Thursday, June 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኢሠማኮ ከስደት ለተመለሱት የቀድሞ ፕሬዚዳንቱ ዕውቅና ሰጠ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) በኮንፌዴሬሽኑ ምሥረታና ሠራተኞችን ለመብታቸው በማታገል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበራቸው ለሚነገርላቸው የቀድሞ የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት ዕውቅና ሰጠ፡፡

በተለያዩ ተፅዕኖዎች ከአገር እንዲሰደዱና ኑሯቸውን በውጭ አድርገው የቆዩት አቶ ዳዊ ኢብራሂም፣ በኢትዮጵያ የሠራተኞች ትግል ታሪክ ውስጥ የነበራቸውን አስተዋጽኦ በመዘከር ዕውቅናው እንዲቸራቸው የተደረገው፣ ሐሙስ ነሐሴ 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ስለሳቸው በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ነው፡፡

ኢሠማኮ ከመንግሥት ተፅዕኖ ውጪ ሆኖ በነፃነት እንዲመሠረትና እንዲንቀሳቀስ ከንጥስሱ ጀምረው በፕሬዚዳንትነት ያገለገሉት አቶ ዳዊ፣ ከሃያ ዓመታት በላይ በስደት ቆይተው በቅርቡ ወደ አገር ቤት መመለሳቸው ይታወቃል፡፡ ኢሠማኮም የአቶ ዳዊን አስተዋጽኦ በመዘከር ዕውቅና እንደሰጣቸው ከኮንፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ይገልጻል፡፡

አቶ ዳዊ  ለማስታወሻነት የአንገት ሀብል ከኢሠማኮ ተበርክቶላቸዋል፡፡ ከዕውቅናና ማበረታቻ በተጨማሪ ከኢሠማኮ ጋር መሥራት የሚችሉበት ዕድል ተሰጧቸዋል፡፡ አቶ ዳዊ ስለተሰጣቸው ዕውቅናና ማስታወሻም ኢሠማኮን አመሥግነዋል፡፡ የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎም፣ አቶ ዳዊ ስለሠራተኛው መብት መከበር የነበራቸውን አበርክቶ አውስተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች