በአፋን ኦሮሞ የተሠሩ ኪነጥበባዊ ሥራዎችንና ባለሙያዎችን የሚያበረታታው ኦዳ ሽልማት፣ ጥቅምት 7 ቀን 2012 ዓ.ም. በ18 ኪነጥበባዊ ዘርፎች እንደሚሸልም በሻቱ ቶለማርያም መልቲ ሚዲያ አስታውቋል፡፡ የተቋሙ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ በሻቱ ቶለማርያም እንደገለጹት፣ ከኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የሚዘጋጀው ሦስተኛው የኦዳ ሽልማት፤ በአፋን ኦሮሞ የሚሠሩ የኪነጥበብ ሥራዎችን በማበረታታት ለአገራዊ ኪነጥበብ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽዖ ያደርጋል፡፡
በተመስገን ተጋፋው