Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበሕክምና ጥበብ ፍሬ ያፈሩት ጥንዶች

በሕክምና ጥበብ ፍሬ ያፈሩት ጥንዶች

ቀን:

ልጅ መውለድ የፈጣሪ ልዩ ችሮታና በረከት ነው፡፡ ከዚህም በዘለለ የትዳርና የፍቅር መሠረት መሆኑ አሌ የማይባል ሀቅ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ያለመውለድ ችግር (መሐንነት) ሥርጭት ቀላል ባይሆንም ይህ ዓይነቱ ችግር ሴቶች ላይ ብቻ የሚደርስ መስሎ ይታያል፡፡ መካንነት በወንዶችም እንደሚታይ በዘርፉ የተሰማሩ የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በመካንነት ዙሪያ በተወሰነ መልኩ ምርመራዎች ከማድረግ የዘለለ በበቂ ሁኔታ የሕክምና መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችልና በሚገባ የተደራጀ የሕክምና ተቋም እስከ ቅርብ ጊዜ አልነበረም፡፡ በዚህም የተነሳ ጥቂት ጥንዶች እንደየእምነታቸው መጠን ለፈጣሪ ሲማጸኑና ፀበል በመጠጣት አልፎ አልፎ ሲሳካላቸው ይታያል፡፡ የገንዘብ አቅም ያላቸው ብዙዎቹ ጥንዶች ደግሞ በቴክኖሎጂ የታገዘ የመካንነት ሕክምና ወደሚሰጥባቸው አገሮች ሄደው በከፍተኛ ወጪ ለመታከም ይገደዳሉ፡፡ በዚህም ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ ይባክን ነበር፡፡

የችግሩን አሳሳቢነት በመገንዘብ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ከሁለት ዓመት በፊት በአዲስ አበባ በተለምዶ 22 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የመሐንነት ሕክምና ማዕከል አቋቁሟል፡፡ በ1.9 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው ይህ የመካንነት ማዕከል ለሰባት ዓመታት ያህል በጋብቻ ሲኖሩ ለብዙ ዓመታት ልጅ ማፍራት ላልቻሉ ጥንዶች የተመኙትን ልጅ በሕክምና እንዲያቅፉ አድርጓል፡፡

- Advertisement -

የሕክምናው ኮሌጅ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ነዋይ ፀጋዬ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ጥንዶች ልጃቸውን ሊታቀፉ የቻሉት በቴክኖሎጂ የታገዘ የመካንነት ሕክምና ማለትም በአርቲፊሻል (ሰው ሠራሽ) በሆነ ዘዴ ጽንስ የሚፈጠርበትን ሁኔታ በማመቻቸት ነው፡፡ ይህም የወንዱንና የሴቷን ዘር በመፍጠርና በብልቃጥ ውስጥ በመክተትና የዘሩንም ውህደት ወደ ሴትየዋ ማሕፀን በማስገባት (ኢንትሮ ቪትሮ ፈርትላይዜሽን) የሚፈጸም ነው፡፡

ከመንግሥት ሕክምና ተቋማት መካከል ኢንትሮ ቬትሮ ፊርትላይዜሽን የተባለውን የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ማዕከሉ የመጀመርያው መሆኑን ኃላፊ ጠቆሙ፡፡ በዚህ መልኩ ጥር 1 ቀን 2012 ዓ.ም. የተወለደችውም ሕፃን በአሁኑ ጊዜ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

በሕክምና ጥበብ የሚወለዱ ቁጥራቸው 70 የሚደርሱ ነፍሰጡሮችም በቀጣይ ወራት ልጃቸውን ለማቀፍ በመጠባበቅ ላይ እንደሆኑ ከኃላፊው ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ የመሐንነት ሕክምና ማዕከል ተመርቆ የተከፈተው ሚያዝያ 2010 ዓ.ም. ሲሆን ሕክምናውን ፍለጋ ወደ ውጪ የሚሄዱ ዜጎችን እንግልት እንዳስቀረና በዚህም ሊወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሪ እንዳዳነ አቶ ነዋይ ተናግረዋል፡፡ የሕክምናው ኮሌጅ በመጪው ሁለት ዓመታት በአገር ውስጥ የማይገኙ ሌሎች የሕክምና አገልግሎቶችን ለመጀመር በሒደት ላይ መሆኑንም አውስተዋል፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት የአዳማ የግል ጠቅላላ ሆስፒታል የመሐንነት ሕክምና ክፍል ‹‹በኢንትሮ ቪትሮ ፈርትላይዜሽን›› ሕክምና ጥንዶች ልጅ እንዲያቅፉ ማስቻሉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...