Sunday, June 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የውጭ ባለሀብቶች ትርፋቸውን በመውሰድና መልሶ በመጠቀም መሀል ይዋልላሉ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የውጭ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ በመጡ ማግ ስለገጠሟቸው በርካታ ንካዎች ሲናገሩ ደመጣሉ። በአን በርካቶቹ የውጭ ባለሀብቶች ከአገር በቀሎቹ የተሻለና ለእነሱ ያደላ የመንግሥት ድጋፍ ሲቀርብላቸው እንደቆየ በመግለጽ በአገር ውስጦቹ ይተቻሉ

ይሁን እንጂ ሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ መሠረታዊ ችግር ነሳሉ። ለዓመታት የሚንከባለል የውጭ ምንዛሪ ችግር። በሥራ እንቅስቃሴያቸው ትርፋማ ሲሆኑ፣ ትርፋቸውን ወደ አገራቸው ለመውሰድ መቸገራቸው የበርካቶቹ ጥያቄ ነው ‹‹ዶላር ስለሌለ ጠብቁ›› የመንግሥት የዘውትር ምላሽ ነው። ይህን ተከትሎ በርካቶች ለረዥም ጊዜ እንዲጠብቁ ሲገደዱ፣ ጥቂት የማይባሉትም በመግሥት ውትወታና ልምምጥ ትርፋቸውን መልሰው ሥራ ላይ እንዲያውሉት (ሪኢንቨስት እንዲያደርጉት) ይገደዳሉ። ይህንን ችግር ሰርክ የምሽት መወያያ ርዕሳቸው ሲያደርጉት፣ የውጭ ጋዜጠኞችም ከውጭ ባለሀብቶች ዘንድ ሲነሱ ከሚሰሟቸው ችግሮች አንዱ ይ‹‹የዶላር የለም፣ ጠብቁ›› ጉዳይ እንደሆነ ሲናገሩ ይመጣሉ

በመንግሥት በሚሰጡ አጓጊ ማበረታቻዎች በርካቶች ኢንቨስት ለማድረግ ይመጣሉ። አንዳንዶቹም የኢትዮጵያ ሚስዮኖች በየጊዜው እየጋበዙ በሚያቀርቡላቸው ገለ፣ ትልልቅ የሚባሉት ኩባንያዎችም የዓለም ባንክን ጨምሮ የውጭ አማካሪ ድርጅቶች ከሚያወጧቸው አኃዞች ጥቂት የማይባሉትም ከየራሳቸው ኤምባሲዎች ከሚቀርቡላቸው መረጃዎች በመነሳት ለኢንቨስትመንት ይመጣሉ። ባተረፉ ጊዜ ሙሉ ትርፋቸውን ወደ አገራቸው መውሰድ እንደሚችሉም የኢትዮጵያ ሕግ ይደነግላቸዋል።

 ይሁን እንጂ በርካቶች በሥራ ውጤት የሚያገኙትን ትርፍ ሊወስዱ ቀርቶ ለልዩ ልዩ ግብዓቶችና አቅርቦቶች ከውጭ ግዥ ለመፈጸም ሲቸገሩ ይታያሉ። በየስብሰባውም ይህንኑ ችግራቸውን ነሳሉ። ይጠይቃሉ። ሆኖም የዶላር አቅርቦት እጥረት በሰፈነበትና የጥቁር ገበያው በደራበትም ወቅት፣ ባንኮች የሚሰጡት አላጡም። ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይፋ እንዳደረገው ለግል ዘርፍ ብቻ ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ አቅርቧል። ይህም አገሪቱ የግብርናና የኢንዱስትሪ ብሎም የአገልግሎት ውጤቶችን ለበርካታ አገሮች ልካ ካገኘችው አጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ ጋር የሚቀራረብ ነው። እንደ ገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ፣ 2011 .. የተገኘው አጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ 2.67 ቢሊዮን ዶላር ነው። 

የንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ባጫ ጊና ከጥቂት ቀናት በፊት ይፋ እንዳደረጉት፣ ንግድ ባንክ ለግ ዘርፍ ብቻ ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ አቅርቧል። ይህ በቂ ባይሆንም ከሌላው ጊዜ የተሻለ እንደሆነ ተናግረው፣ በፕሮጀክት ብድር እየቀረበለት ከሚገኘው በርካታ ጥያቄ አኳያ ያቀረበው የዶላር መጠንም ሆነ ለግ ዘርፍ ያሰራጨው 22.5 ቢሊዮን ብር ብድር በቂ አይደለም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ 2007 .. ጀምሮ ባንኮች ሲቀርቡላቸው ለነበሩ የዶላር ይሰጠን ጥያቄዎች ማስታገሻ ይሆን ዘንድ 100 ሚሊዮን ዶላር ለግል ባንኮች አከፋፍ ነበር። ከዚህ ውስጥ አብዛኛው ለትርፍ ድርሻ ጥያቄዎች እንደሚውል ቢታመንም፣ የአገር ውስጥ ባለብቶችም ለግብዓትና ለሌሎች ግዥዎች ጥያቄያቸው በቂ ምላሽ የማይሰጥ አቅርቦት እንደሆነ በመግለጽ ብሔራዊ ባንክን ተቸተው ነበር።

እንዲህ ያሉ መለስ ቀለስ ጉዳዮች፣ የውጭ ባለሀብቶች ትርፋቸውን ሊወስዱ ባለመቻላቸው ስለሚያሰሙት ቅሬታና ወደፊት ለመምጣት በሚፈልጉና የውጭ ምንዛሪ ጉዳይ ጥያቄ በሆነባቸው ባለሀብቶች ጉዳይ ላይ መንግሥት ምን ይላል? ስለእነዚህ ጉዳዮች ከሪፖርተር ተጠይቀው ያብራሩት፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) እንዲህ ይላሉ። ‹‹ይህ ሁለት ነገር ይናገራል። አንደኛው ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ያላቸውን አመኔታ የሚያሳይ ነው። ዶላር እንደሌለ እያወቁት፣ እንደ ሁሉም ሰው ጠብቀውና ተሰልፈው እንደሚያገኙት እያወቁት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ኢንቨስት ማድረጋቸው ምን ዓይነት አመኔታ እንዳላቸው የሚያሳይ ነው።›› እንደ ከፍተኛ አማካሪው ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡበት ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና ልፍ የመጠበቁ አባዜ መፈታቱ እንደማይቀር ይህን ማድረግ የሚቻልባቸውም ‹‹ግልጽ መንገዶች አሉ፤›› በማለት ከመንገዶቹ አንዱ የወጪ ንግዱን ማሻሻል እንደሆነ ይገልጻሉ።

‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ዶላር አያትምም። ነገር ግን ገበያው ላይ ማነቆ የሆኑትን ነገሮች ፈትቶ፣ ወጪ ንግድ ማበረታታት አለበት። 100 ሚሊዮን ሕዝብ ባለበት አገር ውስጥ ወደ ውጭ የሚላኩት ምርቶችን ዝርዝር ብታወጣ ብዛታቸው ከአንድ ገጽ አይበልጥም። ነግር ግን በርካታ ለውጭ መቅረብ የሚችሉ ነገሮች አሉ።››

በመሆኑም የአገሪቱን የወጪ ንግድ ማሻሻል ስለሚቻልባቸው መንገዶች መንግሥት እየሠራ እንደሚገኝ፣ አዳዲስ የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ ግብሮቹ ውስጥም ይህንኑ በማካተት በሦስት ዓመታት ውስጥ የሚተገበር የማክሮ፣ የመዋቅር እንዲሁም የዘርፍ ማሻሻያ ዕቅዶችን እንደነደፈ በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ አቶ ማሞ እስመለዓለም ምኅረቱ መገለጹን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ እነዚህ መዋቅራዊ ማሻሻያዎች በግብርናው፣ በኢንዱስትሪውና በአገልግሎት መስኩ የሚተገበሩ ሲሆኑ፣ በመስኮቹ ለውጭ ምንዛሪ ግኝት የሚረዱ ዕርምጃዎችና እንቅስቃሴዎች ይከናወኑባቸዋል፡፡

መንግሥት የወጪ ንግዱን በምን አግባብ እንደሚያሻሽለው ይህ ነው የሚባል ተጨባጭና የተዘረዘረ መፍትሄ ሲያመላክት ባይታይም፣ ቢያንስ ከውጭ የሚገቡ የምግብ ሸቀጦችን በተለይም ስንዴና የምግብ ዘይትን ለመተካት የሚያስችል አካሄድ እንደሚከተል ሲያስታውቅ ሰንብቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለሰሞኑ የስንዴ እርሻ ማሳዎችን በመጎብኘት ተስፋ የሚሰጡ ጅምሮች እንዳሉ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥም የኢትዮጵያ የስንዴ አቅርቦትና ፍጆታ በአገር ውስጥ ምርት እንሚሸፈን ከወዲሁ አረጋግጠዋል፡፡ ግብርና ሚኒስቴርም ይህንኑ ዕውን ለማድረግ በቆላማ አካባቢዎች የተጀመሩ የሙከራ ሥራዎችን እያስኬደ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ይህ ሁሉ እንደሚሳካና ለውጥ እንደሚያመጣ ታሳቢ ይደረግና፣ ከውጭ ኢንቨስትመንት ጋር በተያያዘ የሚነሳ አንድ መሠረታዊ ጥያቄ በአገር ውስጥ ባለሀብቱም ሆነ በኢኮኖሚ ባለሙያዎች ዘንድ ጥያቄ አለ፡፡ ይኸውም ከዕውቀትና ከቴክኖሎጂ ሽግግር አኳያ የውጭ ኩባንያዎችና ባለሀብቶች ያስገኙት ውጤት ምን እንደሆነ ተንትኖና መዝኖ ይህ ነው ውጤቱ የሚል አካል አለመገኘቱ ነው፡፡ በየመድረኩም ይህ ጥያቄ ሲነሳ ይደመጣል፡፡

የጥያቄው መነሾም መንግሥት የውጭ ኢንቨስትመንትን ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ ከሚያደርግባቸው ምክንያቶች መካከል የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፈጠር ለማስቻል በማሰብ እንደሆነ የሚገልጸው ይጠቀሳል፡፡ ከዚህ ባሻገር የሥራ ዕድል እንዲፈጠርና ከቅርብ ጊዜ ወዲህም የውጭ ኢንቨስተሮች በወጪ ንግድ ላይ ያተኮሩ ምርቶች ላይ በማተኮር ለውጭ ገበያ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ፣ ብሎም የውጭ ምንዛሪ እንዲያስገኙ በማሰብ ጭምር ነው፡፡ አብዛኞቹ ከሚያስገኙት የውጭ ምንዛሪም ሆነ ከሚልኩት ምርት ይልቅ፣ ለጥሬ ዕቃና ለማሽነሪ ግዥ የሚጠይቁት ዶላር ትርፋቸው ታክሎበት፣ መንግሥትን በሌላ አቅጣጫም ማየት እንዲጀምር የሚያስገድደው እንደሆነ ምሁራን ይመክራሉ፡፡

አገሪቱ የምትልከው ምርት አነስተኛ ከመሆኑም ባሻገር የምታገኘው የውጭ ምንዛሪ እያሽቆለቆለ በመጣበት ወቅት ወደ ውጭ የሚወጣው የውጭ ምንዛሪ መጠን በተለይም ለዕቃ ግዥ እየተጠየቀ የሚወጣው ገንዘብ ላይ መንግሥት ተገቢውን ክትትል እንዲያደርግ በማሳሰብ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ገቢን አሳንሶ በማቅረብ (አንድ ኢንቮይሲንግ) እንዲሁም ወጪን አንሮ በመጠየቅ (ኦቨር ኢንቮይሲንግ) ወይም በጥቅሉ የንግድ ዋጋን በማዛባት በሚፈጸም የውጭ ምንዛሪ ማሸሽ ተግባር ተጎጂ ከሆኑ አሥር ዋና ዋና የአፍሪካ አገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷ ስለመሆኗ ይፋ የተደረገው ከአምስት ዓመታት በፊት ነበር፡፡

ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ግልጽነት ተቋም ወይም ግሎባል ፋይናንሺያል ኢንተግሪቲ ይፋ እንዳደረገውም በዚህ መንገድ ገንዘባቸው ከሚሸሽባቸው አገሮች አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ በየዓመቱ እስከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ እየሸሸባት እንደሚገኝ ሪፖርት አውጥቶ ነበር፡፡

 የውጭ ምንዛሪ ከሚሸሽባቸው መንገዶች አንዱ ለውጭ ባለሀብቶች የሚቀርቡ ቅጥ አልባ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችና የታክስ ዕፎይታዎች፣ በገቢና በወጪ መካከል የሚፈጸሙ ማጭበርበሮችና በሐሰተኛ ሰነድ ከተፈጠሩ፣ ህልውና ከሌላቸው፣ ነገር ግን እንዳሉ በማስመሰል የንግድ ግንኙነት እንደሚፈጸምባቸው በሚቀርቡ እህት ኩባንያዎች (ኦፍሾር ቢዝነስ) በኩል በርካታ ገንዘቦች ሲሸሹና ሲዘዋወሩ ተደርሶባቸው ተጋልጠዋል፡፡ ‹‹ፓናማ ፔፐርስ›› የተሰኘውን ጉድ የዘከዘኩ አጋላጭ ዘገባዎች የቅርብ ጊዜ ትዝታዎች ናቸው፡፡ በናፓማ ፔፐርስ ወይም በፓናማ ዶሴ ውስጥ ኢትዮጵያንም የተመለከቱ ጉዳዮች በጨረፍታ መገኘታቸው ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በውጭ ምንዛሪ ጥያቄዎች ላይ ብቻም ሳይሆን፣ መንግሥት ለውጭ ኩባንያዎች በሚሰጣቸው ማበረታዎችና ድጋፎች ላይም ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባው የሚጠይቁ አካላት እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን በማመላከት ጭምር ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች