Sunday, June 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የአሜሪካ ሞሮቶላ ኩባንያ ለኤሌክትሪክ አገልግሎት የሬዲዮ መገናኛ ቴክኖሎጂ አቀረበ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በሔለን ተስፋዬ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሞቶሮላ ሶሉሽንስ ከተሰኘው የአሜሪካ ኩባንያ ጋር በመተባበር ሠራተኞቹ መረጃ የሚለዋወጡበትና የደኅንነት ሥጋቶች የሚቀረፉበት እንዲሁም ለደንበኞቹም የተቀላጠፈ አገልግሎት ለማቅረብ ያስችላል ያለውን የሞባይል ሬዲዮ ግንኙነት ቴክኖሎጂ ግዥና የግንኙነት መስመር የመጀመርያ ምዕራፍ ተከላ ሥራ ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡  

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስትሮ 25 የተሰኘውን የሞቶሮላ ኩባንያ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም ዘመናዊ የምድር ለምድር ገመድ አልባ የሬዲዮ ግንኙነት በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ለሚገኙ ከተሞች አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የ1.8 ሚሊዮን ዶላር ግዥ ፈጽሞ፣ የመጀመርያው ምዕራፍ የግንባታና የገጠማ ሥራ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡

ፕሮጀክቱ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ የመጀመርያ ምዕራፍ ተግባራዊ የተደረገው በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች እንደሆነ ያስታወቁት፣ የፕሮጀክቱ የአውቶሜሽንና የኢነርጂ ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደመቀ ሮቢ ናቸው፡፡ የሬዲዮ ግንኙነት ፕሮጀክቱ ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ በአገሪቱ ባሉ የክልል ከተሞችና በተመረጡ 13 አካባቢዎች ገጠማው እንደሚከናወን አቶ ደመቀ አብራርተዋል፡፡

የፕሮጀክቱን ዲጂታል የሬዲዮ ግንኙነት በተቋሙ ለመተግበር የሞቶሮላ ሶሉሽንስ ምርት የሆነው አስትሮ ሬዲዮ ግንኙነት ሲስተም እየሠራ ነው ያሉት አቶ ደመቀ፣ አሠራሩን ለማሻሻልም በእንጦጦ ተራራና ገርጂ ከሚገኘው የኃይል ጭነት መቆጣጠሪያ ማዕከል (ኤልደሲ) ሁለት ሪፒተሮችን ተክሎ የሬዲዮ የግንኙነት አቅሙን ለሚፈልገው አካባቢ እየደረሰ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የሬዲዮ ግንኙነት ሲስተሙ ፕሮግራም የተደረገው ስድስት የተለያዩ ቡድኖች እንዲኖሩት ሲሆን፣ እነዚህ ቡድኖች በሁለት የሬዲዮ ግንኙነት ቻይናሎች በጋራ/እኩል እንዲጠቀሙ ያስችላልም ተብሏል፡፡

ኩባንያዎቹ ያደረጉት የግዥ ስምምነት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ በአቶ ሽፈራው ተሊላና በሞቶሮላ ሶሉሽንስ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ኃላፊ ሚስተር ዩቫል ሃናን መካከል ተፈርሟል፡፡ አቶ ሽፈራው እንደተናገሩት፣ አስቸኳይ ጥገና ተልዕኮን ቀልጣፋ ለማድረግ ከተቋቋሙ ቅርንጫፎች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሳለጥ፣ በግንኙነት ክፍተት ሊፈጠሩ የሚችሉት የሰው ሕይወትና የንብረት መጥፋትን ለመቀነስ ትልቅ ሚና እንዳለው አብራርተዋል፡፡

መረጃዎችን ለመቀበልና መልዕክት ለማስተላለፍ፣ የሠራተኞችና የደንበኞችን ደኅንነት ለመጠበቅና ሊደርስ ከሚችሉ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል ጠቀሜታው ላቅ ያለ መሆኑን አክለዋል፡፡

የሬዲዮ ኮሙዩኒኬሽን ፕሮጀክቱ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ 300 የሚሆኑ በእጅ የሚያዙ፣ 200 መኪና ላይ የሚገጠሙ እንዲሁም በጥሪ ማዕከል ለአስቸኳይ ጥገና ማዕከላት የሚገጠሙ 100 ዲጂታል ሬዲዮዎች ጥቅም ላይ እንደዋሉ አቶ ደመቀ ገልጸዋል፡፡

የኃይል መቆራረጥን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመቅረፍ ለሬዲዮ መገናኛና ማሠራጫ ጣቢያው በፀሐይ ኃይል የሚሠራ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ የተገነባለት ሲሆን፣ በአጠቃ     ቀሙ ዙሪያም የሬዲዮ ፕሮግራሚንግና የተከላ ሥራዎችን የተመለከቱ ሥልጠናዎች ለተቋሙ ሠራተኞች መሰጠቱን አቶ ደመቀ ተናግረዋል፡፡ በሥራ ላይ የዋለው ‹‹አስትሮ 25›› የምድር ለምድር ገመድ አልባ ሬዲዮ ግንኙነት (Land Mobile Radio) በሠራተኞች መካከል የነበረውን የመገናኛ ግንኑነት በማሻሻል በርካታ የግንኙነት ፍላጎቶችን ማሟላት እንዳስቻለ አብራርተዋል፡፡

 የፕሮጀክቱ ሙሉ ወጪ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደተሸፈነም ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በእጅ የሚያዘው አምስት ቮልት ኃይል ሲኖረው በመኪና ላይ የሚገጠመው 25 ቮልት ያለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የነበረው የሬዲዮ ግንኙነት ለረዥም ጊዜ ተቋርጦ እንደነበርና ኋላቀር መሆኑን የገለጹት አቶ ደመቀ፣ አዲሱ ቴከኖሎጂ ግነኙነቱን በማሻሻል ትልቅ የአገልግሎት ለውጥ እንደሚያመጣ ተናግረዋል፡፡

ሞቶሮላ ሶሉሽንስ የአንድ ለአንድና የአንድ ለብዙ ግንኙነትን ማስኬድ የሚያስችል የሬዲዮ መገናኛ ሥርዓት በመገንባት ልምድ አካብቷል ያሉት ሚስተር ሃናን፣ የሬዲዮ መገናኛ ፕሮጀክት ስምምነቱ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና በሞቶሮላ ሶሉሽንስ መካከል የተፈረመው እ.ኤ.አ. 2017 እንደነበርና በእ.ኤ.አ. 2018 ስምምነቱ ወደ ተግባር እንደተሸጋገረ አቶ ደመቀ አስታውሰዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች