ማክሰኞ የካቲት 24 ቀን 2012 ዓ.ም. አምባሳደር ሆነው በተሾሙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ባጫ ጊና ምትክ፣ አቶ አቤ ሳኖ መሾማቸው ተገለጸ፡፡
አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት በመሆን መሾማቸው የተገለጸው አቶ አቤ፣ እስካሁን የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንት በመሆን እያገለገሉ የቆዩ ናቸው፡፡
አቶ አቤ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክን ከመቀላቀላቸው ቀደም ብሎም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት እንደነበሩ ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበርም ፕሬዚዳንት በመሆን እያገለገሉ ያሉት አቶ አቤ፣ በዚህ ሳምንት ወደ ቀድሞው ቢሯቸው ገብተው ሥራ ይጀምራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡