Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልአርሶ አደሩ ለገጠመው ማኅበራዊ ችግሮች መፍቻ የፈጠራ ሐሳብ ውድድር ተዘጋጀ

አርሶ አደሩ ለገጠመው ማኅበራዊ ችግሮች መፍቻ የፈጠራ ሐሳብ ውድድር ተዘጋጀ

ቀን:

ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ አርሶ አደሩ ለገጠመው ማኅበራዊ ችግሮች መፍትሔ ማመንጨት የሚችሉ የፈጠራ ሐሳቦችን ለውድድር መጋበዙን አስታወቀ፡፡

አቶ አብደላ ዓረብ የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የሶሻል ኢኖቬሽን ቻሌንጅ ፕሮጀክት ማኔጀር ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ለውድድር የሚቀርቡት የፈጠራ ሐሳቦች አነስተኛ መሬት ላላቸው አርሶ አደሮች ምርታማነትና ትርፋማነት መሰናክልና የሥራ ዕድሎችም እንዳይፈጠሩ ማነቆ በሆኑ ማኅበራዊ ችግሮች ዙሪያ መፍትሔዎችን ማመንጨት የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ የሚመነጩትም መፍትሔዎች ከነባር የግብርና ልማዶች ጋር የተቀናጁ፣ ያለምንም ችግርና ውጣ ውረድ በቀላሉ ሊተገበሩ፣ አገራዊ ወይም አገር በቀል የሆኑና ግራ የማያጋቡ ሊሆኑ ይገባል፡፡

ከማኅበራዊ ችግሮቹም መካከል አንዱና ዋነኛው በአርሶ አደሩ ዘንድ የሚታየው የመሬት ጥበት ነው፡፡ ይህም ማለት እያንዳንዱ አርሶ አደር ከአቅሙ በላይ ብዙ ልጆች እንዳሉት፣ በዚህም የተነሳ የቤተሰቡ ቁጥር እንደሚያድግ፣ ቤተሰቡን የሚያስተዳድርበት የእርሻ መሬትም የበሬ ግምባር ያህል ጠባብ ወይም አነስተኛ እንደሆነና ልጆችም ወደ ትምህርት ቤት ቢሄዱም ስምንተኛና አሥረኛ ክፍል ሲደርሱ ትምህርት እንደሚያቋርጡ ነው ያመለከቱት፡፡

- Advertisement -

ትምህርታቸውን ያቋረጡትም ወደ እርሻ እንዳይሰማሩ መሬት የለም፡፡ ያለውም ተይዟል፡፡ በዚህም የተነሳ አማራጩ የቤተሰብ ጥገኛ መሆንና ለሥራ ወደ ከተማ መሰደድ እንደሆነ ነው ከአቶ አብደላ ማብራሪያ ለመረዳት የተቻለው፡፡

ሌላው የሚጠቀሰው ችግር በውርጭ፣ በአካባቢ መጎሳቆልና በሰብል ተባይ ምክንያት የአርሶ አደሩ ምርታማነትና ትርፋማነት እያሽቆለቆለ መምጣቱ ነው፡፡ ከዚህም ሌላ አንዳንዴ ዝናብ ከሚጠበቀውና ከሚያስፈልገው በላይ በመዝነቡ የተነሳ የሚያስከትለው ጎርፍ ሰብሉንና ለም አፈሩን እያጠበና እየፈነቃቀለ ማራቆቱ፣ የሚያስፈልገውና የሚጠበቀው ዝናብ በወቅቱ አለመዝነቡ ለምርታማነት መቀጨጭ ዓብይ ምክንያት መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

በርካታ በሆኑ አጓጉል ልማዳዊ ድርጊቶች፣ መንፈሳዊ በዓላትና በልዩ ልዩ ምክንያቶች ሳቢያ አርሶ አደሩ ከእርሻ ሥራ መስተጓጎሉ ወይም ከሥራ መቅረቱ በምርታማነት ላይ እጅግ ከፍተኛ የሆኑ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መምጣቱን አቶ አብደላ ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡

በዚህም መሠረት ለውድድር የሚቀርቡ የፈጠራ ሐሳቦች በዝርዝር በተጠቀሱት ማኅበራዊ ችግሮች ዙሪያ መፍትሔዎችን ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው መፍትሔዎቹም የሚቀርቡት ከጥር 13 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለ74 ቀናት ያህል ነው፡፡ አቀራረቡም የፈጠራ ሐሳቦችን በድርጅቱ ድረ ገጽ በማስተላለፍ ወይም ለድርጅቱ በአካል በማቅረብ እንደሆነ ነው ያመለከቱት፡፡

የማቅረቢያው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ በፈጠራ ሐሳቦች መካከል ውድድር ተደርጎ አሸናፊ የሆኑ አምስት የፈጠራ ሐሳቦች ይመረጣሉ፡፡ ውድድሩን የሚያካሂደው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ከቢዝነስ ማኅበረሰብ የተወጣጡ ባለሙያዎች ያሉበት የዳኝነት አካል መሆኑን ከማኔጀሩ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡

‹‹በዚህ መልኩ የተመረጡት አምስት የፈጠራ ሐሳብ አመንጪዎች የአቅም ግንባታ ላይ ያተኮረ ሥልጠና የሚያገኙበት መድረክ ይዘጋጃል፡፡ ሥልጠናውንም የሚያካሂዱት ከወርልድ ቪዥን ካናዳ የሚመጡ ባለሙያዎች ሲሆኑ፣ ሥልጠናውም እንዳበቃ ተሳታፊዎቹ የፈጠራ ሐሳቦቻቸውን ለውድድር እንዲያቀርቡ ይጋበዛሉ፤›› ብለዋል፡፡

በዚህም ውድድር የተሻሉ ናቸው የተባሉ ሁለት ሐሳቦች እንደሚመረጡ ከሁለቱም መካከል አንደኛ ለወጣው የ7,000 ዶላር፣ ሁለተኛ ለሆነው ደግሞ የ5,000 ዶላር በብር ተመንዝሮ እንደሚሰጣቸው፣ አሸናፊ የሆኑትን የፈጠራ ሐሳቦች ደግሞ ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ እንደሚተገብራቸው ከአቶ አብደላ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡  

ከፈጠራ ሐሳብ (ኢኖቬቲቭ) ሁለት መልኮች አንዱ የቢዝነስ ፈጠራ ሐሳብ በማንኛውም የንግድ ሥራ ውስጥ የሚንፀባረቅ ማሻሻያን የሚያመላክት ሲሆን፣ የማኅበራዊ ፈጠራ ሐሳብ ደግሞ ማኅበራዊ ችግሮች የሚሻሻሉበትንና አዋጭ የሆኑ አቅጣጫዎችን ማመንጨት የሚችል ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...