Sunday, June 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

​​​​​​​ብሔራዊ ባንክ የአንበሳ ባንክ ቦርድ አመራሮችን ሹመት አፀደቀ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

አንበሳ ባንክን በቦርድ አመራርነት እንዲያገለግሉ በቅርቡ በከፍተኛ ድምፅ የተመረጡት የቀድሞው የመከላከያ ኤታ ማዦር ሹም ሌተና ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔን ጨምሮ የሌሎች የቦርድ ተመራጮችን ሹመት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተቀብሎ አፀደቀ፡፡

ከባንኩ በተገኘው መረጃ መሠረት፣ አንበሳ ባንክ ያቀረባቸውን ተመራጮች ብሔራዊ ባንክ ከገመገመ በኋላ በቦርድ አመራርነት ለማገልገል መሥፈርቶችን እንዳሟሉ በማረጋገጥ ዕውቅና ሰጥቷቸዋል፡፡

አንበሳ ባንክ አዳዲስ የቦርድ አባላትን ለመሰየም ባካሄደው ምርጫ ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት ከተመረጡት ውስጥ ሌተና ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ፣ እንዲሁም የቀድሞ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ይርጋ ታደሰ እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡

በብሔራዊ ባንክ ሹመታቸው የፀደቀላቸው የቦርድ አባላት የሥራ ጊዜያቸው ያጠናቀቁ ነባር የቦርድ አባላትን በመተካት ሥራ ይጀምራሉ፡፡ ባንኩን በቦርድ ሰብሳቢነት ሲመሩ የቆዩት ጣሰው ወልደ ሃና (ፕሮፌሰር) ኃላፊነታቸውን ለአዲስ ተመራጭ የሚያስረክቡ በመሆኑ፣ አንበሳ ባንክ አዲስ የቦርድ ሊቀመንበር ይሰይማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከሰሞኑ ብሔራዊ ባንክ ሹመታቸውን ካፀደቀላቸው የቦርድ አባላት መካከል አዲስ ሊቀመንበር ይሰየማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በቦርድ አባልነታቸው ዳግመኛ የተመረጡና በምርጫ ወቅትም ከፍተኛ ድምፅ ያገኙት አቶ ይርጋ፣ በአሁኑ ወቅት በምክትል ቦርድ ሰብሳቢነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

አንበሳ ባንክ በ2011 ዓ.ም. በጠቅላላው 247 ቅርንጫፎችን በመክፈት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፣ በዚሁ ጊዜ ውስጥ ከታክስ በፊት 695 ሚሊዮን ብር እንዳተረፈ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡  

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች