የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ400 ሚሊዮን ብር ወጪ የገዛቸው 100 የከተማ አውቶቡሶችን፣ ለአንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት መስከረም 21 ቀን 2012 ዓ.ም. አስረክቧል፡፡ ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚገልጸው፣ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) የአውቶቡሶቹን ቁልፍ ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት፣ በቀጣይነትም የከተማ አስተዳደሩ 3000 ዘመናዊ አውቶቡሶችን ከውጪ በማስገባት ያለውን የትራንስፖርት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ይሠራል፡፡ በአውቶቡስ ርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይም ከንቲባው ለ500 የአዲስ አበባ ነዋሪ አካል ጉዳተኞች የሚሆን የአንድ ዓመት የነፃ የአውቶቡስ መጓጓዣ የነፃ ቲኬት ስጦታ በማኅበራቸው በኩል አበርክተዋል፡፡ ፎቶዎቹ የሥርዓተ ርክክቡን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡