Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና‹‹የህዳሴ ግድብ ዓድዋችን ነው›› ሒሩት ወልደ ማርያም (ፕሮፌሰር)፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር

‹‹የህዳሴ ግድብ ዓድዋችን ነው›› ሒሩት ወልደ ማርያም (ፕሮፌሰር)፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር

ቀን:

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ሒሩት ወልደ ማርያም (ፕሮፌሰር)፣ ‹‹የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዓድዋችን፤›› ነው ሲሉ አገራዊ ፋይዳው ጉልህ እንደሆነ አስረዱ፡፡

ሚኒስቴሩ ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አየር መንገድ ስካይላይት ሆቴል በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገነባውን የህዳሴ ግድብ በተመለከተ ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ሒሩት (ፕሮፌሰር)፣ ‹‹የዚህ ግድብ ባለቤት እያንዳንዳችን በመሆናችን የህዳሴ ግድብ ጉዳይ የእያንዳንዳችን የግል ጉዳይ ነው፣ ሁላችንም ያገባናል፡፡ ግድቡ የእኔ ነው፣ ግድቡ የእኛ ነው የሚል ጠንካራ የባለቤትነት ስሜት እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ በመሆኑም ዛሬም እንደ ትናንቱ ሕዝባችን ለፕሮጀክቱ ስኬት አስፈላጊ የሆነውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል በቁጭት ፍላጎቱን እየገለጸ ይገኛል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ ህዳሴ ለእኛ የነብር ጭራ ነውና ይዘነዋል፣ ከሰማይ በታች ባለ ምንም ኃይል አንለቀውም፡፡ ምክንያቱም ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ከድህነት መውጫና የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ብቻ ሳይሆን፣ የትውልዳችን ትልቅ ታሪክ፣ የትውልዳችን ትልቅ አሻራና ሌላው ዓድዋችን ጭምር ነው፤›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡  

በውይይት መድረኩ፣ ‹‹ኢትዮጵያ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ አካሄድ ተጠቅማ መብትና ጥቅሟን ይነካል፤›› ብለው እንደሚያምኑ የገለጹት ደግሞ ሚኒስትር ዴኤታው ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ሲሆኑ፣ ‹‹ግድቦቻችን ኃይል ይሰጡናል፡፡ ኃይል በማግኘት ብዙ እናተርፋለን፡፡ ይህ ግን ለእኛ ቅንጦት አይደለም፡፡ ምክንያቱም እንደ ዓለም ባንክ እ.ኤ.አ. 2017 ግኝት መሠረት ኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል የማግኘት ዕድል ያገኘ ዜጋ ብዛት 44.3 በመቶ ሲሆን፣ ጎረቤቶቻችንና ታሪክ ያዛመደን አገሮች የሱዳን 56.5 በመቶ፣ የግብፅ ደግሞ መቶ በመቶ ነው፡፡ ስለዚህ ግድባችን ለድህነት መታገያ መሣሪያ ነው፡፡ ደን ጭፍጨፋን ለማስቆም ፍቱን መሣሪያ ነው፤›› ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

እንደ ህዳሴ ግድብ ያሉ ፕሮጀክቶች ሲከናወኑ ከኃይል ማመንጨት የዘለለ መልዕክት ያስተላልፋሉ ያሉት ሳሙኤል (ዶ/ር)፣ ‹‹ከሁሉም በላይ ግን በየትኛውም ልዩነቶቻችንና ብዝኃነቶቻችን ሳንገደብ አንድ ቋንቋ የምንናገርበትና የተናገርንበት ነው፡፡ ምክንያቱም ግድቡ የእኛ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ግብፅ የዓባይን ውኃ ለመቆጣጠር የዘመናት ፍላጎቷ ነው ያሉት ደግሞ በመድረኩ ጽሑፍ ያቀረቡት ባህሩ ዘውዴ (ፕሮፌሰር) ሲሆኑ፣ ይህንንም ለማሳካት በቅኝ ገዥዎችና በተለያዩ መንገዶች ጥራለች ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የዓባይን ወንዝና የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ የምትቀበለው ሕግ እ.ኤ.አ. በ2015 የተፈረመውን የመርህ ስምምነት ብቻ ነው ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኢብራሒም እድሪስ (አምባሳደር) ሲሆኑ፣ ይኼ ስምምነት ለግብፅ ከኢፍትሐዊ ተጠቃሚነት ውጪ የተለየ መብት ስለማይሰጣት ሌላ ስምምነት ትሻለች ብለዋል፡፡

ግብፅ በተለይ አሁን በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የፈለገችው በአገር ውስጥ የፖለቲካ ውጥረት አለ በሚል እምነት እንደሆነ ያስረዱት ኢብራሒም (አምባሳደር)፣ ‹‹የውስጥ ችግሮቻችንን በውይይት ፈትተን ብሔራዊ ጥቅማችን ላይ እናተኩር፤›› ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...