Wednesday, June 7, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

አቢሲኒያ ባንክ የብድር ወለድ ምጣኔውን እንደሚቀንስ አስታወቀ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል ባንኮች ከእያንዳንዱ ብድራቸው 27 በመቶ እያሰሉ ለቦንድ ግዥ እንዲያውሉ የሚያስገድደውን መመርያ ከሰረዘ በኋላ፣ አቢሲኒያ ባንክም የብድር ወለድ ምጣኔውን እስከ ስድስት በመቶ እንደሚቀንስ አስታውቋል፡፡

ባንኩ ይህንኑ በማስመልከት እንደገለጸው፣ መንግሥት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየወሰዳቸው ያሉትን የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ እንዲሁም በቀጣይ አሥር ዓመታት ሊያሳካቸው ያሰባቸውን ለውጦች ከግምት በማስገባት የተወሰደ ዕርምጃ መሆኑን ነው፡፡ ‹‹በአጠቃላይ በፋይናንስ ዘርፉ መልካም የሆነ ፉክክርና መነቃቃት ሊፈጥሩ የሚችሉ የፖሊሲ ማሻሻያዎና አዳዲስ አሠራሮች ይኖራሉ፤›› የሚለው የባንኩ መረጃ፣ የተቀዛቀዘውን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት፣ ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ እንደሚያግዝ በመታመኑ ባንኩ የብድር ወለድ መጠኑን ቀንሷል ብሏል፡፡

በዚሁ መሠረት የማበደሪያ ተመንና የአገልግሎት ክፍያዎች ከሌሎች ባንኮች አንፃር ሲቃኙ ተወዳዳሪና የተሻለ ተማራጭ ባንክ እንዲሆን የሚያስችሉትን ሥራዎች እያከናወነ ሲሆን፣ አንዱ ብድር ወለድ መጠን መቀነስ መሆኑንም ገልጿል፡፡

በቅርቡ ማሻሻያ ከተደረገባቸው መመርያዎች መካከል የግል ባንኮች በአስገዳጅነት በእያንዳንዱ ብድር ላይ የ27 በመቶ በብሔራዊ ባንክ የቦንድ ግዥ መፈጽም እንዲቀር መደረጉ በዋናነት የሚጠቀስ ሲሆን፣ ይኼውም በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የሚያበድሩትን የብድር መጠን ለማሳደግና የብድር ተመኑንም ዝቅ ለማድረግ የሚያስችል በጎ ዕርምጃ እንደሆነ ባንኩ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት የብድር ወለድና ተያያዥ የአገልግሎት ክፍያዎቹን እንደ ብድር ዓይነቱ እስከ ስድስት በመቶ ቅናሽ በማድረግ እ.ኤ.አ. ከጥር 2020 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ይኼው የአቢሲኒያ ባንክ መረጃ ይገልጻል፡፡

ባንኩ በመንግሥት በኩል የሚወሰዱ ማሻሻዎችንና የአገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ የሚያወጣቸውን መመርያዎችን ተከትሎ በብድር ወለድና በሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎች እንደ ኢኮኖሚያዊ ነባራዊ ሁኔታው መጠነኛ ጭማሪና ቅናሽ ሲያደረግ መቆየቱንም የባንኩ መረጃ ጠቅሷል፡፡ ወደፊትም የባንኩ መሪ ዕቅዱንና የኢኮኖሚ ሥርዓት መሠረት በማድረግ የብድርና የአገልግሎት ዋጋ ክፍያዎችን እያስተካከለ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡ መንግሥት 27 በመቶ የቦንድ ግዥ መመርያን ካነሳ በኋላ እስካሁን አዋሽ ባንክ እስከ 4.5 በመቶ የብድር ወለድ መጠንን እንደሚቀንስ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡ ሌሎች ባንኮችም ተመሳሳይ ዕርምጃ ይወስዳሉ ተብሎ እየተጠበቀ ሲሆን፣ ሰሞኑን በተሰጠ መግለጫም ዓባይ ባንክ ተመሳሳይ ዕርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡ አቢሲኒያ ባንክ 390 በላይ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን፣ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ከግብር በፊት 1.02 ቢሊዮን ብር ማትረፉን መግለጹ ይታወሳል፡፡  

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች