Friday, June 2, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ሪፎርም አጀንዳዎች ከ100 ሚሊዮን ዶላር መመደቧን ይፋ አደረገች

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

‹‹የኢኮኖሚ  ፖሊሲዎች ለውጭ ብድር ዕዳ በመዳረግ የሚፈለገውን የሥራ ዕድል አላስገኙም››

 ማይክል ሬይኖር፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር

በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራሞችን ለመደገፍ አሜሪካ ካለፈው ዓመት ወዲህ የ100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጓን ይፋ አደረች፡፡ በኢትዮጵያ ለሚካሄዱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖሊቲካዊ ለውጦች ሙሉ ድጋፏን እንደምትሰጥ አረጋግጣለች፡፡

ዓርብ ነሐሴ 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ‹‹አድቫንሲንግ ኢኮኖሚክ ዳይቨርሲፊኬሽን ኢን ኢትዮጵያ›› በሚል ስያሜ የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ ግብር ይፋ በተደረገበት ወቅት ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬይነር፣ አገራቸው በኢትዮጵያ እየተካሄዱ በሚገኙ ፈርጀ ብዙ ለውጦች መደመሟንና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ፍላጎቶችን ቀዳሚ ያደረጉ ማሻሻያዎች እየተካሄዱ በመሆናቸውም መደሰቷን ተናግረዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ የሪፎርም አጀንዳዎች ከወዲሁ በርካታ ድሎች አስገኝተዋል፣ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ምኅዳር እንዲሁም የኢኮኖሚ ዕድሎችን አስፋፍተዋል ያሉት አምባሳደሩ፣ ለውጦቹ እየተጠናከሩ ሲቀጥሉም የአገሪቱን ዘለቄታዊ ሁኔታዎች ጭምር በማረጋገጥ ረገድ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

ከፈርጀ ብዙ የሪፎርም አጀንዳዎች መካከል የኢኮኖሚ ለውጥ ግቦቹ ወሳኝ ስለመሆናቸው አውስተው፣ ሌሎች ለውጦችን ለማስቀጠልም የኢኮኖሚ ለውጦቹ መሠረት መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ስፋትና ውስብስብነት አኳያ ኢኮኖሚውን ማደስና ማሻሻል ቀላል ሥራ እንደማይሆን በማውሳት፣ ነገር ግን ከባዱን ለማስቻል ጥንካሬ የሚሰጡ በርካታ ጎኖች እንዳሉና አገሪቱም በእነዚህ ጥንካሬዎቿ ላይ በመመሥረት እየተሻሻለች እንደምትሄድ አስረድተዋል፡፡ ለእነዚህ ለውጦች አመቺ ካሏቸው መካከልም ኢትዮጵያ ያሏት የኢኮኖሚ ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ብቃታቸው፣ እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ያላቸው ራዕይና የአመራር ብቃታቸው ለውጦችን ውጤታማ በማድረግና የአገሪቱን ትራንስፎሜሽን በማምጣት ረገድ ያላቸው ተስፋ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡  

ይህም ሆኖ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገሪቱ የተመዘገቡ የመሠረተ ልማት አውታሮች ግንባታ፣ በተለይም በመንገዶች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በጤና ክብካቤና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ መስክ የታዩት ለውጦች የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ያስገኟቸው መሆናቸውንም መስክረዋል፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ግንባታዎች ዋጋ አስከፍለዋል ያሉት አምባሳደር ሬይነር፣ ‹‹እነዚህ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ለውጭ ብድር ዕዳ በመዳረግ የሚፈለገውን የሥራ ዕድል አላስገኙም፡፡ የግል ዘርፉን ኢንቨስትመንትም አላመጡም፤›› ሲሉ ተችተዋል፡፡

ይህም ሆኖ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ የሚገኘው የአገሪቱ የሪፎርም አጀንዳ ከዚህ ቀደም ስኬት ባስገኙ ውጤቶች ላይ እንደሚመረኮዝ ተስፋ ሰጥቷል በማለት፣ በተለይ መዋቅራዊ ለውጦች ላይ ይታዩ የነበሩ ፈታኝ ችግሮችን በመፍታት፣ በግሉ ዘርፍ የሚመራ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ መነሳቱ ይበል እንደሚያሰኝ ተናግረዋል፡፡

የኢኮኖሚ ለውጥ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ የሚንቀሳቀሰው የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩኤስኤአይዲ)፣ የአሜሪካ ባለሀብቶችንና ባለሙያዎችን በማሳተፍ በኢትዮጵያ ለሚያካሂዳቸው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ድጋፍ የሚሰጥባቸውን ጨምሮ፣ አዲስ የጀመረውን የኢኮኖሚ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ለመገደፍ የ100 ሚሊዮን ዶላር አዲስ ዕርዳታ ማቅረቡን አምባሳደሩ አስታውቀዋል፡፡

ይህ ፕሮግራም ይፋ በተደረገበት ወቅትም የመንግሥት ባለሥልጣናት የተገኙ ሲሆን፣ በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ የልማት ማዕከል የተሰኘው ተቋም ፕሮፌሰር ሪካርዶ ሀውስማን (ዶ/ር) ተቋሙን ወክለው የአሜሪካ መንግሥት ይፋ ያደረገውን የኢኮኖሚ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ለማስተባበር ተገኝተዋል፡፡     

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች