Friday, June 2, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የብርሃን ባንክ የዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎቱ በ49 በመቶ ማደጉ ተገለጸ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ብርሃን ባንክ ባጠናቀቀው 2011 የሒሳብ ዓመት ከዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት 49 በመቶ ብልጫ ያለው ውጭ ምንዛሪ ማግኘቱንና ዓመታዊ ትርፉንም በ42.2 በመቶ ማሳደጉን ገለጸ፡፡

ባንኩ ባለፈው ሳምንት ባካሄው የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ይፋ እንዳደረገው፣ ከዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት 161.7 ሚሊዮን ዶላር ማግኘት ችሏል፡፡ ይህ የውጭ ምንዛሪ ግኝት ከባለፈው ዓመት አንፃር በ53.2 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ ያሳየ መሆኑን ተጠቅሷል፡፡፡ የተቋቋመበትን አሥረኛ ዓመት ባከበረ ማግሥት ይፋ ባደረገው ዓመታዊ ሪፖርቱ መረዳት እንደተቻለውም፣ የባንኩ ትርፍ 580.1 ሚሊዮን ብር መድረሱን ነው፡፡

የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ጉማቸው ኩሴ የተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በአገሪቱ ውስጥ የታየው የፖለቲካዊ፣ የኢኮኖሚያዊና የማኅበራዊ ተግዳሮቶች ከፍተኛ የነበሩ ቢሆንም፣ ተግዳሮቶቹን ለመሻገር ባንኩ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ቀይሶ ተግባራዊ በማድረጉ በሁሉም የሥራ ዘርፎች አጥጋቢ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ ለዚህም አንዱ ማሳያ የትርፍ መጠኑን ከግብር በፊት 580.1 ሚሊዮን ብር ማድረሱ ነው ብለዋል፡፡

ይህም አፈጻጸም ካለፈው የሒሳብ ዓመት ጋር በንፅፅር ሲታይ 169.1 ሚሊዮን ብር ወይም የ41.2 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ በመሆኑም የባንኩ 1,000 ብር ዋጋ ያለው አክሲዮን የትርፍ መጠኑ 246.5 ብር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ባንኩ ባለፈው የሒሳብ ዓመት ካስመዘገበው አፈጻጸም ጋር ሲወዳደር የተሻለ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ ባንኩ በቀደመው ዓመት የአንድ አክሲዮን ትርፍ 203.6 ብር ነበር፡፡

በሒሳብ ዓመቱ መጨረሻ የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ 14.9 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ካለፈው የሒሳብ ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ4.1 ቢሊዮን ብር ወይም የ37.8 በመቶ ዕድገት ማስመዝገብ ችሏል፡፡

የባንኩ የብድር ክምችት ባለፈው ዓመት ከነበረው በ42.1 በመቶ በማደግ 10.2 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም በ3.02 በመቶ ዕድገት የታየበት ነው፡፡ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ደግሞ ካለፈው ዓመት በ36.3 በመቶ ዕድገት አሳይቶ 19.2 ቢሊዮን ብር እንደደረሰም ተገልጿል፡፡

የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል ከባለፈው ዓመት በ27 በመቶ በማደግ 2.8 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ የተከፈለ ካፒታል ደግሞ የ17 በመቶ ዕድገት በማሳየት ሁለት ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡  የባንኩ የደንበኞች ቁጥር ደግሞ በ133 ሺሕ ወይም በ25.5 በመቶ በማደግ በሒሳብ ዓመቱ መጨረሻ 657,026 ደርሷል፡፡ በተጨማሪም ባንኩ የሞባይል ቶፕ አፕና አፕሊኬሽን ቤዝድ ሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶች እንዲሁም የማስተር ካርድ የክፍያ አገልግሎት በመጀመር ደንበኞች የተቀላጠፈና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉንም በጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተገልጿል፡፡

ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ ውስጥ 18 አዳዲስ ቅርንጫፎችን የከፈተ ሲሆን፣ አጠቃላይ የቅርንጫፍ ሥርጭቱን 200 ማድረስ ችሏል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች