Thursday, June 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የተሻለ ወለድ የሚገኝበት የግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ ዛሬ በይፋ ይጀመራል

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በገበያ ምጣኔ የተሻለ ወለድ በማስገኘት ግብይት የሚፈጸምበት የመንግሥት የግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ ገበያ፣ ዛሬ ረቡዕ ኅዳር 24 ቀን 2012 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በይፋ ይጀመራል፡፡ በይፋ በሚጀመረው የመንግሥት የግምጃ ቤት ሰነድ ጨረታ ተሳታፊ ለመሆን፣ የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ግዥ ለመፈጸም የሚያስችላቸውን ሰነድ መግዛታቸው ታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም ከነበረው አሠራር በጨረታ የግምጃ ቤት ሰነድ ግዥ ለመፈጸም በሚያስችለው አዲሱ አሠራር፣ ለመጀመርያ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ ገበያ ባንኮችና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ተጫራች በመሆን ይቀርባሉ፡፡ ሌሎች የቢዝነስ ተቋማትም የዚሁ አካል ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በቀጣይ የስቶክ ገበያ ለመጀመር በግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ መንግሥት የተለያዩ ገበያዎችን ለመፍጠር ተጠቁሟል፡፡ ብሔራዊ ባንክ የግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጩ ውጤታማ ከሆነ በቀጣይ ወደ ስቶክ ማርኬት ገበያ ይገባል፡፡

ብሔራዊ ባንክ 27 በመቶ የቦንድ ግዥ መመርያን በሻረ ማግሥት ባንኮች ተሳታፊ የሚሆኑበትና በገበያ ዋጋ በየሳምንቱ ረቡዕ በሚካሄደው የመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ ባንኮችና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ እንዲሁም ሌሎች የቢዝነስ ተቋማት ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡

በመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ግብይት የግሉ ዘርፍ የሚሳተፍበት ይህ አሠራር፣ ለመንግሥትም ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል፡፡ መንግሥት ለተለያዩ ተግባራት የሚያስፈልገውን ፋይናንስ ከገበያ እንዲያገኝ እንደሚያስችለው ታምኖበታል፡፡

ወደፊት ከባንኮችና ከብሔራዊ ባንክ ተበድሮ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን ስለሚያዳግተው፣ ከግምጃ ቤት ሰነድና ከመሳሰሉት ግብይቶች የበጀት ጉድለቱንና ሌሎች ወጪዎቹን መሸፈን እንደሚችልም ይነገራል፡፡

የኢኮኖሚው ባለሙያዎች እንደሚጠቁሙት እንዲህ ዓይነት ገበያ መፈጠሩ መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ መበደሩን አቁሞ፣ ከገበያ ከሚያገኘው ገንዘብ በመጠቀም የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ያስችለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግሥት 27 በመቶ የቦንድ ግዥ መመርያውን በማንሳቱ ባንኮች የብድር ወለድ መጠናቸውን እንዲቀንሱ፣ ብሔራዊ ባንክ ለግል ባንኮች ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ብሔራዊ ባንክ የባንኮችንና የኢንሹራንስ ኩባንያዎችን ከፍተኛ አመራሮች በመጋበዝ ሰሞኑን ባደረገው ውይይት የ27 በመቶ የቦንድ ግዥ መመርያ በመነሳቱ፣ እነሱም የብድር ወለድ ምጣኔያቸውን እንዲቀንሱ ላቀረበው ጥያቄ ባንኮቹም አዎንታዊ ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አንዳንድ ባንኮችም የብድር ወለድ ምጣኔያቸውን እንደሚቀንሱ በወቅቱ መግለጻቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከዚህ ውይይት ቀደም ብሎ አዋሽ ባንክ ከ0.5 እስከ 4.5 ፐርሰንት የሚደርስ የወለድ ቅናሽ ማድረጉን በይፋ ያስታወቀ ሲሆን፣ ሌሎች ባንኮችም የብድር ወለድ ምጣኔያቸውን ለማስተካከል እየሠሩ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች