዥዎች እጄ ላይ ይዣለሁ፡፡
 • በዚህ ጊዜ?
 • እኔ እኮ መቼም አልተኛም፡፡
 • ለነገሩ ልተኛ ብትልስ እንቅልፍ ከየት ይመጣልሃል?
 • ክቡር ሚኒስትር ይኼ እኮ በሽታ ጊዜያዊ ነው፡፡
 • በምን አወቅክ?
 • መቼም ለዘለዓለም አይቆይም ብዬ ነው፡፡
 • እሱን ማን ነገረህ?
 • ለማንኛውም ተዘጋጅቶ መጠበቁ አይከፋም፡፡
 • እንዴት?
 • ማለቴ በሽታው ሲያልፍ እኛም አብረን ከብረን መነሳት አለብና፡፡
 • አልገባኝም?
 • ያው ኢኮኖሚው ስለተቀዛቀዘ አሁን የተገኘውን አጋጣሚ እንጠቀም እያልኩዎት ነዋ፡፡
 • እንዴት ነው የምንጠቀመው?
 • የበሽታውን ስትራቴጂ ዓይነት በመጠቀም ነዋ፡፡
 • ማለት?
 • እንውረር፡፡
 • ምን?
 • መሬት!

[ለክቡር ሚኒስትሩ አንድ ተቃዋሚ ስልክ ደወለላቸው]

 • ምን ይሻልሃል?
 • ምን አደረግኩ ክቡር ሚኒስትር?
 • ለመሆኑ ታይተኸዋል?
 • ምኑን?
 • ወገብህን ነዋ፡፡
 • ምንድነው የሚያወሩት ክቡር ሚኒስትር?
 • ማለቴ አልተቀጨም ወይ?
 • አልገባኝም?
 • ከአንዱ ቡድን ወደ ሌላው ስትገለባበጥ ማለቴ ነው፡፡
 • ቀልደኛ ነዎት ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ኧረ እኔ እውነቴን ነው፡፡
 • ምን ላድርግ ታዲያ ክቡር ሚኒስትር?
 • እኔማ ለራስህም ጥሩ አይደለም ብዬ ነው፡፡
 • በሥልጣን ግን ቀልድ የለም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • አልገባኝም?
 • በሥልጣን ክፍፍል ተጣልተን እኮ ነው፡፡
 • ገና ሥልጣን ሳትይዙ?
 • እህሳ፡፡
 • ለነገሩ ዶሮ ብታልም ጥሬዋን አሉ፡፡
 • ማን ነው ዶሮ ክቡር ሚኒስትር?
 • ወዲህ ነው ነገሩ፡፡
 • እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጉ ነበር?
 • እኔ እኮ ቅድሚያ የምሰጠው ለሕዝብ ነው፡፡
 • ምን አሉኝ?
 • ሰምተሃል ያልኩትን፡፡
 • እኔማ ደፍረው ከደገሙዋት ብዬ ነበር፡፡
 • ለምን አልደግመውም?
 • ለሕዝብ አስበው ስለማያውቁ ነዋ፡፡
 • እና ለማን ነው የማስበው?
 • ለራስዎ፡፡
 • እ…
 • ተሳሳትኩ እንዴ?
 • ተደፋፍረናል ልበል?
 • ይቅርታ ያድርጉልኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ለመሆኑ ምን ፈልገህ ደወልክ?
 • ላማክርዎት ነዋ፡፡
 • ምንድነው የምታማክረኝ?
 • ታስገቡኛላችሁ ወይ?
 • የት ነው የምናስገባህ?
 • እናንተ ጋ ነዋ፡፡
 • የፈጣሪ ያለህ፡፡
 • ምነው?
 • አንተ ግን ንግድ ነው የያዝከው?
 • ምን ጥያቄ አለው?
 • ፖለቲካ እኮ ንግድ አይደለም፡፡
 • ለእኔ ነው ክቡር ማኒስትር፡፡
 • እ…
 • እናንተም ጋ መግባት የፈለግኩት ለዚያ ነው፡፡
 • ለምን?
 • አዋጭ ስለመሰለኝ!

[ለክቡር ሚኒስትሩ የቀድሞ ሚኒስትር ስልክ ደወሉላቸው]

 • ምን ሆነው ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ምን ሆንኩ?
 • ስልክ አያነሱም፡፡
 • አውቄ ነው፡፡
 • ለምን?
 • ሙሉ መልዕክቱን እንድትሰማው ነዋ፡፡
 • የምኑን?
 • ጥሪው ላይ ያደረግነውን ነዋ፡፡
 • ለማንኛውም ስልኬን አሰብረውኝ ነበር፡፡
 • ምን አድርጌ?
 • በመልዕክቱ ተናድጄ ነዋ፡፡
 • በመልዕክቱ ነው ወይስ ድምፁን ስለሰማኸው?
 • ትገርሙኛላችሁ እኮ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እንዴት?
 • በዚህ ጊዜ ሕዝቡን ልታስጨርሱት ነው እንዴ ችግኝ እንትከል የምትሉት?
 • አረንጓዴ አሻራ እንድናሳርፍ ነው እንጂ፡፡
 • ድንቄም አረንጓዴ አሻራ አሉ፡፡
 • ለነገሩ እናንተ እንደዚህ ዓይነት አሻራ አይገባችሁም፡፡
 • ምን እያሉ ነው?
 • ማለቴ እናንተ የምትታወቁት ሕዝብን በማሰቃየትና በመጨቆን ስለሆነ አሻራችሁ አረንጓዴ አይደለማ፡፡
 • ምን ዓይነት ነው አሻራችን?
 • ቀይ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን ቅሬታውንም አልሰማሁም። እንዴት? አልሰማሁማ? የምን ቅሬታ ቀርቦባቸው ነው? ሰሞኑን ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ውድና ቅንጡ አውሮፕላን ተከራይተዋል የሚል ቅሬታ...