Wednesday, June 7, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ተጠባባቂ ዋና ጸሐፊ ተሰየመለት

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና ጸሐፊ በመሆን እያገለገሉ የነበሩት አቶ እንዳልካቸው ስሜ ኃላፊነታቸውን በመልቀቃቸው፣ የንግድ ምክር ቤቱ ቦርድ አቶ ውቤ መንግሥቱን በተጠባባቂ ዋና ጸሐፊነት መሰየሙ ተገለጸ፡፡

ያልተጠበቀ ነው የተባለው የዋና ጸሐፊው የሥራ መልቀቂያ ጥያቄን አዎንታዊ መልስ ካገኘ በኋላ፣ የንግድ ምክር ቤቱ ቦርድ በአቶ እንዳልካቸው ምትክ አቶ ውቤን በተጠባባቂ ዋና ጸሐፊነት ሰይሟል፡፡ ተሰናባቹ ዋና ጸሐፊም ለአዲሱ ዋና ጸሐፊ ኃላፊነታቸውን ያስረክባሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡

አቶ እንዳልካቸው ከዋና ጸሐፊነታቸው ለመልቀቅ የፈለጉትበት ምክንያት በዝርዝር ባይታወቅም፣ ከአቶ እንዳልካቸው ያገነኘው መረጃ ኃላፊነታቸውን በፈቃደኝነት መልቀቅ መፈለጋቸውን ብቻ የሚጠቁም ነው፡፡

አቶ ውቤ የተጠባባቂ ዋና ጸሐፊነቱን ኃላፊነት እንዲረከቡ ውሳኔ ከመተላለፉ በፊት በምክትል ዋና ጸሐፊነት ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን፣ በዚሁ ንግድ ምክር ቤት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ከአሥር ዓመታት በላይ ያገለገሉ ናቸው፡፡ አቶ እንዳልካቸው በንግድ ምክር ቤቱ ውስጥ አምስት ዓመታት በምክትል ዋና ጸሐፊነት፣ ሦስት ዓመታት ደግሞ በዋና ጸሐፊነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንትና ቦርድ አባላትን ለመምረጥ ጠቅላላ ጉባዔ ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በንግድ ምክር ቤቱ ሕገ ደንብ መሠረት በየሁለት ዓመቱ በሚካሄድ ምርጫ አመራሮች የሚመረጡ ሲሆን፣ ይህንን ምርጫን የሚያካትተውን ጠቅላላ ጉባዔ በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ውስጥ ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከንግድ ምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተውም ለጠቅላላ ጉባዔውና ለምርጫው በጽሕፈት ቤቱ በኩል ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ንግድ ምክር ቤቱን ለመምራት ሲደረጉ በነበሩ ምርጫዎች ከምርጫው ዋዜማ ጀምሮ የተለያዩ ውዝግቦችን ሲያስተናግድ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ ዘንድሮ ግን ወደ ኃላፊነት ለመምጣት ሲካሄዱ የነበሩ ውዝግቦች ባለመታየታቸው የተለየ አድርጎታል፡፡

በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ እንደዚህ ቀደሙ አወዛጋቢ ክስተቶች ያልተሰሙበት ሲሆን፣ ወደ ኃላፊነት ለመምጣት እወዳደራለሁ ብሎ ራሱን ያቀረበ እስካሁን ብቅ ያለማለቱም በተለየ የሚታይ ሆኗል፡፡ አሁን የንግድ ምክር ቤቱን በፕሬዚዳንትነት የሚመሩት መላኩ እዘዘው (ኢንጂነር)፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ አሰፋ ገብረ ሥላሴና የቦርድ አባልነቱ ኃላፊነታቸውን የተረከቡት ጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደነበር ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች