Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዓለምስደተኛ ሕፃናት በአሜሪካ ማቆያ

ስደተኛ ሕፃናት በአሜሪካ ማቆያ

ቀን:

በመላው ዓለም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ስደተኛ ሕፃናት በፖሊስ ጣቢያና በስደተኞች ማቆያ ማዕከላት ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል በአሜሪካ የስደተኞች ማዕከል ብቻ ከ100,000 በላይ ስደተኛ ሕፃናት ከስደት ጋር በተያያዘ ታስረው ይገኛሉ፡፡ አሜሪካ ከፍተኛውን የሕፃናት ስደተኞች ቁጥር በስደተኞች ማቆያ ማዕከል በመያዝ በዓለም ውስጥ ግንባር ቀደም መሆኗን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) አስታውቋል፡፡ ሕፃናት በማቆያ ማዕከል የማስቀመጥ እንቅስቃሴውም የዓለም አቀፍ ሕጉን እንደሚፃረር አመልክቷል፡፡

በተመድ ግሎባል ስተዲ ኦን ችልድረን ዲፕራይቭድ ኦፍ ሊበርቲ እንዳመለከተው፣ ስደተኛ ሕፃናትን ከወላጆች ነጥሎ በተወሰነ ማቆያ ማዕከል ማኖር የተከለከለ ቢሆንም ይህ በአሜሪካ እየተተገበረ ነው፡፡ አሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፣ በአሜሪካና በሜክሲኮ ድንበር በተቋቋመው የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ሕፃናትን ከቤተሰቦቻቸው በመለየት ማኖሩ ዓለም አቀፍ የሕፃናት መብት ስምምነትን የጣሰ መሆኑንም ጥናቱ አሳይቷል፡፡

ስደተኛ ሕፃናት በአሜሪካ ማቆያ

- Advertisement -

 

አሜሪካ ዋና ዋና የሆኑ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን አፅድቃለች፡፡ ከእነዚህም መካከል አንደኛው የሰዎችን የሲቪልና የፖለቲካ ዋስትና መጠበቅና ማክበር ሲሆን፣ በአንፃሩ ደግሞ ሰዎችን ማሰቃየትን ማስቀረት ይገኝበታል፡፡ ሆኖም አሜሪካ የሕፃናትን መብት ያላፀደቀች ብቸኛዋ አገር መሆኗን በቬና ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ሕግ ምሁር ማንፍሬድ ኖዋክ (ፕሮፌሰር) ተናግረዋል፡፡

በአሜሪካ ጨቅላ ሕፃናትን ከቤተሰቦቻቸው በመለየት በስደተኞች ማቆያ ማዕከል እንዲቀመጡ የተደረገበት ምክንያት ከመካከለኛው አሜሪካ በሕገወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ የሚፈልሱትን ስደተኞች ለመቆጣጠር ሲባል ነው፡፡ ይህም ሆኖ ግን በሁለቱም ስምምነቶች መሠረት እንዲህ ዓይነቱ ተግባር የተከለከለ ነው፡፡

በማዕከሉ ከሚገኙት 100,000 ሕፃናት መካከል 29,000 ሕፃናት ከአይኤስ ጋር ተያያዥነት ያላቸውና ከሰሜን ሶሪያና ኢራቅ የመጡ ሲሆን ጥቂቶቹም የሕፃናት ወታደሮች እንደሆኑ ታውቋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሥልጣን ላይ ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ ምንም ዓይነት መቻቻል የሌለበት ጠንካራና አግላይ የስደተኛ ፖሊሲ አውጥተዋል፡፡ በዚህም ፖሊሲ መንግሥታቸው የስደተኛ ቤተሰብ መለያየትን ተግባራዊ አድርጓል፡፡

በ2010 ዓ.ም. ሕፃናትን ከቤተሰቦቻቸው ለይቶ የማኖሩ ሥራ ቆሟል ቢባልም፣ አንዳንድ የስደተኛ መብት ተሟጋቾች ከቤተሰብ የመለየቱ ሥራ በተዘዋዋሪ መንገድ መቀጠሉን ይሞግታሉ፡፡

አሶሼትድ ፕሬስና ባለፈው ሳምንት የወጣውን የመንግሥታቱን መረጃ ዋቢ አድርጎ እንደገለጸው፣ ባለፉት ዓመታት ብቻ 69,550 ስደተኛ ሕፃናት በአሜሪካ መንግሥት ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ዓመታት ሲነፃፀርም ሕፃናቱ ረዥም ሰዓት በመጠለያ ውስጥ ያሳልፋሉ፣ ከቤሰተብም ይለያሉ፡፡

የአሜሪካ መንግሥት ሕፃናትን ከወላጅ ለይቶ በማቆያ የሚያስቀምጠው ከማዕከላዊ አሜሪካ የሚሰደዱ ዜጎችን ተስፋ ለማስቆረጥ ነው፡፡ በአሜሪካና ሜክሲኮ ድንበር አሜሪካ በስደተኞች ላይ የምትፈጽመው ያልተገባ አያያዝም ከሰዋዊነት የመነጨ እንዳልሆነ ፕሮፌሰር ኖዋክ ይገልጻሉ፡፡

በአሜሪካ በስደት ከሚገኙት ሕፃናት የተወሰኑት ወታደር የነበሩ ቢሆንም፣ ወታደርነትን ፈልገውት የገቡበት ባለመሆኑ ሕፃናቱ እንደ ተጠቂ እንጂ እንደ አጥቂ ሊቆጠሩ እንደማይገባም አክለዋል፡፡

ወታደር የነበሩ ሕፃናት በመልሶ ማገገሚያ ማዕከላት ገብተውም፣ ሥልጠና ካገኙ በኋላ ወደ ማኅበረሰቡ መቀላቀል እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...