Monday, May 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየአዲስ አበባ አስተዳደር አቋርጦት የነበረውን የመሬት የሊዝ ጨረታ ሊጀምር ነው

የአዲስ አበባ አስተዳደር አቋርጦት የነበረውን የመሬት የሊዝ ጨረታ ሊጀምር ነው

ቀን:

የግሉን ዘርፍ በማስተባበር አንድ የፓርኪንግ ሕንፃ ቦሌ መንገድ ላይ ሊያስገነባ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቋርጦት የነበረውን የመሬት ሊዝ ጨረታ በቅርቡ እንደሚጀምር፣ ከከተማ አስተዳደሩ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ አመለከተ።

ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ካስተላለፏቸው ውሳኔዎች መካከል፣ ለአልሚዎች ተላልፈው ለበርካታ ዓመታት ታጥረው የተቀመጡ ይዞታዎችን በመንጠቅ ወደ አስተዳደሩ የመሬት ባንክ መመለስ፣ እንዲሁም መሬት ለአዲስ አልሚዎች በጨረታ የሚተላለፍበት ሥርዓት ላይ ያለው የአሠራር ችግር ተጠንቶ እስኪቀረፍ ድረስ መሬት በጨረታ እንዳይቀርብ የሚሉት ይገኙበታል።

- Advertisement -

ይህ ውሳኔ ለረዥም ጊዜ ሳይነሳ መቆየቱ በበርካታ መሬት ፈላጊ ባለሀብቶች ላይ ቅሬታ የፈጠረ መሆኑን፣ በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል። የአስተዳደሩ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ሰሞኑን ለሪፖርተር ባደረሰው መረጃ፣ ተቋርጦ የነበረውን የሊዝ ጨረታ ለመጀመር አስፈላጊው ዝግጅት መገባደዱን አስታውቋል።

እንደ አዲስ በሚጀመረው የሊዝ ጨረታ የሚቀርቡ 100 የተለያየ መጠን ያላቸው የመሬት ይዞታዎች፣ በአንድ ጊዜ እንደሚቀርቡም ለማወቅ ተችሏል። ለጨረታ ከሚቀርቡት የመሬት ይዞታዎች መካከል በርከት ያሉት በከተማዋ መሀል በሚገኙ አካባቢዎች የተለዩ መሆኑን በከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ጨረታው በቅርቡ እንደሚጀመርና ትክክለኛውም ቀን ወቅቱ ሲደርስ ለሕዝብ በይፋ እንደሚገለጽ ተጠቁሟል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ዓርብ ጥር 8 ቀን 2012 ዓ.ም. በከተማዋ ከሚገኙ ከሁሉም የንግድ ባንክ አመራሮች ጋር፣ ለከተማዋ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን በጋራ መሥራት ስለሚቻልበት አሠራር መወያየታቸው ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በዚህም ውይይት የከተማ አስተዳደሩ ለታለመው የሥራ ፈጠራ የሚውል መሬት ለማቅረብ፣ በከተማዋ የሚገኙ ባንኮች ደግሞ ፋይናንስ በማቅረብ ዕቅዱን በትብብር ለመፈጸም ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በዚህ ስምምነት መሠረት በዋናው የቦሌ መንገድ (አፍሪካ ጎዳና) በፍሬንድሺፕ ሕንፃና በዓለም ሲኒማ መካከል የሚገኘውን ክፍት ቦታ፣ የከተማ አስተዳደሩ ያቀረበ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

 በዚህ ቦታ ላይም ለከተማዋ ሥራ አጥ ወጣቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥር፣ ግዙፍ ዘመናዊ የንግድና የፓርኪንግ ሕንፃ በጋራ ለመገንባት ከስምምነት እንደተደረሰ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ በተጨማሪም አስተዳደሩ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ይሰበስብ የነበረውን የገቢ ግብርና የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎች፣ በሁሉም ንግድ ባንኮች ለማድረግ የያዘውን ዕቅድ በተመለከተ የተሠሩ ጥናቶች የደረሱበት ደረጃ ላይ ከባንኮቹ ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...