Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበ450 ሚሊዮን ብር የተገነባው የእናቶችና ሕፃናት ሕክምና ማዕከል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

በ450 ሚሊዮን ብር የተገነባው የእናቶችና ሕፃናት ሕክምና ማዕከል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ቀን:

የሥነ ተዋልዶ ጤና ልቀት ማዕከል ሊገነባ ነው

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ፣ በ450 ሚሊዮን ብር የተገነባው የእናቶችና የሕፃናት ሕክምና ማዕከል ጥር 9 ቀን 2012 ዓ.ም. ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡  

በሁለት ሺሕ ሜትር ካሬ ቦታ ላይ የተገነባውና የስፔሻሊቲ ሆስፒታል ደረጃ ያለው የሕክምና ማዕከሉ ባለስምንት ፎቅ ሲሆን፣ ለእናቶችና ሕፃናት የሕክምና አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ በርካታ ክፍሎች አሉት፡፡ የሕክምና ማዕከሉ 456 አልጋዎችን የማስተናገድ አቅም ያላቸው ክፍሎች፣ እንዲሁም 13 የቀዶ ሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ ሰፋፊ ክፍሎችና 16 የሕፃናት የጽኑ ሕሙማን አገልግሎት መስጫ ክፍሎች አሉት።

- Advertisement -

የማዋለድ አገልግሎትን ጨምሮ የሴቶች የካንሰር ሕክምና፣ የጡትና የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ልየታና ሕክምና ይሰጣል። መደበኛ የጨቅላ ሕፃናት ሕክምና እስከ ልብ ቀዶ ሕክምና ድረስ የዘለቁ ሙሉ የሕፃናት ሕክምና ይሰጣል። ሆስፒታሉ በቀን ከ2500 በላይ ለሚሆኑ እናቶችና እስከ 300 ለሚጠጉ ጨቅላ ሕፃናት አገልግሎት መስጠት ይችላል።

በተያያዘ ዜና በዕለቱ በአምስት ሚሊዮን ዶላር ለሚገነባው የሥነ ተዋልዶ ጤና የልቀት ማዕከል ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡ የልቀት ማዕከሉ በተዋልዶ ጤና ዙሪያ ያተኮሩ የምርምርና የሥልጠና ሥራዎች የሚሠሩበት እንደሆነ ታውቋል፡፡

ባለአራት ፎቅ የሚሆነውን የልቀት ማዕከሉን የግንባታ ወጪ የሚሸፍነው የሱዛን ቶምሰን ቡፌት ፋውንዴሽን  መሆኑን ከሕክምና ኮሌጁ ፕሮቮስት ወንድማገኝ ገዛኸኝ (ዶ/ር) ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡

በእናቶችና ሕፃናት ጤንነት ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገው ይህ ማዕከል ከሌሎች መሰል ማዕከላት ለየት የሚያደርገው በስፔሻሊት ሆስፒታል ደረጃ የሕክምና አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም ያለው መሆኑ፣ እንዲሁም ከጨቅላ ሕፃናት ውጪ ላሉ ሕፃናት የቀዶ ሕክምና፣ የልብ ቀዶ ሕክምና እንዲሁም የጡትና የማሕፀን በር ጫፍ ቅድመ ካንሰር ሕክምና መስጠቱ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ሕፃናት ገና ሳይወለዱ ወይም በእናታቸው ማሕፀን ውስጥ እያሉ የሚያስፈልጋቸው የሕክምና አገልግሎት የሚሰጥበት ዩኒት/ክፍል ለማቋቋም መታቀዱን ገልጸዋል፡፡

ማዕከሉ ካለው 13 የቀዶ ሕክምና ክፍሎች መካከል ለጊዜው በአምስት የቀዶ ሕክምና ክፍሎች ብቻ አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለጹት ዶ/ር ወንድምአገኝ፣ አንዲትን ነፍሰ ጡር ተከትሎ ማዋለጃ ክፍል መግባት ይከለከል እንደነበር፣ በአሁኑ ወቅት ግን የወላዷ ቤተሰቦች እንዲገቡ እንደሚፈቀድላቸው ተናግረዋል፡፡

በሥነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ በአገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሠሩትና በአሜሪካ የሚችጋን ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ፋካልቲ ባለሙያ ሠናይት ፍሥሐ (ፕሮፌሰር) ‹‹በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ የማሕፀንና ፅንስ ዲፓርትመንት ውስጥ ከዛሬ አሥር ዓመት በፊት ሁለት የፅንስና ማሕፀን ሐኪሞች ብቻ ነበሩ፡፡ አሁን ግን 27 ስፔሻሊስቶች፣ እንዲሁም ከ90 በላይ ሬዜዳንስ ስፔሻሊስት ሐኪሞች ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ካሉት የፅንስና ማሕፀን ሕክምና ማዕከላት መካከል ትልቁና በሚገባ የተደራጀው የሕክምና ኮሌጁ የፅንስና ማሕፀን ክፍል ነው፤›› ብለዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) የእናቶችና ሕፃናት ሕክምና ማዕከል ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት በመስጠትና ሥልጠናዎችንም በማስፋፋት ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...