Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበሕገወጥ መንገድ ድንበር የሚሻገሩት ምግብና መድኃኒቶች

በሕገወጥ መንገድ ድንበር የሚሻገሩት ምግብና መድኃኒቶች

ቀን:

በተለያዩ አጋጣሚዎች በአንድ አፍታ በርካቶች ይረግፋሉ፡፡ ጦርነት፣ አደጋ፣ በሽታና ሌሎችም በየሰዓቱ ለሚመዘገቡ የሞት ክስተቶች ምክንያት ይሆናሉ፡፡ አንዳንዴም ሰዎችን ከሞት ለመታደግ የሚደረገው የሕይወት አድን ሩጫም ባልተጠበቀ ሁኔታ ሰዎችን ለሞት ሲዳርግ ይታያል፡፡ በዚህ ረገድ የሕክምና ስህተት አልፎ አልፎም የሐኪሞች ብቃት ማነስ ጉዳይን ማንሳት ይቻላል፡፡ ሰዎች በቀላል ሕክምና መዳን ሲችሉ፣ ሳይጠበቅ ለሞት የሚዳረጉበት ሁኔታም አለ፡፡

ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶችን መደርደር ይቻል ይሆናል፡፡ ሕሙማን የሚወስዷቸው መድኃኒቶችስ ፈዋሽነታቸው እስከ ምን ድረስ ነው? ከውጭ በገፍ የሚገቡ የታሸጉ ምግቦች ጤንነትስ? የሚለው ጉዳይም በተወሰነ መንገድ አጠያያቂ ነው፡፡ ምክንያቱም ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጡና ከየት እንደተገዙ የማይታወቁ መድኃኒቶች እንዲሁም ምግብና ምግብ ነክ ምርቶች በሕገወጥ መንገድ በመውጫና መግቢያ ኬላዎች በገፍ ይገባሉ፡፡ በኮንትሮባንድ የሚገቡትን ምርቶች ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረትም የበርካቶችን ድጋፍ የሚሻ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ የመጣው የፍተሻና የቁጥጥር ሥርዓትም ሊያስቆመው ያልቻለ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡  

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ ደኅንነታቸውና ጥራታቸውን ያልጠበቁ 4,763.62 ቶን የተለያዩ ዓይነት የምግብ ምርቶችን፣ እንዲሁም 31.6 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ መድኃኒቶችን፣ የሕክምና መሣሪያዎችንና የመዋቢያ ምርቶችን በመግቢያና መውጫ ኬላዎች እንዲሁም በኦዲቲንግ ኢንስፔክሽን ቁጥጥር ወቅት አግኝቶ አስወግዷል፡፡

- Advertisement -

የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሳምሶን አብርሃም እንደገለጹት፣ በጉዞ ወቅት የተበላሹና አምራች ድርጅቶቻቸው የማይታወቁ ሩዝ፣ የአኩሪ አተር ዘይት እንዲሁም የተበላሸ ስኳር የጥራትና ደኅንነት መጓደል ያለባቸውን የምግብ ምርቶች ኬላዎች ላይ በመያዝ፣ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ በማገድ እንዲሁም ገበያ ላይ የተሠራጩትን የፍተሻና የማጣራት ሥራ በመሥራት እንዲወገዱ ተደርጓል፡፡  

ከጅማ ከተማ ጤና ጽሕፈት ቤት ተቆጣጣሪዎችና ከጅማ ፖሊስ ጋር በመሆን በተደረገው ዘመቻም 2.15 ቶን የማርና ቅቤ ምርት ላይ ፍተሻ ምርመራ ተካሂዶ ውጤታቸውም ለሚመለከተው አካል ተልኳል፡፡ በመቀሌ በ45 ማር የሚሸጡ ተቋማት ላይ ቅኝት የተደረገ ሲሆን፣ በቅኝቱም በ24 ተቋማት ላይ የጥራት ችግር ተገኝቶባቸዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አራት ተቋማት የማር ምርትን ከስኳር ጋር ሲቀላቅሉ በመገኘታቸው ከእነማቀነባበሪያ መጋዘናቸው እንዲታሸጉ ተደርጓል፡፡ 1,183 ኪሎ ማር እንዲወገድ በማድረግም ጥቅም ላይ ቢውል ሊያደርስ የሚችለውን የጤና እክል አስቀድሞ መከላከል እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡

እንደ ኃላፊው፣ የምግብ ገበያ ቅኝት በማካሄድ ጁስ፣ ቪምቶ፣ የምግብ ዘይት፣ ሞሪንጋ፣ ብስኩት፣ ማር፣ ቸኮሌት፣ አቼቶ፣ ቴምር፣ የለውዝ ቅቤ፣ ማስቲካ፣ ለስላሳዎች፣ የሕፃናት ምግብ፣ የጃር ውኃና (20 ሊትር ውኃ የሚይዝ ላስቲክ) ወተት በአጠቃላይ በ101 የምግብ ዓይነቶች ላይ የተለያዩ ችግሮች ታይተዋል፡፡

የመጠቀሚያ ጊዜው ማብቃት፣ ምርቱ ላይ የብልሽት ምልክት ማሳየት ለምሳሌ ማሸጊያው ማበጥ፣ ምንም ዓይነት ገላጭ ጽሑፍ የሌለው መሆን፣ የተመረተበትና የመጠቀሚያ ጊዜ የሌለው መሆን፣ የመያዣ ዕቃው የተበላሸ (መጨራመት) የመጠቀሚያ ማብቂያ ጊዜው ግልጽ ያለመሆን፣ ምርቱ ላይ የመበላሸት ምልክት ማሳየት፣ በእንግሊዝኛ ብራንድ ስሙ አለመጻፍ፣ ምርቱ የተጻፈበት ቋንቋ አለመታወቅ የመሳሰሉ ችግሮች የታየባቸው እነዚህ ምርቶች እንዲታገዱ ተደርጓል፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰመራ ሎጊያ፣ አሳይታ፣ አዋሽ፣ ሚሌ በመኮኒ፣ አላማጣ፣ ሁመራ፣ ዓድ ሐቂ፣ ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ ቶጎ ጫሌ፣ ሞያሌ፣ ሻሸመኔ፣ ዝዋይ፣ አርባ ምንጭን ጨምሮ በሌሎች 73 ቦታዎች ላይ የሕገወጥ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሙያዎች መሠራታቸውን ጠቁመው፣ በተጨማሪም በዲላ፣ በኮንሶ፣ በወላይታ ሶዶ፣ በሆሳዕና እና በአርባ ምንጭ በሚገኙ 17 መድኃኒት መደብሮች ላ ከዚህ በፊት በተደረገው ቅኝት መሠረት ከመንግሥት ጤና ተቋም የወጣ የወባ መድኃኒት እንዲሁም ያልተመዘገቡ መድኃኒቶች ተገኝተው ዕርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡

እንደ አቶ ሳምሶን፣ በ32 የምግብ አምራቾች ላይ የተለያዩ ዕርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ ከተወሰዱትም ዕረምጃዎች መካከል ጊዜያዊ ዕገዳ፣ ቀላልና ከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ፣ የብቃት ማረጋገጫ ስረዛ ይገኙባቸዋል፡፡ በ12 የምግብ አስመጪና አከፋፋይ ድርቶች ላይም የብቃት ማረጋገጫ ስረዛ፣ እስከ ሦስት ወራት የሚዘልቅ ዕገዳና የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ዕርምጃዎች ተወስዶባቸዋል፡፡                                                                                                       

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...