በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የመስቀል ደመራ በዓል ተከብሮ ውሏል፡፡ በየዓመቱ መስከረም 17 ቀን የሚከበረው መስቀል፣ እንደየአካባቢው ባህልና ወግ ከዕለቱ ቀድሞ በሚከናወኑ ሥነ ሥርዓቶች ይታጀባል፡፡ ከመስከረም 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በተከበረው የጎፋ መስቀል ላይ የምርቃት፣ የዕርቅ፣ የእርድና የደመራ ሥርዓቶች ከተከወኑት ይገኙበታል፡፡ ፎቶዎቹ በከፊል የበዓሉን አከባበር የሚያሳይ ናቸው፡፡