ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) 74ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባለፈው ሳምንት የተናገሩት፡፡ ፕሬዚዳንቷ በአማርኛ ባደረጉትና የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች በያዘው ዲስኩራቸው ስለ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ሳያነሱ አላለፉም፡፡ የዓባይ ወንዝን የምንጠቀመው 60 ሚሊዮን የሚሆነው ሕዝብ ቢያንስ እራት በመብራት ለመብላት እንዲችል ነው ሲሉም አስምረውበታል፡፡ የዓባይ ወንዝ ለተፋሰሱ አገሮች የጋራ ሀብት እንጂ የጥርጣሬና የውድድር ምንጭ ሊሆን አይገባም ሲሉም አሳስበዋል፡፡