በቻይና ያሉ የተለያዩ አገሮች ተማሪዎች በየዓመቱ በየዩኒቨርሲቲያቸው የባህል ቀን ያከብራሉ፡፡ ከነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ በሆነው ሀርቢን ኢንጂነሪንግ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች ባለፈው ሳምንት የባህል ቀናቸውን አክብረዋል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ የአገራቸውን ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦችን የሚያስተዋውቁበት ጎጆ አዘጋጅተው በባህላዊ ምግብ፣ በዘፈንና በአለባበስ ሲያስተዋውቁ ውለዋል፡፡ በዚህ ፌስቲቫል ላይ ከ5000 የሚበልጡ እንግዶች መጎብኘታቸውን የቱሪዝምና ሆቴል አስተዳደር ተማሪዋ ዓለምነሽ ፍቅረሥላሴ ወልዴ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ፎቶዎቹ ያከባበሩን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡