Monday, June 17, 2024

ለክቡር ሚኒስትሩ የቀድሞ ሚኒስትር ስልክ ደወሉላቸው

[ለክቡር ሚኒስትሩ አንድ ዳያስፖራ ወዳጃቸው ስልክ ደወለላቸው]

 • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • ዛሬ እንዴት ትዝ አልኩህ?
 • ኧረ ሁሌም ነው የማስብዎት፡፡
 • እንዴት ነህ እባክህ?
 • እስካሁን ሰላም ነኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እናንተ ጋ ወረርሽኙ አደገኛ ነው፡፡
 • ይኸው በጭንቀት ውስጥ ነው ያለነው፡፡
 • እዚህም እኮ ከእናንተ የተለየ አይደለም፡፡
 • ምን ይወዳደርና ክቡር ሚኒስትር?
 • እንዴት?
 • እኛ ጋ እኮ ሁሉ ነገር ተዘጋግቷል፡፡
 • እዚህ እንዳንዘጋጋው ይጨርሰናል ብለን ፈርተን ነው፡፡
 • በሽታው ነው?
 • ኧረ ድህነቱ፡፡
 • አሁንማ እኛም እየደኸየን ነው እኮ፡፡
 • ምን ትቀልዳለህ?
 • ክቡር ሚኒስትር የሥራ አጡ ቁጥር እኮ በየቀኑ ነው የሚጨምረው፡፡
 • ምንም ቢሆን የእናንተ ይሻላል፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር እኔ ያለሁበት ቦታ እኮ ወፍ ዝር አይልም፡፡
 • ለደኅንነታችሁ ተብሎ ነዋ፡፡
 • ሕዝቡ ግን እያለቀ ነው፡፡
 • ባይዘጋጋ ከዚህም የባሰ ይገጥማችሁ ነበራ፡፡
 • እኔማ አንድ ነገር ልጠይቅዎት ነው፡፡
 • ምን?
 • ምንድነው የምሰማው ወሬ?
 • ስለምን?
 • ስለግድቡ ነዋ፡፡
 • ምን ሰማህ ደግሞ?
 • ያው ግብፆች እያስፈራሩ ነዋ፡፡
 • እነሱ እኮ ልማዳቸው ነው፡፡
 • ወደ UN ወሰዱት አይደል?
 • ትክክል ነህ፡፡
 • አንድ የማይገባኝ ነገር አለ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምንድነው?
 • ለምንድነው ሁልጊዜ ተከታይ የምንሆነው?
 • አልገባኝም?
 • ማለቴ ግብፆች እየቀደሙን እኛ መከተል ሆነ እኮ ሥራችን፡፡
 • እንዴት?
 • ከዚህ በፊትም አሜሪካ ታደራድረን ብለው የመረጡት እነሱ ናቸው፡፡
 • እ. . .
 • አሁንም ጉዳዩን ወደ UN  ወስደውታል፡፡
 • ልክ ነህ፡፡
 • ታዲያ ሁሌ እነሱን እየተከተልን መሄድ ተገቢ ነው?
 • ኧረ በፍፁም፡፡
 • ባለፈው ጉዳዩን ወደ አፍሪካ ኅብረት እንወስደዋለን ስንል ነበር፡፡
 • ትክክል ነው፡፡
 • አሁን እሱን ሳናደርግ ይኸው እነሱ ቀድመውን ወደ UN ሄዱ፡፡
 • እ. . .
 • ክቡር ሚኒስትር ግድቡ እኮ ህልውናችን ነው፡፡
 • ምን ጥያቄ አለው?
 • ታዲያ ሁሌ ለምን ተከታይ እንሆናለን?
 • እ. . .
 • እየሰማዋኋቸው ያሉ ቁጥሮችም ብዥታ ፈጥረውብኛል፡፡
 • የምን ብዥታ?
 • በመጀመርያ ግድቡ የሚይዘው ውኃ 74 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ነበር፡፡
 • እውነት ነው፡፡
 • አሁን ግን 49 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ መሆኑን ነው የሰማሁት፡፡
 • ያው ይኼ ቴክኒካል ነገር ስለሆነ በደንብ አላውቀውም፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • አቤት፡፡
 • በዚህ ግድብ. . .
 • እ. . .
 • አንደራደርም!

[ለክቡር ሚኒስትሩ አንድ ተቃዋሚ ስልክ ደወለላቸው]

 • ያዋጣል ክቡር ሚኒስትር?
 • ምኑ?
 • እየሄዳችሁበት ያለው መንገድ ነዋ፡፡
 • አዋጥቶንማ ነው እየተጓዝንበት ያለው፡፡
 • እናንተ የነገሩ ክብደት የገባችሁ አልመሰለኝም፡፡
 • ምን ማለት ነው?
 • ይኼ እኮ የምርጫ ጉዳይ አይደለም፡፡
 • ስለምርጫው የምታወራ መስሎኝ?
 • እሱማ ስለምርጫው ነው የማወራው፡፡
 • ታዲያ ምኑን ነው የምርጫ ጉዳይ አይደለም ያልከኝ?
 • ምርጫው ነዋ፡፡
 • ምን ይደረግ ነው የምትለው?
 • መደረግ አለበት ነዋ፡፡
 • እ. . .
 • በሕዝብ ድምፅ መቀለድ አይቻልም፡፡
 • ምን ማለት ነው?
 • እናንተ ነገሩን ከአንድ ጎን ብቻ ነው እያያችሁት ያለው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ከምን ጎን?
 • ሥልጣናችሁን ከማራዘም ጎን ነዋ፡፡
 • ለነገሩ እናንተም ከአንድ ጎን ብቻ አይደለም እንዴ የምታዩት?
 • ከምን ጎን?
 • ሥልጣን በአቋራጭ ከመያዝ ጎን ነዋ፡፡
 • አይ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምነው?
 • እንደዚህ እየተባባልን የምንዘልቅ አልመሰለኝም፡፡
 • እሱን የምናየው ነገር ነው፡፡
 • ምርጫውን ማድረግ ምነው ፈራችሁ?
 • ምን ያስፈራናል?
 • እሱንማ እናንተ ንገሩን ክቡር ሚኒስትር?
 • ወረርሽኙ ነዋ፡፡
 • አልመሰለኝም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ሌላማ ምን ይሆናል?
 • ልባችሁ አውቆት ነዋ፡፡
 • ምኑን?
 • እንደምናሸንፋችሁ፡፡
 • ዶሮ ብታልም ጥሬዋን አሉ፡፡
 • እንዴት?
 • እናንተ ለነገሩ ወረርሽኙ የማያስጨንቃችሁ ዓላማችሁ ሥልጣን መያዝ እንጂ ስለሕዝቡ ማሰብ ስላልሆነ ነው፡፡
 • ስለሕዝቡ ስለምናስብማ እኮ ነው ምርጫ ይደረግ የምንለው፡፡
 • እንዴት?
 • ሕዝቡ የሰጣችሁ ኮንትራት ያልቃል፡፡
 • መቼ?
 • መስከረም 30፡፡
 • ለጊዜው ይቀጥላል፡፡
 • ይኼ የዕድሜ ማራዘሚያ ኪኒናችሁ ነው፡፡
 • ነገርኩህ እኮ በኪኒንም ቢሆን ተራዝሟል፡፡
 • እኔ የፈራሁት አንድ ነገር ነው፡፡
 • ምን?
 • ኪኒኑ ከመስከረም 30 በኋላ አንድ ነገር የሚያደርግ ይመስለኛል፡፡
 • ምን?
 • ኤክስፓየር!

[ለክቡር ሚኒስትሩ ሌላ ተቃዋሚ ስልክ ደወለላቸው]

 • ክቡር ሚኒስትር አንቀበልም፡፡
 • ምኑን?
 • አካሄዳችሁን ነዋ፡፡
 • አልገባኝም?
 • እንደዚህ የሚያስኬድ ይመስላችኋል?
 • ማለት?
 • እናንተ ሙሉ ለሙሉ በምትቆጣጠሩት ፓርላማ ሌላ ውሳኔ እንደማይተላለፍ እኮ ግልጽ ነው፡፡
 • አልገባኝም?
 • ያው ይኼ ወረርሽኝ አለ ብላችሁ ሥልጣናችሁን እንደምታራዝሙት ይታወቃል፡፡
 • እናንተ ግን ጤነኞች ናችሁ?
 • ምን እያሉ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • አሁን በዚህ ወቅት ስለጤና ነው ወይስ ስለምርጫ ነው ማውራት ያለብን?
 • ስለምርጫ ካላወራን ስለምን እናውራ ታዲያ?
 • ዓለም እኮ በዚህ ወረርሽኝ ተጨንቆ ነው ያለው፡፡
 • እኛ መድኃኒቱን አግኝተነዋል አይደል እንዴ?
 • መድኃኒቱ ምርጫ ነው እንዳትለኝ?
 • ምን ጥያቄ አለው?
 • ለመሆኑ ተመርምረሃል?
 • ኮሮና ነው?
 • ኧረ አማኑኤል፡፡
 • እንከባበራ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እ. . .
 • እየሰደቡኝ እኮ ነው፡፡
 • ምን ብዬ?
 • ዕድብ ነህ ለማለት ፈልገው አይደል እንዴ?
 • እኔማ አረጋግጫለሁ፡፡
 • ማበዴን ነው?
 • ባታብድማ ኖሮ እንደዚህ ዓይነት የዕብደት ሐሳብ አታወራም ነበር፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ኮንትራታችሁ ሊያልቅ ነው፡፡
 • እሱንማ እናውቃለን፡፡
 • ስለዚህ ለመቀጠል ምርጫ ማድረግ አለባችሁ፡፡
 • ካላደረግንስ?
 • እንደዚያማ ከሆነ ሁላችን እኩል እንሆናለን፡፡
 • እሱን እንተያያለን፡፡
 • እያስፈራሩኝ ነው እንዴ?
 • ሞክሩት አልኩህ እኮ፡፡
 • የእኛ ጥያቄ እኮ አንድ ነው፡፡
 • ምንድነው?
 • አካፍሉን ነዋ፡፡
 • ምን?
 • ሥልጣን፡፡
 • አሁን እኛን የሚያስጨንቀን የሕዝባችን ጤና ነው፡፡
 • እኛን ደግሞ ሌላ ነገር ነው የሚያስጨንቀን፡፡
 • ምንድነው የሚያስጨንቃችሁ?
 • ሥልጣን!

[ለክቡር ሚኒስትሩ የቀድሞ ሚኒስትር ስልክ ደወሉላቸው]

 • ዋጋ ትከፍላላችሁ ክቡር ሚኒስትር?
 • የምን ዋጋ?
 • አያውቁም እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
 • ምኑ?
 • ለሕገ መንግሥቱ የከፈልነውን ዋጋ ነው፡፡
 • እ. . .
 • ስለዚህ በሕገ መንግሥቱ አንደራደርም፡፡
 • እና ምን ልታደርጉ?
 • እንደነገርናችሁ እኛ ምርጫውን እናካሂደዋለን፡፡
 • ያኔ እንተያያለን፡፡
 • እያስፈራሩን ነው?
 • ከዚያም በላይ ይኖራል፡፡
 • ምን ክቡር ሚኒስትር?
 • ዕርምጃ እንወስዳለን፡፡
 • ምን ልታደርጉን?
 • እሱን ምርጫ ስታደርጉ ታዩታላችሁ፡፡
 • እኛ በቀላሉ እንደማንበረከክ መቼም ያውቃሉ፡፡
 • እኛም በአገር ጉዳይ ቀልድ አናውቅም፡፡
 • የእኛ ጥያቄ እኮ አንድ ነው፡፡
 • ምንድነው?
 • ሕገ መንግሥቱ ይከበር የሚል ነዋ፡፡
 • አታስቀኝ እስኪ?
 • ምኑ ነው የሚያስቀው ክቡር ሚኒስትር?
 • ሕገ መንግሥቱ ይከበር ስትለኝ ነዋ፡፡
 • ለምን?
 • እናንተ መቼ አክብራችሁ ታውቁና?
 • ነገርኩዎት እኮ፡፡
 • ምኑን?
 • በደምና በአጥንት ዋጋ ከፍለን ነው ሕገ መንግሥቱን ያቆምነው፡፡
 • እውነት?
 • ለመተግበር የሚያስከፍለውን ዋጋም እንከፍላለን፡፡
 • እውነቱን ልንገርህ?
 • ንገሩኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እናንተ እስከ ዛሬ ሕገ መንግሥቱን እየተገበራችሁት ሳይሆን ሌላ ነገር እያደረጋችሁት ነበር፡፡
 • ምን እያደረግን?
 • እየናዳችሁት!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን ቅሬታውንም አልሰማሁም። እንዴት? አልሰማሁማ? የምን ቅሬታ ቀርቦባቸው ነው? ሰሞኑን ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ውድና ቅንጡ አውሮፕላን ተከራይተዋል የሚል ቅሬታ...