Friday, May 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊዓለም አቀፍ ትብብር የሚሻው የመድኃኒት አቅርቦት

ዓለም አቀፍ ትብብር የሚሻው የመድኃኒት አቅርቦት

ቀን:

ኢትዮጵያ ውስጥ በድምሩ 4,500 ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች ይገኛሉ፡፡ የተጠቀሱት የጤና ተቋማት የሚገኙትም ለማኅበረሰቡ አማካይ በሆኑ አካባቢዎች ነው፡፡ ይሁን እንጂ በመድኃኒቶች አቅርቦት ላይ ሰፊ ክፍተት ይታያል፡፡ ይህንን ክፍተት ለመሙላት የመፍትሔ አቅጣጫዎች ተቀይሰዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሙኒር ካሳ (ዶ/ር) ‹‹መንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ለዘላቂ የጤና ሥርዓት›› በሚል መሪ ቃል በስዊድንና ኢትዮጵያ የጤና ሥርዓት ላይ ትኩረት አድርጎ በተዘጋጀ ጉባዔ እንደገለጹት፣ የውጭ አገር የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት  ሊያደርጉ የሚያስችላቸውን ሁኔታ ማመቻቸት ችግሩን ለመፍታት ያስችላል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍም ሁለት የስዊድን ኩባንያዎች የደም ግፊት መድኃኒቶችን በመጠነኛ ዋጋ ከዓምና ጀምሮ እያቀረቡ ሲሆን፣ አንድ የጀርመን ኩባንያ ደግሞ አልትራሳውንድ ለማምረት የሚያስችል ፋብሪካ ለማቋቋም በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡

- Advertisement -

ስዊድን ጥራታቸውን የጠበቁ ልዩ ልዩ ዓይነት መድኃኒቶችንና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችን በማምረት ረገድ በዓለም ውስጥ ከፍተኛ ዝና እንዳተረፈች ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ከአገሪቱ የጤና ዘርፍና ከልዩ ልዩ ኩባንያዎች የተውጣጣ ልዑካን ቡድን ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር የተሞክሮ ልውውጥ አድርጓል፡፡

በስዊድን የጤናና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር በሚሲዝ ሊና ሀሊንግሪን የተመራው ልዑካን ቡድን፣ ከጤና ሚኒስትር አሚር አማን (ዶ/ር) ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን፣ በዚህም አጋጣሚ በኢትዮጵያ ስላለው አማራጭ ኢንቨስትመንት ዙሪያ ገለጻ እንደተረገ ዶ/ር ሙኒር ተናግረዋል፡፡

እንደ ኃላፊው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የጤና ትኩረት በጤና ጣቢያ ላይ ያለመ ክብካቤ ሲሆን፣ የስዊድን ትኩረት ደግሞ በሦስተኛ ደረጃ ወይም ሆስፒታል ላይ ያለመ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ በስዊድን እየተመረቱ የሚወጡ መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ዋጋ በጣም ውድ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን ድረስ የመድኃኒት ግዥ ሲከናወን የቆየው በጨረታ ነው፡፡ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ መሆኑና በዝቅተኛ ዋጋ የሚቀርበው መድኃኒት ጥራትና ፈዋሽነቱ አጠያያቂ ሊሆን እንደሚችልም አመልክተዋል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ስዊድን ሠራሽ መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶች ዋጋቸው ውድ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚው የሚደርስበት እንዲሁም በግሉ  ዘርፍና በመንግሥት አጋርነት መርህ መሠረት የስዊድን የሕክምና ባለሙያዎች በተለያዩ የመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ ተመድበው በሚያገለግሉበት ላይ ያተኮረ ውይይት መደረጉም ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ የኅብረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኤባ አባተ (ዶ/ር) በዓለም ጠንካራ የተባለ የጤና ሥርዓት ከዘረጉ አገሮች መካከል አንዷ ከሆነችው ስዊድን የምንማራቸው ነገሮች አሉ ብለዋል፡፡

በአገሪቱ በርካታ የጤና ተቋማት ቢቋቋሙም የማኅበረሰቡ ቁጥርና ፍላጎት እየጨመረ ሄዷል፡፡ በፊት የነበሩ የበሽታ ዓይነቶችም አሁን ተለውጠዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ተላላፊ የነበሩ በሽታዎች ላይ ብቻ ማዕከል ተደርጎ ሲሠራ የቆየ ሲሆን፣ አሁን ላይ ግን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ቀድሞ ለመከላከልና በሽታው ሲከሰት ለማከም የሚያስችሉ የጤና ተቋማት መገንባት ግድ የሚልበት ደረጃ ላይ መደረሱን ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር ሚስተር ቶርበጀርን ፒተርሰን የስዊድን ልዑካን ቡድን አባላት በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸው፣ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ያላቸውን ፍላጎት እንዳነሳሳው አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...