Wednesday, June 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሰዎች ሲገደሉ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሰዎች ሲገደሉ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

ቀን:

በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጭልጋ ወረዳና በአካባቢው ከመስከረም 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በተከሰተ ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ሲገደሉ፣ በንብረት ላይ ውድመት መድረሱ ታወቀ፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው በአማራና በቅማንት ማኅበረሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሰዎች መሞታቸውና ንብረት መውደሙ ይታወሳል፡፡

የአካባቢው ምንጮች ለሪፖርተር እንደተናገሩት ከጎንደር ወደ መተማ የሚወስደውን መንገድ በመቆጣጠር፣ በተሽከርካሪዎችና በመንገደኞች ላይ ጥቃት ተፈጽሟል፡፡ በጥቃቱም ሰዎች መገደላቸውንና መታፈናቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ጥቃቱን አስመልክቶ ለአማራ መገናኛ ብዙኃን መግለጫ የሰጡት የአማራ ክልል የሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጭልጋ አካባቢ በተፈጠረ ችግር የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና ንብረት መውደሙን አረጋግጠዋል፡፡

መንግሥት የማንነትና የአስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት እየሠራ ባለበት ወቅት ችግሩ ማጋጠሙን ተናግረው፣ ግጭቱም ዕገዛ በሚደረግላቸው ሰላም በማይወዱ አካላትና በፀጥታ ኃይሉ መካከል የተፈጠረ እንጂ በሕዝብ መካከል አለመሆኑንም አስረድተዋል፡፡

‹‹የአማራን ክልል የጦርነት አውድማ ለማድረግ የሚጥሩ አካላት አይሳካላቸውም፣ ይህን ለማድረግ የሚመጡ ካሉም ለመከላከል አቅሙ ሆነ ብቃቱም አለን፤›› ብለዋል፡፡

ምንጮች እንደሚሉት በአካባቢው የቅማንት ኮሚቴ አባላትና የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ የቅማንት ከሚቴ አባላት ተገድለዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የአማራ ተወላጆችም በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸውን ምንጮች አክለዋል፡፡

በተኩስ ልውውጡ ወቅትም ከቀላል መሣሪያዎች ጀምሮ የመካከለኛና የከባድ መሣሪያዎች ድምፅ ይሰማ እንደነበር ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት አንፃራዊ ሰላም መስፈኑ ቢገለጽም፣ በአካባቢው ድንገተኛ ጥቃት የሚፈጽሙ ኃይሎች እንዳሉ ተሰምቷል፡፡

የቅማንት የማንነት ጥያቄ በክልሉ ምክር ቤት ምላሽ ማግኘቱን፣ የአስተዳደር ጥያቄውንም ለመመለስ በክልሉ መንግሥት እየተሠራ መሆኑን በመጠቆም፣ ችግር እያደረሱ ያሉ አካላትንም ከማኅበረሰቡ በመነጠል የማያዳግም ዕርምጃ እንደሚወሰድ አቶ አገኘሁ አስታውቀዋል፡፡ ችግሩ እንዲፈታ የፌዴራል መንግሥት ድጋፍ እያደረገ እንደሆነም አክለዋል፡፡

አቶ አገኘሁ እንዳሉት ከሰኞ መስከረም 19 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል፡፡ ‹‹በአካባቢውና በፀጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት ሊያደርስ የነበረው የጥፋት ኃይል አልተሳካለትም፤›› ብለው፣ ችግሩን ለመቅረፍ የክልሉ ልዩ ኃይልና የመከላከያ ሠራዊት በጋራ እየሠሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

‹‹የጥፋት ኃይሉ ዋና ዓላማ የመተማ – ጎንደር መንገድን ዘግቶ ባለሀብቶች ምርታቸውን በወቅቱ እንዳይሰበስቡና ለገበያ እንዳያደርሱ በማድረግ በኢኮኖሚ ማዳከም ነው፡፡ በዚህ ደግሞ አንደራደርም፡፡ በአጭር ጊዜም መንገዱ ክፍት ይሆናል፤›› ብለዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአካባቢው እየተፈጸመ ያለው ድርጊት አጀንዳው የአማራን ሕዝብ ማዳከም ነው ያሉት አቶ አገኘሁ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብም ይህንን አውቆ አጀንዳውን ውድቅ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

‹‹በኢትዮጵያ እንደ አማራ ክልል የማንነት ጥያቄ የተመለሰበት ክልል የለም፤›› ያሉት አቶ አገኘሁ፣ የቅማንት የማንነት ጥያቄ በክልሉ ምክር ቤት ምላሽ ማግኘቱንና የአስተዳደር ጥያቄውንም ለመመለስ በክልሉ መንግሥት እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ችግር እያደረሱ ያሉ አካላት ከማኅበረሰቡ በመነጠል የማያዳግም ዕርምጃ እንደሚወሰድ አቶ አገኘሁ አስታውቀዋል፡፡ ችግሩ እንዲፈታ የፌዴራል መንግሥት ድጋፍ እያደረገ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

አጀንዳ ለመስጠት ጥረት የሚያደርጉ አካላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንና በቅርቡም ለመንግሥትና ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረጉ፣ ወጣቶችም ከስሜታዊነት በመውጣት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

‹‹ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት የክልሉ መንግሥት ጥረት እያደረገ ነው፤›› ሲሉም አቶ አገኘሁ አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...