Tuesday, February 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበቡድን ሆነው በመዝገቦች ላይ ውይይት የሚያደርጉ ዳኞች የኮሮና ቫይረስ ሥጋት ውስጥ መሆናቸውን...

በቡድን ሆነው በመዝገቦች ላይ ውይይት የሚያደርጉ ዳኞች የኮሮና ቫይረስ ሥጋት ውስጥ መሆናቸውን ተናገሩ

ቀን:

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ በጠቅላይና በሰበር ሰሚ ችሎቶች ሦስትና ከዚያ በላይ በቡድን በመሆን በመዝገብ ላይ እያደረጉት ያለው ውይይት፣ የኮሮና ቫይረስ ሥጋት ውስጥ እንደከተታቸው ዳኞች ተናገሩ፡፡

ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ዳኞች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የሥጋታቸው ምንጭ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዓለምን በፍጥነት ያዳረሰው የኮሮና ቫይረስ ነው፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በሰጡት መግለጫ፣ ከመጋቢት 10 እስከ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ሦስቱም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በችሎት ተሰይመው መሥራት እንዲያቆሙ፣ ቀደም ብለው የተሰጡ ቀጠሮዎች እስከ መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደማይካሄዱና ተለዋጭ ቀጠሮ እንደሚሰጥ መነገሩን ዳኞች አስታውሰዋል፡፡

ነገር ግን ፕሬዚዳንቷ የወሰዱት ዕርምጃ የቫይረሱን ሥርጭትን ለመከላከል ስለሆነ የሚመሠገን ቢሆንም፣ አንዳንድ ክፍተቶች እንዳሉበት ዳኞቹ ተናግረዋል፡፡  በከፍተኛ ፍርድ ቤት በአብዛኞቹ ችሎቶች የሚሠሩ ዳኞች ቁጥር ሦስት መሆኑን አስታውሰው፣ በአንድ መዝገብ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ውይይት መደረግ እንዳለበት አስረድተዋል፡፡

በፌዴራል፣ በጠቅላይና በሰበር ችሎቶችም ከሦስት እስከ ሰባት ዳኞች አንድ ላይ ተቀምጠው በመወያየት ውሳኔ ስለሚሰጡ መንግሥት ጭምር መሰብሰብ በከለከለበትና ርቀትን ጠብቆ መንቀሳቀስ ግዴታ መሆኑ በተነገረበት ወቅት፣ እነሱ በጠረጴዛ ዙሪያ ተሰብስበው ውይይት ማድረጋቸው ሥጋት ውስጥ እንደጣላቸው አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም የበላይ ኃላፊዎች ያለውን ሁኔታና ቫይረሱም በፍጥነት እየተሠራጨ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ዳኞች መዝገቦችን ተከፋፍለው በየቤታቸው ውሳኔ ከሠሩ በኋላ ውይይቱን በቪዲዮ ኮንፈረንስ እንዲያደርጉ ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹላቸው ጠይቀዋል፡፡ እስከዚያው ድረስ ግን መዝገብ ወስደው በቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ እንዲወሰንላቸውም አክለዋል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የሰበር ሰሚ ችሎቶች ዳኞች ባነሱት ሥጋት ላይ ማብራሪያ ለማግኘት፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊዎችን ለማነጋገር የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

ምንም እንኳን የሚኒስትሮች ምክር ቤት መጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ፣ የፌዴራል መንግሥት ተቋማት ሠራተኞች ከመጋቢት 16 ቀን 2012 ዓ.ም. በቤታቸው ሆነው ሥራቸውን እንዲሠሩ ውሳኔ ቢያሳልፍም፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥር ስለሆነ እንደማይመለከተው ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...