Saturday, May 18, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየሕወሓት ጠቅላላ ጉባዔ በኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች ውህደትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ለመወሰን በሳምንቱ...

የሕወሓት ጠቅላላ ጉባዔ በኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች ውህደትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ለመወሰን በሳምንቱ መጨረሻ ይሰበሰባል

ቀን:

ምርጫ ቦርድ በዚህ ጉባዔ ላይ በታዛቢነት እንዲገኝ ጥሪ መደረጉ ተጠቆመ

በትግራይ እሳት ለመለኮስ ከሚንቀሳቀሱት በመነሳት ትግላችንን እንጀምራለንደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (/)

የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ጠቅላላ ድርጅታዊ ጉባዔ በተያዘው ሳምንት ማጠናቀቂያ ላይ እንደሚካሄድ፣ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል  አቶ ጌታቸው ረዳ አስታወቁ።

- Advertisement -

አቶ ጌታቸው ለሪፖርተር እንደገለጹት የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ እንዲሁም ማዕከላዊ ኮሚቴው የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ውህደትን አስመልክቶ ቀደም ሲል ባሳለፋቸው የውሳኔ ሐሳቦች ላይ ጠቅላላ ጉባዔው ተወያይቶ የመጨረሻ ውሳኔ ያሳልፋል፡፡

በተጨማሪም ሕወሓት ወደፊት በሚከተላቸው ጉዳዮች ላይም ጠቅላላ ጉባዔው መክሮ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ተናግረዋል።

የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶችን ለማዋሀድ የታለፈው ሒደት የግንባሩን መተዳደሪያ ደንብ የጣሰ እንደሆነ የገለጹት አቶ ጌታቸው፣ ጠቅላላ ጉባዔው በሚያሳልፈው ውሳኔ መሠረት ውህደቱ የተፈጸመበት መንገድ ሕግን የጨፈለቀ እንደነበር ለማሳየት ሕወሓት በቀጣይ ሊንቀሳቀስ እንደሚችልም ጠቁመዋል።

በሕገወጥ  መንገድቢሆንም ኢሕአዴግ መፍረሱ አሁን እርግጥ መሆኑን የተናገሩት የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሉ አቶ ጌታቸው፣ሦስቱ የኢሕአዴግ አባል የነበሩ ድርጅቶችና አጋሮች በውህደት አዲስ ፓርቲ የመመሥረት መብት ቢኖራቸውም ኢሕአዴግን መውረስ አይችሉም፤ብለዋል።

ምርጫ ቦርድ በውህደት ለተፈጠረው ፓርቲ ዕውቅና ከመስጠት ባለፈ አዲስ የተመሠረተው ብልፅግና ፓርቲ የኢሕአዴግ ወራሽ ስለመሆኑ ቦርዱ ያስተላለፈው ውሳኔ አለመኖሩን፣ ይህንንም መወሰን ቦርዱ እንደማይችል ገልጸዋል።

ነገሮች ወደዚህ የሚያመሩ ከሆነ ግን ሕወሓት እስከ መጨረሻው ድረስ ሕጋዊ ትግል እንደሚያደርግይህንንም የሚያደርገው ኢሕአዴግ የተለየ ድርጅት ሆኖ ኢሕአዴግን ለማዳን እንደማይሆን ተናግረዋል። ይልቁንም የአገሪቱ ፖለቲካ ሕጋዊነትን የተከተለ፣ የአገሪቱ ተቋማትም ሕጋዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው ከሚል መርህ እንደሆነ ገልጸዋል። በምርጫ ሕጉ መሠረትም በሕወሓት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በታዛቢነት እንዲገኝ ለምርጫ ቦርድ ጥሪ መደረጉን አስታውቀዋል።

በተያያዘ ዜና በአገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የመከረ የትግራይ ሕዝብ ጉባዔ፣ ከቅዳሜ ኅዳር 18 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት በመቀሌ ተካሂዷል።

የሕወሓት አመራሮችን ጨምሮ የትግራይ ሕዝብን የወከሉ ተሳታፊዎች በመከሩበት በዚህ ጉባዔ፣ ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ በሕገወጥ መንገድ እንዲፈርስ መደረጉን በመግለጽ አውግዘዋል። የኢሕአዴግ አባላትን በሕገወጥ  መንገድ በማፍረስና እንዲዋሀዱ በማድረግ የተመሠረተው ፓርቲ የትግራይ ሕዝብን ጥቅም የማያስከብር፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦችን ከኅብረ ብሔራዊ ወደ መልክዓ ምድራዊ ፌዴራሊዝም አስተዳደር የሚወስድ በመሆኑ እንደሚታገሉት፣ በጉባዔው ማጠናቀቂያ ላይ ባወጡት የአቋም መግለጫ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ከሌሎች ፌዴራሊስት ኃይሎች ጋር በመሆን የፌዴራል ሥርዓቱን ለመጠበቅ ሕወሓት የጀመረውን ጥረት እንደሚደግፉ፣ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር  ያልተፈታው የድንበር ጉዳይ የሁለቱን ሕዝቦች ጥቅም በማይጎዳና በሰከነ መንገድ ለመፍታት ሕወሓት ሊሠራ እንደሚገባ አጽኖኦት መስጠታቸውን በአቋም መግለጫቸው አካተዋል።

ይህንን ጉባዔ በንግግር የከፈቱት የሕወሓት ሊቀመንበርና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (/)፣ የትግራይን ሰላምና የሕዝቡን አንድነት ለማወክ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች መኖራቸውን በመጥቀስ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል።

ያለንበት ወቅት የቁርጥ ነው፤ያሉት ደብረ ጽዮን (ዶ/ር)፣ “እነዚህ ኃይሎች ወይ ከትግራይ ሕዝብ ጋር ይሠለፋሉ አልያም ጥግ ይይዛሉ። አሠላለፉ መለየት አለበት፣ አለበለዚያ በትግራይ እንለኩሰዋለን ባሉት እሳት የሚቃጠሉ ይሆናሉ፤ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ‹‹በትግራይ እሳት ለመለኮስ ከሚንቀሳቀሱት በመነሳት ትግላችንን እንጀምራለን፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ