የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት የጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተ ወልድ ታሪክ በአማርኛና በእንግሊዝኛ በተዘጋጁ ሁለት ዲቪዲዎች ቀርበዋል፡፡ በተወዳጅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን አማካይነት ለገበያ የቀረበው ዲቪዲ፣ የጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉን ያልተነገሩ ታሪኮች፣ አብረዋቸው ከሠሩ ሰዎችና ከቅርብ ቤተሰቦቻቸው ጋር የተደረገውን ቆይታ ማካተቱን ዋና አዘጋጁና አሳታሚው እዝራ እጅጉ ገልጿል፡፡ አንዱ ዲቪዲ በ150 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
***