Monday, June 17, 2024

ለክቡር ሚኒስትሩ የቀድሞ ሚኒስትር ስልክ ደወሉላቸው

[የክቡር ሚኒስትሩን ቢሮ አንድ የክፍል ኃላፊ በርግዶ ገባ]

 • ምን ሆነሃል?
 • ምን እየተደረገ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • መጀመሪያ ሥርዓት ይኑርህ እንጂ፡፡
 • የምን ሥርዓት ነው?
 • በሩን እንዴት በርግደህ ነው የገባኸው?
 • ተናድጄ ነዋ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምንድነው ያናደደህ?
 • እዚህ መሥሪያ ቤት እየተደረገ ያለው ነገር ነዋ፡፡
 • እኮ ምንድነው?
 • ክቡር ሚኒስትር እኛ እኮ ለዚህች አገር ሕይወታችንን ሳይቀር የገበርን ሰዎች ነን፡፡
 • ለመሆኑ እናንተ ማን ናችሁ?
 • እሱን ልብዎት ያውቀዋል፡፡
 • ምን ፈልገህ ነው አሁን?
 • ይኸው የበረሃ ጓዶቻችንን ሥልጣን ነጥቃችሁ አባረራችኋቸው፡፡
 • እኛ አላባረርናቸውም ሸሽተው ነው የሄዱት፡፡
 • ትንሽ ግፍ አትፈሩም ግን?
 • ጆሮዬ ነው ወይስ ግፍ ስትል ነው የሰማሁት?
 • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
 • እናንተ ደግሞ ስለግፍ ለማውራት የሞራል ብቃቱ አላችሁ?
 • ምን እያሉ ነው?
 • ከእናንተ በላይ ግፈኛ ታይቶ ይታወቃል እንዴ?
 • ተው ክቡር ሚኒስትር ቀን ጥሎን ነው እንጂ እንደ እኛ ሩህሩህ የለም፡፡
 • ስማ አገሪቱን ለዚህ ያበቃችሁ ግፈኞች ናችሁ፡፡
 • እ…
 • ከራሳችሁ ውጪ ለማንም ግድ የማይሰጣችሁ አረመኔዎች መሆናችሁን አጥተኸው ነው?
 • ለነገሩ የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታል ስለተባለ ምን እልዎታለሁ?
 • አገሪቷን እንደ ግል ንብረታችሁ ቆጥራችሁ ስትፈነጩባት አልነበር እንዴ?
 • ክቡር ሚኒስትር ውለታችን በአንዴ ተረሳ ማለት ነው?
 • የምን ውለታ ነው?
 • በድርቅ ትታወቅ የነበረችን አገር በልማት እንድትታወቅ ያደረጋት ማን ሆነና?
 • ተወኝ እስቲ፡፡
 • ምነው?
 • ሙሉ አገሪቱ ትልቅ እስር ቤት አልነበረች እንዴ?
 • ለማንኛውም ለእኛ እንዲህ አይገባንም ነበር፡፡
 • ምን ተደረጋችሁ?
 • እዚህ የቀረነውም ተጠቅልለን እንድንገባ ነው እንዴ የፈለጋችሁት?
 • ምን እያልክ ነው?
 • ይኸው ከኃላፊነታችን እንድንዘዋወር ደብዳቤ ደርሶናል እኮ?
 • አላሠራ አላችኋ፡፡
 • ምን ማለት ነው?
 • ሁሉን ነገር እያደናቀፋችሁ ምን እናድርግ ታዲያ?
 • ምን አድርገን ነው ያደናቀፍነው?
 • በቢሮክራሲው ውስጥ ተሰግስጋችሁ ምንም ነገር መተግበር አልቻልንም፡፡
 • ስለዚህ እኛን ከቦታ ማፈናቀል ጀመራችሁ?
 • ያው በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም አይደል ተረቱ፡፡
 • አሁን የተመደብንበት ቦታ ግን አይመጥነንም፡፡
 • ምን እያልክ ነው?
 • ከነበርንበት ቦታ የወረደ ነዋ፡፡
 • የበፊቱን ቦታ በአቅማችሁ እኮ አይደለም የያዛችሁት፡፡
 • ታዲያ በምንድነው?
 • በጉልበት!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከአንድ ባለሀብት ጋር ተገናኝተው እያወሩ ነው]

 • እንዴት ነህ?
 • አለሁ ግራ እንደገባኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምንድነው ግራ የሚያጋባህ?
 • ሁሉ ነገር  ነዋ፡፡
 • እንዴት?
 • አገር ውስጥ አይደል እንዴ ያሉት ክቡር ሚኒስትር?
 • ምንድነው የምትለው?
 • ማለቴ ሁሉ ነገር መላ ቅጡ እንደጠፋው ያውቃሉ ብዬ ነዋ፡፡
 • አልገባኝም?
 • ፖለቲካው፣ ኢኮኖሚው  ቢሉ ብቻ ሁሉ ነገር ግራ ያጋባል፡፡
 • ስማ የኢትዮጵያ መፃኢ ዕድል እኮ ብልፅግና ነው፡፡
 • የበፊቶቹም እንዲህ ነበር የሚሉን፡፡
 • እ…
 • ይኸው ባዷችንን አስቀርተውን እብስ አሉ እንጂ፡፡
 • አሁን እኛና እነሱ የምንነፃፀር ነን?
 • ያልጠረጠረ ተመነጠረ አይደል የሚባለው?
 • እ…
 • መጠርጠሩ አይከፋም ብዬ ነው፡፡
 • ለስሰሰሰበበስማ እኛ እኮ የእነሱን ጥፋት ለማረም ነው እየሠራን ያለነው፡፡
 • የእናንተንስ ጥፋት ማን ነው የሚያርመቡበየእናንተንስ ጥፋት ማን ነው የሚያርመው?
 • ምን አበበምን አጠፋን?
 • ምን አሉምን አሉኝ?
 • አአአበበበበአናጠፋም እያልኩህ ሳይሆን ይኼን ያህል ምን የሚያስመርር ነገር አየህ ብዬ ነው፡፡
 • ዓይዓይንዎን ከፍተው ካዩ እኮ ብዙ ነገር አለ፡፡
 • ማለት?
 • ሕገሕገወጥነቱ፣ ዝርፊያው ኧረ ስንቱ?
 • እኛ እኮ የምንሠራው ሕገወጥነትንና ዝርፊያን ለማጥፋት ነው፡፡
 • ክቡክቡር ሚኒስትር እንግዲያው እውነቱን ልንገርዎት?
 • ነንንገረኝ፡፡
 • ጭራሽ ብሶበታል፡፡
 • ምኑ?
 • ሕገወሕገወጥነቱና ዝርፊያው ነዋ፡፡
 • እ…
 • ይኸይኸው በየቦታው አይደል እንዴ መሬት የሚወረረው፡፡
 • እሱ በቅርቡ መፍትሔ ያገኛል፡፡
 • መሬቱ ተወሮ ካለቀ በኋላ መፍትሔ ምን ያደርጋል?
 • እ…
 • ዝርፊያውም ቢሆን ተባብሶበታል፡፡
 • ማን ነው የሚዘርፈው?
 • መንግሥት እኮ ሥራ መፍጠር ሲያቅተው ሌባ እየፈጠረ ያለ ነው የሚመስለው፡፡
 • እ…
 • ከተማዋ ውስጥ ያለ ዝርፊያ እኮ እየተባባሰ ነው፡፡
 • ለማንኛውም ሥራችንን በሚገባ እንድንሠራ የአንተ ድጋፍ ያስፈልገናል፡፡
 • የምን ድጋፍ ክቡር ሚኒስትር?
 • የገንዘብ ድጋፍ ነዋ፡፡
 • ማለት?
 • ለአዲሱ ፓርቲያችን የገንዘብ ድጋፍ አድርግልና?
 • በሉ ክቡር ሚኒስትር እንደ እኔ ሌላ ሰው እንዳይሰማዎት?
 • ለምን?
 • ባለፀጋ እኮ…
 • እ…
 • ይሰጣል እንጂ…
 • እ…
 • አይለምንም!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከደላላ ወዳጃቸው ጋር ተገናኙ]

 • አሁን አመንኩ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምኑን?
 • ዘመኑ የብልፅግና እንደሆነ ነዋ፡፡
 • እንዴት?
 • እናታችን ስታበድረን ነዋ፡፡
 • እናቴ ሞተዋል አላልከኝም ነበር እንዴ?
 • የሁላችንም እናት እኮ ነው ያልኩዎት?
 • ኢትዮጵያን ማለትህ ነው?
 • የለም! የለም!
 • ማን ናት እናታችን ታዲያ?
 • አይኤምኤፍ ናት፡፡
 • እ…
 • ሁሉ ነገር አለቀለት እኮ በቃ፡፡
 • እንዴት?
 • ቻው ቻው ነው ማለት ያለብን፡፡
 • ማንን?
 • ድህነትን ነዋ፡፡
 • እንዲህ በቀላሉ?
 • ቢያንስ እኔና እርስዎ ማለት እንችላለን፡፡
 • ለምን?
 • ከማንም በፊት የምንቋደሰው እኛ ነና፡፡
 • ምኑን?
 • ዶላሩን ነዋ፡፡
 • እ…
 • ክቡር ሚኒስትር መወሰን እኮ ነው ያቃተኝ፡፡
 • ምኑን?
 • የቱን ቢዝነስ እንጀምር የሚለውን ነዋ?
 • እ…
 • የኮንስትራክሽን ዕቃ እናስመጣ ወይስ መኪና የሚለውን መወሰን አልቻልኩም፡፡
 • የደላህ ነህ እባክህ?
 • እንዴት?
 • ዶላሩ እኮ ለአገሪቱ እንጂ ለአንተ አይደለም የሚለቀቀው?
 • ክቡር ሚኒስትር ከሰፈፏማ ካልበላን ሥልጣናችን ምን ሥልጣን ነው?
 • እ…
 • እንደዚህ ዓይነቱ ዕድል መቼም አይገኝም፡፡
 • እንዴት?
 • በዚህ ግርግር ወቅት የድርሻችንን አንስተን ዞር ማለት ነዋ፡፡
 • ምን እያልክ ነው ሰውዬ?
 • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
 • አዲሱ ፓርቲያችን እኮ እንዲህ ዓይነት ነገር አይፈቅድም፡፡
 • የድርሻችንን እናግኝ እንጂ ለእሱ ችግር የለውም፡፡
 • ምን እያልከኝ ነው?
 • የድርሻችንን ካገኘን ክቡር ሚኒስትር…
 • እ…
 • ፓርቲ ብንቀይርስ ምን ችግር አለው?
 • ከምን ወደ ምን ነው የምንቀይረው?
 • ከብልፅግና…
 • እ…
 • ወደ ብልግና!

[ለክቡር ሚኒስትሩ የቀድሞ ሚኒስትር ስልክ ደወሉላቸው]

 • ክቡር ማኒስትር ጆሯችንን አደማችሁት እኮ፡፡
 • በምን?
 • በዚህች ሳተላይት ዜና ነዋ፡፡
 • የቀና ብዙ ያወራል፡፡
 • ገና ከመላኳ አገሮች ዳታ ለመግዛት ጠየቁ ብላችሁ ዜና ትሠራላችሁ?
 • ምን ችግር አለው?
 • ለነገሩ ዜናው ላይ ዳታ መሸጥ ያልቻልነው ዋጋ ገና ስላልወጣለት ነው አለማለታችሁም ጥሩ ነው፡፡
 • ቀልደህ ሞተሃል?
 • ሳተላይቷ ከዚህ ብትመጥቅ ኖሮ ግን ምን ልታደርጉን ነበር?
 • እናንተንም አብረን እንልካችሁ ነበራ፡፡
 • ህዋ ላይ?
 • እህሳ፡፡
 • ይኼን ያህል ጠልታችሁናል እንዴ?
 • ለማንኛውም የሳተላይቷ ነገር ምነው አንገበገባችሁ?
 • ኧረ ምንም፡፡
 • በቅርቡ ድሮን ልንሠራ ነው፡፡
 • ምን አሉኝ?
 • ሰምተሃል እባክህ?
 • አለቀልን በሉኛ፡፡
 • ስነግርህ ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ የሁሉን ነገር ከፍታ ትረግጣለች፡፡
 • ምን እኛንም ልትረግጡን አስባችኋል እንዴ?
 • መቼ ይቀርላችኋል?
 • እ…
 • ሳተላይቷ እኮ ሁሉንም ነገር እየተከታተለች ትልክልናለች፡፡
 • ምን?
 • ከዚህ በኋላ የምትበሉትንና የምትጠጡትን ሳይቀር እናውቃለን፡፡
 • እንደዚያ ከሆነማ ልፈትንዎታ ክቡር ሚኒስትር?
 • ምንድነው የምትፈትነኝ?
 • አሁን ምን እየጠጣሁ ነው?
 • እሱንማ ሳተላይትም ሳንልክ ልነግርህ እችላለሁ፡፡
 • እኮ ምን እየጠጣሁ ነው?
 • ውስኪ፡፡
 • በምን?
 • ደረቁን!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን ቅሬታውንም አልሰማሁም። እንዴት? አልሰማሁማ? የምን ቅሬታ ቀርቦባቸው ነው? ሰሞኑን ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ውድና ቅንጡ አውሮፕላን ተከራይተዋል የሚል ቅሬታ...