Saturday, June 22, 2024

ለክቡር ሚኒስትሩ የቀድሞ ሚኒስትር ስልክ ደወሉላቸው

[ለክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊያቸው ደወለችላቸው]

 • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • ምነው ጠየቅሽኝ?
 • ማለቴ ጠፉ ብዬ ነው፡፡
 • ከቤቴ ነዋ የምሠራው፡፡
 • ቢሆንም አንዳንዴ ለምን ብቅ አይሉም?
 • አንቺ ከእኔ ጋር ችግር አለብሽ እንዴ?
 • የምን ችግር?
 • ታዲያ ምን እያልሽኝ ነው?
 • አንዳንዴ ቢሮ ለምን ብቅ አይሉም ነው እኮ ያልኩት?
 • እኮ ችግርሽ ምንድነው?
 • ምን አጠፋሁ ክቡር ሚኒስትር?
 • ለመሆኑ አንቺን ተቆጣጣሪ ያደረገሽ ማን ነው?
 • ኧረ እንደዚያ ለማለት ፈልጌ አይደለም፡፡
 • ታዲያ ምን እያልሽ ነው?
 • በቃ ይቅርታ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • የጤንነቴን ሁኔታ ታውቂያለሽ አይደል እንዴ?
 • እሱማ ይገባኛል ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ታዲያ ምን ፈልገሽ ነው?
 • እኔ እኮ በፊትም እንዲጠነቀቁ እነግርዎት ነበር፡፡
 • ምን ላድርግ ታዲያ እኔ?
 • ማለት?
 • ስኳርና ደም ግፊትን ፈልጌ አላመጣኋቸው፡፡
 • እሱን እንኳን ተውት ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ማለት?
 • እርስዎ ሲነገርዎት መቼ ይሰማሉ?
 • ምን እያልሽ ነው?
 • ያላግባብ አልነበር እንዴ የሚያግበሰብሱት፡፡
 • ስለምግብ ነው የምታወሪው?
 • ኧረ ሌላ ነገር ነው የምልዎት ያለው፡፡
 • እኮ ምን?
 • ክቡር ሚኒስትር ለእነዚህ በሽታዎች የዳረግዎት እኮ ሙስና ነው፡፡
 • እ…
 • ከመጠን በላይ ስለሚጨነቁ አይደል እንዴ ለዚህ የበቁት፡፡
 • ግድ የለም ስመጣ እንገናኛለን፡፡
 • ይመጣሉ ግን?
 • ማለት እንድቀር ፈለግሽ?
 • ያው ኮሮና እንደ እርስዎ ዓይነት ሰዎችን ያጠቃል ብዬ ነው፡፡
 • ችግር የለም አንቺ ሟርተኛ፡፡
 • ለማንኛውም ሥራ እንዴት ነው የምንሠራው?
 • ይኸው ከቤት ሆኜ እየሠራሁ አይደል እንዴ?
 • ተው እንጂ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምነው?
 • የምልክልዎትን ደብዳቤ እንኳን መቼ ፈርመውልኝ ያውቃሉ?
 • ሞኝሽን ፈልጊ፡፡
 • ምነው?
 • በሽታው በወረቀት ሊተላለፍ እንደሚችል አታውቂም እንዴ?
 • ለዚያ ነው የማይፈርሙት?
 • ስሚ በኮሮና ቀልድ የለም፡፡
 • ስለዚህ እኔም ቢሮውን ዘግቼ ቤቴ ልቀመጣ?
 • ለማንኛውም አሁን ደመወዜን በአስቸኳይ ላኪልኝ፡፡
 • እንዴ በወረቀት ይተላለፋል አላሉኝም እንዴ?
 • ቢተላለፍስ?
 • ማለቴ ገንዘቡ ወረቀት እኮ ነው ብዬ ነዋ፡፡
 • አሁን አንድ ጥናት ሳነብ በእሱ እንደማይተላለፍ አንብቤያለሁ፡፡
 • በምንድነው የማይተላለፈው?
 • በገንዘብ!

[ለክቡር ሚኒስትሩ አማካሪያቸው ስልክ ደወለላቸው]

 • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • እስካሁን አለሁ፡፡
 • ቢሮ መቼ ነው የሚመጡት?
 • መቼም አልመጣም፡፡
 • ለምን ክቡር ሚኒስትር?
 • በሕይወት ቀልድ የለማ፡፡
 • እሱማ ልክ ነዎት፡፡
 • ታዲያ መንግሥት ከቤት አትውጡ እያለ የምን ጨዋታ ነው ቢሮ አትመጣም ወይ የምትለኝ?
 • አይ እንዲያው ነገሩ አስፈርቶኝ ነው፡፡
 • ምኑ ነው ያስፈራህ?
 • እየሄድንበት ያለው መንገድ ነዋ፡፡
 • እንዴት ማለት?
 • በቃ ሁሉም ነገር እኮ ተቀዛቅዟል፡፡
 • ምን ይደረግ?
 • እያስፈራኝ ያለው በተለይ የኢኮኖሚው ጉዳይ ነው፡፡
 • እንዴት?
 • ይኸው ኢንተርኔት ብዙ ነገሮችን እያነበብኩ ነበር፡፡
 • ታዲያ ምን አገኘህ?
 • ያው የዚህን ወረርሽኝ ጉዳይ ሳስበው ብዙ ጥያቄዎች ተፈጥረውብኛል፡፡
 • ምን ዓይነት ጥያቄ?
 • ማለት ይህ ወረርሽኝ እንዴት ነው ዓለምን በአንዴ ቀጥ ሊያደርጋት የቻለው ብዬ ነዋ፡፡
 • አደገኛ ስለሆነ ነዋ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ዓለም ላይ ግን ከኮሮና በላይ አደገኛ በሽታዎች የሉም ብለው ነው?
 • እሱማ በርካታ ገዳይ በሽታዎች አሉ፡፡
 • ታዲያ ለምንድነው ይኼ ወረርሽኝ ዓለምን እንደዚህ ያቆማት?
 • በሽታው ገዳይና በቀላሉ ተላላፊ ስለሆነ ነዋ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር እኔ ግን ከዚያም ያለፈ ነገር ያለ ይመስለኛል፡፡
 • ምን?
 • ማለት የዓለምን ኢኮኖሚ ሥርዓት ለመቀየር የታሰበ ይመስለኛል፡፡
 • አልገባኝም?
 • በዚህ በሽታ ሽፋን የዓለምን ኢኮኖሚ ሊቆጣጠሩ የሚያስቡ አካላት ያሉ ይመስለኛል፡፡
 • እንዴት ማለት?
 • በበሽታው ሳቢያ የዓለም ኢኮኖሚ እንደዚህ ሲሽመደመድ ጥያቄዎችን መጠየቅ ተገቢ መሰለኝ፡፡
 • እሱማ ልክ ነህ፡፡
 • ስለዚህ በወረርሽኙ ምክንያት የዓለምን ኢኮኖሚ በመቆጣጠር እንደፈለጉ ሊዘውሩት የሚፈልጉ አካላት ይነሳሉ እየተባለ ነው፡፡
 • ወይ ፈጣሪ?
 • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
 • በስንቱ ነገር ግራ ተጋብተን እንችለዋለን ብዬ ነዋ?
 • ያው እኔ ያነበብኩትን ነው ያካፈልኩዎት፡፡
 • መጠርጠሩ አይከፋም ስልህ?
 • ግራ የሚገባው ግን ከእንደ እኛ ዓይነቱ አገር ምን እንደሚያገኙ ነው?
 • ማለት?
 • ያው ደሃ አገር ነን ብዬ ነዋ፡፡
 • ያነበብካቸው ጽሑፎች ምን ይላሉ?
 • ከጽሑፎቹማ የተገነዘብኩት ድጋሚ ሊመጣብን እንደሆነ ነው፡፡
 • ምንድነው የሚመጣብን?
 • ቅኝ ግዛት!

[ለክቡር ሚኒስትሩ ደላላ ወዳጃቸው ስልክ ደወለላቸው]

 • እንዴት ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ምኑ?
 • የቤት ቆይታዎት ነዋ፡፡
 • ኧረ ተወኝ ወዳጄ፡፡
 • ምነው?
 • ለካ ቢሮአችን ብዙ ጉድ ነው የሸፈነልን፡፡
 • እንዴት?
 • አሁን በቃ ሁሉ ነገር ያለበት እስር ቤት እንደገባሁ ቁጠረዋ፡፡
 • ኧረ ቶሎ በቃችሁ ባለን፡፡
 • እንዲህ በአጭር ጊዜ የሚፈታ ይመስልሃል?
 • ሁሉ ነገር ፀጥ ረጭ ብሏል፡፡
 • ምን ታደርገዋለህ?
 • እኔማ ጉድጓድ እየፈነቀልኩ ነው፡፡
 • ማለት?
 • ክቡር ሚኒስትር በአንድ በኩል እኮ ጥሩ ነው፡፡
 • ምኑ?
 • ወረርሽኙ ነዋ፡፡
 • አንተ አረመኔ?
 • እውነቴን ነው ስልዎት?
 • ምን እያልክ ነው?
 • በዚህ ወቅት ሕዝቡ የሚፈልጋቸው በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ 
 • እ…
 • ስለዚህ እነሱን ያለተወዳዳሪ በፈለግነው ዋጋ መቸብቸብ እንችላለን፡፡
 • ጤነኛ ነህ ግን አይደል?
 • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
 • መንግሥት አዋጅ ማወጁን ረሳኸው እንዴ?
 • ምን ችግር አለው ታዲያ?
 • እንዴት የለውም?
 • ያው እርስዎ ነዎት መንግሥት ብዬ ነዋ፡፡
 • ሰውዬ በሕግ፡፡
 • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ከእንደዚህ ዓይነት ነገር ጋር እንዳታገናኘኝ፡፡
 • እየተሳሰብና ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ማለት?
 • ስለእኔ ሕይወት አያስቡም እንዴ?
 • አንተ ስለሕዝቡ ሕይወት አታስብም እንዴ?
 • ፈሩ እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
 • ስማ ለመሆኑ ምን ያህል እኖራለሁ ብለህ አስበህ ነው?
 • ምን እያሉኝ ነው?
 • ሕዝብ እንደዚህ ተጨንቆም ማጭበርበር ታስባለህ?
 • እኔ ሥራ መዝጋት አልችልማ?
 • በጣም ቀልደኛ ነህ ልበል?
 • የእውነቴን እኮ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ለምን?
 • የእኛ ሥራ አሁን ነዋ የሚጦዘው፡፡
 • ለማንኛውም ተጠንቀቅ፡፡
 • ክቡር ማኒስትር መቼም መንግሥት እስረኛ እየለቀቀ እኔን አያስረኝም፡፡
 • ስማ በዚህ ከቀጠልክ መጨረሻህ አንድ ቦታ ነው፡፡
 • የት ነው?
 • እስር ቤት!

[ለክቡር ሚኒስትሩ የቀድሞ ሚኒስትር ስልክ ደወሉላቸው]

 • የእኛ ግፍ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምኑ?
 • ይኼ ወረርሽኝ ነዋ፡፡
 • ማለት?
 • ይኸው እየተከፈላችሁ ነዋ፡፡
 • አልገባኝም?
 • እኛ ላይ በሠራችሁት ሸር ነው ይኼ በሽታ የመጣባችሁ፡፡
 • እናንተ ግን ትችሉታላችሁ?
 • ምኑን ክቡር ሚኒስትር?
 • ሁሉን ነገር ፖለቲካ አድርጋችሁ ነዋ፡፡
 • ጥርሳችንን ያወለቅነው እኮ በፖለቲካ ነው፡፡
 • ታዲያ ይኼን በሽታ እንዴት ፖለቲካ ልታደርጉት ትሞክራላችሁ?
 • ፖለቲካ ስለሆነ ነዋ፡፡
 • ምኑ ነው ፖለቲካው?
 • ተነቃቃን እኮ፡፡
 • ምኑን ነው የተነቃቃነው?
 • ምርጫውን አራዘማችሁት አይደል እንዴ?
 • ታዲያ በዚህ ሁኔታ እንዴት ማድረግ እንችላለን?
 • አካሄዳችሁ ሁሉ ገብቶናል፡፡
 • ምኑ ነው የገባችሁ?
 • ማንም ስለማይመርጣችሁ በሥልጣን ላይ ለመቆየት የምታርጉት ሩጫ ነው፡፡
 • የኮሮና ወረርሽኙስ?
 • የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም አካሄድ ገብቶናል፡፡
 • ወረርሽኙ ከባድ ነው እኮ፡፡
 • በእጅ አዙር እኛን ለማንበርከክ እንደሆነም ደርሰንበታል፡፡
 • መቼ ይሆን ይኼ በሽታ የሚለቃችሁ?
 • በሽታው እኮ እኛ ጋ አልደረሰም፡፡
 • ኧረ ይኼ የሴራ በሽታውን ነው የምልህ?
 • ለማንኛውም ተነቃቅተናል፡፡
 • ምኑን?
 • በኮሮና ምን ልታቀምሱን እንደሆነ ነዋ፡፡
 • ምንድነው የምናቀምሳችሁ?
 • ኩርኩማችሁን!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...

ብሔራዊ ባንክ ጥርስ እያወጣ ይሆን እንዴ?

በአመሐ ኃይለ ማርያም ‹‹Better late than never›› (ከቀረ የዘገየ ይሻላል) የኢትዮጵያ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሐዘን ለመድረስ ጎረቤት ተገኝተው ለቀስተኛው በሙሉ የሚያወራው ነገር አልገባ ብሏቸው ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ባለቤታቸውን ስለጉዳዩ እየጠየቁ ነው] 

ጎረቤታችን ሐዘን ለመድረስ ብሄድ ለቀስተኛው በሙሉ በሹክሹክታ ያወራል። ግን የሚያወሩት ነገር ሊገባኝ አልቻለም። ምንድነው የሚያወሩት? እኔ ምን አውቄ? እንዴት? የሚያወሩትን ምንም አልተሰማሽም? እኔ እንድሰማ የፈለጉ አይመስልም ግን ... ግን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...