Monday, May 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊስለሰላም የመከረ ጉባዔ

ስለሰላም የመከረ ጉባዔ

ቀን:

ኢትዮጵያ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የተለያዩ አገሮች ስደተኞችን ተቀብላ አያስተናገደች ነው፡፡ አንዳንድ የሶሪያ ስደተኞችም አዲስ አበባ ውስጥ ዕርዳታ ሲጠይቁና ሲለምኑ ይስተዋላሉ፡፡ ስደተኞቹ ይህ ሁሉ ችግር ሊደርስባቸው የቻለው በየአገሮቻቸው ሰላምና መረጋጋት ባለመኖሩ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገሮች ኬንያ፣ ጂቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳንና ኤርትራ ጋር ሰላም መሥርታለች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ሰላም እንዲሰፍን የአንበሳውን ድርሻ ወስደዋል፡፡ ሰላምም ሆነ ጦርነት በሌለበት ሁኔታ ከ20 ዓመታት በላይ የቆየውን ውጥረትም አርግበውታል፡፡ ሆኖም ግን የኢትዮጵያን ሰላም የሚያደፈርሱ የውስጥ ጉዳዮች አልታጡም፡፡

ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዚዳንትና የዕርቅና የሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ ናቸው፡፡ እንደ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ አነጋገር፣ ከጎረቤት አገሮች ጋር ሰላም ሲመሠረት በኢትዮጵያውያን መካከል ግን ሰላም የለም፡፡ የሚፈለገው ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ እያንዳንዱ ሰው ታሪኩን፣ ባህሉንና ሃይማኖቱን መሠረት ያደረገ ማኅበራዊ ግንኙነቱንና በሰላም አብሮ የመኖር እንቅስቃሴውን ማጠናከር ይገባዋል፡፡

- Advertisement -

አዲስ አበባ እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ጉባዔ ማዕከል ‹‹ዘ ኮንትሪቢዩሽን ኦፍ ዘ ካቶሊክ ቸርች ኢን አድሬሲንግ ኮውዝ ኦፍ ኮንፍሊክት ኢን ቪው ኦፍ ሪስቶሪንግ ፒስፉል ኮ ኤግዚስታንስ ኢን ኢትዮጵያ›› [የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ የግጭት መንስዔን መፍታትና በሰላም አብሮ መኖርን ለማዳበር የሚኖራት አስተዋጽኦ] በሚል መሪ ሐሳብ ለሁለት ቀናት በተካሄደው ጉባዔ ላይ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ በዓይነቱ የመጀመርያ የሆነው የዕርቅና የሰላም ኮሚሽን ሰላምና መረጋጋትን ለመፍጠር ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት መማክርት ጉባዔና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር አብሮ እየሠራ ነው፡፡

2012 ዓ.ም. ከመግባቱ በፊት መላው የአገሪቱ ሕዝብ ለሰላምና በሰላም አብሮ ለመኖር ፀሎትና ምህላ እንዲያደርግ መደረጉንና ይህ ዓይነቱም ሁኔታ ወደፊት የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሴቶች እንዲመራ መደረጉ፣ ቦርዱም የተለያዩ ፓርቲዎችን በአንድ ላይ ማሰባሰቡ፣ ፍርድ ቤትም ከመንግሥት ጣልቃገብነት እንዲፀዳ መደረጉ ለዴሞክራሲ ግንባታ ምቹ መደላደልን እንደሚፈጥር አመልክተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግና አስተዳደር ትምህርት ኮሌጅ ዲን ሰለሞን ንጉሤ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ‹‹ሂስቶሪካል ፐርስፔክቲቭ ኦፍ ኢትዮጵያ ዊዝ ሪጋርደ ቱ ፒስፉል ኮኤክዚስታንስ ሪጋርድለስ ኦፍ ኢቲኒክ፣ ሪሊጂየስ ኤንድ ካልቸራል ዳይቨርሲቲስ›› በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ በልማት ፕሮግራሞች ላይ ሰላምና የሰላም ተነሳሽነት ቀዳሚ አጀንዳ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ በግንቦት 2012 ዓ.ም. ሊካሄድ የታቀደው ብሔራዊ ምርጫ ፈታኝ የሆኑ ተግዳሮቶች ሊገጥሙት እንደሚችሉ፣ ይህን ችግር ለመቅረፍ ብሔራዊ የዕርቅና ሰላም ኮሚሽን፣ ከሃይማኖት ተቋማትና ከአገር ሽማግሌዎች ጋር ሆኖ ለሰላምና መረጋጋት አብሮ ሊሠራ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የሃይማኖት ተቋማት ለሰላም ግንባታና ሕዝቡንም ወደ አንድነት ለማምጣት ከፍ ያለ ሚና በመጫወት እንደሚታወቁ፣ በተለይ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ድምፅ አልባ ለሆኑ ወገኖች ድምፃቸው እንዲሰማ በማድረግ ረገድ የበኩሏን አስተዋጽኦ እንዳደረገች፣ ይህም ሊሆን የቻለው ገለልተኛና የፖለቲካ ፍላጎት ካላቸው ኃይሎች ጋር ባለመወገኗ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ጠቅላይ ፀሐፊ አባ ተሾመ ፍቅሬ (ዶ/ር) በአገሪቱ የሚገኙ ልዩ ልዩ ሃይማኖት ተቋማት፣ ማኅበረሰቦችና ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች ሁሉ አንድ ላይ ሆነው በአገሪቱ የሰላም ግንባታ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚቻልበትን አካሄድ በመቀየስ ረገድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ሚና ልትጫወት እንደምትችል አክለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊና ልማት ኮሚሽን ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለንጹህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦትና ለመሳሰሉት በርካታ የልማት ሥራዎች ማከናወኛ በዓመት 2.2 ቢሊዮን ብር እንደሚያወጣ ጠቅላይ ፀሐፊው ተናግረዋል፡፡

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለኅብረተሰቡ ሃዋሪያዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች እያበረከተች ሲሆን፣ ይህንንም የምታከናውነው ከዓለም አቀፍ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ጋር በመተባበር መሆኑን ከጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

አገልግሎቷንም ከወቅታዊ የአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣምና ኅብረተሰቡንም ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ በመላው አገሪቱ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ ማኅበራዊ የልማት ኮሚሽን ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችና ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የመጡ አጋር ድርጅቶች በጋራ ተሰባስበው ተወያይተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...