Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናፓርላማውን ለቁጥጥር የሚያግዙ ተቋማትና የመብት ተሟጋቾች የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ረቂቅ አዋጅ...

ፓርላማውን ለቁጥጥር የሚያግዙ ተቋማትና የመብት ተሟጋቾች የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ረቂቅ አዋጅ እንዳይፀድቅ ጠየቁ

ቀን:

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠራው ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች በተለይም ምክር ቤቱ በሥራ አስፈጻሚው መንግሥት ላይ ለሚያደርገው ቁጥጥር ሙያዊ ድጋፍ እንዲሰጡ ተብለው የተቋቋሙ መንግሥታዊ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃርጭትን ለመከላከል የተረቀቀው የወንጀል ሕግን በመተቸት፣ ፓርላማው ረቂቅ አዋጁን በዚህ ሁኔታ ሊያፀድቀው እንደማይገባ አሳሰቡ፡፡

የፓርላማው የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲያዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ረቂቅ አዋጁን ለመመርመር ረቡዕ ታኅሳስ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. በጠራውዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ በርከት ያሉ በፕሬስ ነፃነትና በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ የሚሟገቱ የሲቪክ ተቋማት ተወካዮች፣ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት፣ እንዲሁም በግላቸው የሚንቀሳቀሱ የሕግ ባለሙያዎችለፓርላማው ተጠሪ የሆኑ የዴሞክራሲ ተቋማት አመራሮችና ውስን የሚዲያ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

ከሞላ ጎደል ሁሉም ተሳታፊዎች ለምክር ቤቱ የቀረበው የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃርጭትን ለመከላከል የቀረበው ረቂቅ የወንጀል ሕግ፣ በሕገ መንግሥቱ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለትን የፕሬስና የመናገር ነፃነትን በአደገኛ ሁኔታ ይጨፈልቃል የሚል ሥጋት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

መንግሥታት ሁልጊዜ ሲጀምሩ የፕሬስ (የሚዲያ) ነፃነትን ይፈቅዱና ፕሬሱ ማበብ ሲጀምር የሚዲያው አጠቃቀም አሳሳቢ ሆኗል ብለው ባወጧቸውጎች የሚዲያ ነፃነት እየጠፋ መሄዱን፣ ከሌሎች አገሮች የመንግሥታት ታሪክም ሆነ በተለየ ሁኔታ ደግሞ በኢትዮጵያ ከነበሩ ተሞክሮዎች መረዳት እንደሚቻል ለፓርላማው ተጠሪ የሆነው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (/) አመላክተዋል፡፡ በንጉሡ ዘመን መጀመሪያ ላይ የሚዲያው ሚና ያበበበት እንደነበር ነገር ግን ይህንን ተከትሎ በወጣው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሰናከሉን፣ በደርግ የመጀመሪያዎቹ ዘመን በተመሳሳይ ሁኔታ ሚዲያው ዳግም ማንሰራራት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም፣ ይህንን ተከትሎ በወጣው ልዩ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ዳግም እንደተሰናከለ፣ ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን ሲመጣም እንዲሁ ዳግም ሚዲያው ማበብ ጀምሮ የነበረ ቢሆንም፣ጥሎ በወጣው የፕሬስ ሕግ መመታቱን ማሳያዎችን ዋና ኮሚሽነሩ ጠቃቅሰዋል፡፡

‹‹አሁንም አዲስ በተጀመረው የፖለቲካ ምዕራፍ ሚዲያው አዲስ የነፃነት ምዕራፍ እንዲያገኝ በሩ ተከፍቶ ሳለ ተመሳሳይ መንገድ በመከተል ይህ ሕግ እንዲወጣ መፈለጉ ያሠጋኛል፤›› ሲሉ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል (/) አስረድተዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥታት የፕሬስ ነፃነትን በተመለከተ የተከተሉትን መንገድና የዚህን ፖለቲካዊ አንድምታ ለቋሚ ኮሚቴው ለማስገንዘብ ሞክረዋል፡፡

የአሁኑን ከሌሎቹ መንግሥታት ልዩ የሚያደርገው የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃርጭትን ለመከላከል የተረቀቀው አዋጅ ፍላጎት የፕሬስ ነፃነትን ለመገደብ ሳይሆን፣ ለማስተዳደር ነው መባሉና አዋጁንም አስፈላጊ የሚያደርጉ ተቀባይነት ያላቸው ምክንያቶች መሬት ላይ መኖራቸው እንደሆነ የተናገሩት ዋና ኮሚሽነሩ፣ ‹‹ቢሆንም ያሠጋኛል፣ እጅግ ከባድ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል›› ብለዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ መፅደቅ ካለበትም የሐሰተኛ መረጃርጭትን የተመለከቱት አንቀጾች ሙሉ በሙሉ ተለይተው ከረቂቁ እንዲወጡ መደረግ አለበት የሚል ምክረ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡

ምክንያታቸውን ሲያስረዱም፣ ‹‹የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ሁለት የተለያዩንሰሳቦች ናቸው፡፡ ሁለቱንሰሳቦች ሥራ ላይ አዋዋላቸውም የተለያየ ነው፡፡ በመሆኑም ሁለቱን ጽንሰሳቦች በአንድ ሕግ ለማስተዳደር መሞከር ስህተት ነው፡፡ ከዚህ ባለፈም የሐሰተኛርጭትን በወንጀል ሕግ መከላከል ፅንሰ ሐሳብ በበርካታ አገሮች የሚዲያ ነፃነትን ለመግደል ጥቅም ላይ የዋለ በመሆኑ ያሳስበኛል፤›› ብለዋል፡፡ የሐሰተኛ መረጃርጭትን የሚመለከቱ አንቀጾች በሙሉ ከረቂቅ አዋጁ ከወጡ በኋላም የጥላቻ ንግግርን የሚመለከቱት አንቀጾች ልዩ ጥንቃቄ ተደርጎ፣ የዘር ፍጅትን፣ የብሔርናይማኖታዊ ግጭትን የሚያስከትሉ የጥላቻ ንግግሮችን ለመከላከል ብቻ እንዲውል ጠቦ ዳግም መቀረፅ እንደሚገባው ተናረዋል፡፡

ይህንን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ የጥላቻ ንግግርን በወንጀል ሕግ ለመከላከል የሞከሩ አገሮች ችግሩን አባብሰው ተቸግረው እንደሚገኙ የገልጸው፣ የጥላቻ ንግግርን ፈፅሞ ማስቀረት እንደማይቻልም ገልጸዋል፡፡ የጥላቻ ንግግርን በወንጀል ሕግ መከላከል ተገቢ የሚሆነው ከላይ በተገለጸው ሁኔታ የዘር ፍጅት፣ በሃይማኖትና በብሔሮች መካከል ግጭት በሚፈጥሩ ጥላቻዎች ላይ ብቻ ትኩረት ካደረገ መሆኑን በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡ ‹‹የሚነቀፉ ወይም የሚወገዙጥላቻ ንግግሮች ግን በአንድገር ውስጥ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ብዝኃነት ባለባቸውገሮች የሚነቀፉ የጥላቻ ንግግሮችን ማስቀረት የማይቻል በመሆኑ፣ ማኅበረሰቡ እንዲለማመደው ማድረግና ማኅበረሰቡን በትምህርት በማነፅ ሊስተካከሉ የሚችሉ ናቸው፤›› ብለዋል፡፡

ተመሳሳይሳብ የሰነዘረው የፎርቹን ጋዜጣ አሳታሚ ድርጅት ባለቤት አቶ ታምራት ገብረ ጊዮርጊስ፣ ‹‹መውደድና መጥላት ሰብዓዊ ባህሪያት ናቸው፡፡ ለመናገር ነፃነት መንግሥታዊ ጥበቃ የሚደረግበት መሠረታዊ ምክንያት ሰዎች ጥላቻቸውን ጭምር እንዲገልጹ ነው፤›› ብሏል፡፡ ‹‹ሰዎች የፍቅር ቃላትን ብቻ እንዲናገሩ ነፃነት አያስፈልጋቸውም፤›› ሲልም አክሏል፡፡

በሰብዓዊ መብት ተሟጋችነታቸው የሚታወቁት የሕግ ባለሙያና ጠበቃው አቶ አምሐ መኮንን በበኩላቸው፣ የጥላቻ ንግግር ማለት ምን እንደሆነ ባልታወቀበትና አከራካሪ በሆነበት የፖለቲካውድ ውስጥ፣ ይህንን ሕግ ተግባራዊ ማድረግ አስቸጋሪ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ ‹‹ለአንድ ቡድን የመብት መጠየቂያ የሆነ ንግግር፣ ለሌላ ቡድን የጥላቻ መግለጫ ነው፤›› ያሉት አቶ አምሐ፣ ‹‹በዚህ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ የጥላቻ ንግግር የሚባለው የቱ ነው?›› ሲሉጋታቸውን በጥያቄ መልክ አንስተዋል፡፡

የዲጂታል መብቶች ተሟጋች ቡድንን የወከሉት የሕግ ባለሙያው አቶ ዮሐንስ እንየው፣ ‹‹አንድ መረጃ እውነተኛ ወይም ሐሰተኛ መሆኑ እንዴት ነው የሚረጋገጠው?›› ሲሉ ነቀፌታ አዘል አስተያየታቸውን በጥያቄ መልክ ሰንዝረዋል፡፡ አንድ መረጃ እውነተኛ ወይም ሐሰተኛ መሆኑ የሚረጋገጠው በእውነት አረጋጋጮች ነው (ፋክት ቼከርስ) ነው? ወይስ በዓቃቤ ሕግ? ሲሉ ባነሱት ጥያቄ ለጉዳዩ ሙያተኛ ባልሆኑቃቤያነጎች ትርጓሜ፣ የፕሬስ ነፃነት አደጋ ሊገጥመው እንደሚችል ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

በማከልም ኢትዮጵያ የተቀበለችውና የሕገ መንግሥቷ አካል እንዲሆን ያደረገችውለም አቀፉ የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ኮንቬንሽን (ICCPR) አገሮች ብሔርን፣ ዘርንና ሃይማኖትን የተመለከቱ የጥላቻ ንግግሮች በሰዎች ላይ ጥቃትና መገለል እንዳይደርስ በሕግ መጠበቅ እንደሚገባቸው ቢደነግግም፣ ይህንን መሠረት በማድረግ አገሮች የሚያወጡት ሕግ የመናገርና የፕሬስ ነፃነት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥበቃ እንዲደረግ የሚያስገድድ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በዚህም መሠረት በኮንቬንሽኑ ድንጋጌ አንቀጽ 20 አገሮች በሚያወጡት ሕግ ሊጥሉት የሚችሉት ክልከላ ግጭት በሚፈጥር የጥላቻ ቅስቀሳን (advocacy of hatred) ብቻ የተመለከተ መሆን እንደሚገባው መደንገጉን የተናገሩት ባለሙያው፣ ኮንቬንሽኑ የጥላቻ ቅስቀሳ ክልከላ እንዲደረግበት የደነገገበት ምክንያት ቅስቀሳ በሚለው ውስጥ ግጭት ለመቀስቀስ ሆን ተብሎ የሚደረግ መሆኑን ለመለየት ስለሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ረቂቅ ሕጉ ከዚህ አንፃር ሲመዘን ግልጽነት እንደሚጎድለው አመልከተዋል፡፡

ከሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የተወከሉ የሕግ ባለሙያ በበኩላቸው ረቂቅ አዋጁ አስፈላጊ ነው ብለው እንደማያምኑ ገልጸው፣ ረቂቁ መፅደቁ የግድ አስፈላጊ ከሆነ ደግሞ በሚዲያ ነፃነት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በጥንቃቄ ተቀርፆ መሆን እንዳለበት አስረድተዋል፡፡ ‹‹መረጃማግኘት ነፃነት በአስተሳሰባዊ ይዘቱና ሊያስከትል በሚችለው አስተሳሰባዊ ውጤት ሊገታ አይገባውም፤›› በማለት ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 29 (6) ላይ ባስቀመጠው ድንጋጌ ልዩ ጥበቃ እንዳለው፣ በዚህ መብት ላይ የሚጣል ገደብ በጥንቃቄ መቀረፅ እንደሚገባው መደንገጉን ላቀረቡት አስተያየት ማጠናከሪያ አድርገዋል፡፡

መንግሥታዊ ድንጋጌን መሠረት አድርጎ አስተያየት የሰጠው አቶ ታምራት፣ በመናገርና ሐሳብን በመግለጽ ነፃነት ገደብ ሊጣል የሚችለውጦርነት ቅስቀሳዎችን፣ የወጣቶችን ደኅንነትሰብዓዊና የሰውን ክብር የሚነኩትን ለመካላከል በመሆኑ ፓርላማው ይህንን ሕግ ለማውጣት ሕጋዊ መሠረት እንደሌለው አስረድቷል፡፡

ይህንን ክርክሩን ሲያጠናክርም በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ የፌዴራልና የክልል ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚና ተርጓሚ አካላት ከላይ የተገለጸውን ጨምሮ በሕገ መንግሥቱ ምዕራፍ ሦስት ሥር የተደነገጉ መብቶችንና ነፃነቶችን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነትና ግዴታ፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 13 ላይ መጣሉን፣ እንዲሁም እነዚህ መብቶች የተደነገጉበት የሕገ መንግሥቱ ምዕራፍ ሦስት በቀላሉ እንዳይሻሻል ልዩ መሥፈርቶች በሕገ መንግሥቱ መቀመጡን አስረድቷል፡፡

የተነሱትን ጥያቄዎችና የተንፀባረቁትን አቋሞች በተመለከተ ረቂቅጉን ያዘጋጀው የፌዴራል ጠቅላይቃቤ ሕግ ምክትል ጠቅላይቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (/) በሰጡት ምላሽ፣ ረቂቁ የተሰናዳው የፕሬስ ነፃነትን ለመጋፋት እንዳልሆነና የመናገርና የፕሬስ ነፃነትን የሚጋፋው የወንጀለኛ መቅጫ ድንጋጌዎች እንዲሻሩ በዚህ ረቂቅ አዋጅ ተካቶ የቀረበበት ምክንያትም ለፕሬስ ነፃነት ጥበቃ ሲባል እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪ ክልከላ የሚደረገው ሆነ ተብሎ በሚፈጸም የጥላቻ ንግግርናሰተኛ መረጃርጭቶች ላይ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አበበ ገዴቦ ከነበረው ውይይት ጠቃሚ መረጃዎችን መውሰድ እንደተቻለ ገልጸው፣ ቋሚ ኮሚቴው በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለበት ተመካክሮ ይወስናል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...