Thursday, March 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየዋሊያዎቹና የሉሲዎቹ አኅጉራዊና ዓለም አቀፍ ተሳትፎ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ

የዋሊያዎቹና የሉሲዎቹ አኅጉራዊና ዓለም አቀፍ ተሳትፎ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ

ቀን:

ኢትዮጵያ በነሐሴ ወር በሁለቱም ፆታ ለምትወከልባቸው አኅጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮችን በሜዳዋ ሦስት ወሳኝ ጨዋታዎችን እንደምታከናውን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ያወጣው መርሐ ግብር ያስረዳል፡፡ ቀደም ብሎ ዝግጅት የጀመረው የሴቶች ብሔራዊ ኦሊምፒክ ቡድን ለቶኪዮ ኦሊምፒክ የካሜሮን አቻውን በሜዳው ሲያስተናግድ፣ ለዓለምና ለአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የሚጠብቃቸው የወንዶቹ ብሔራዊ ቡድኖች በተመሳሳይ ሜዳቸው ላይ ሩዋንዳንና ሌሴቶን ያስተናግዳሉ፡፡

በአሠልጣኝ ሰላም ዘርዐይ እየተዘጋጀ የሚገኘው የሴቶች ኦሊምፒክ ቡድን ለ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ የሚያደርገው በአፍሪካ በጥንካሬያቸው ከሚጠቀሱት ብሔራዊ ቡድኖች አንዱ ከሆነው ከካሜሮን ብሔራዊ ቡድን ጋር ሲሆን፣ ጨዋታውን የሚያደርገው ደግሞ ካፍ በቅርቡ ዝቅተኛውን መመዘኛ አያሟላም በሚል ጊዜያዊ ዕገዳ ጥሎበት በነበረው የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም ነሐሴ 20 ቀን 2011 ዓ.ም. ነው፡፡ ቡድኑ ወቅታዊ አቋሙን መፈተሽ ይችል ዘንድ ባለፈው ሳምንት ከኬንያ አቻው ጋር ከሜዳው ውጪ የወዳጅነት ጨዋታ አድርጎ ሦስት ለአንድ በሆነ ጠባብ ውጤት ተሸንፎ መመለሱ ይታወሳል፡፡

እንደ ሴቶቹ ሁሉ ከፊት ለፊቱ ወሳኝ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የሚጠብቀው የወንዶቹ ማለትም ለ2022 የኳታር ዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያና በ2020 ካሜሮን ለምታስተናግደው የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) ማጣሪያ ለሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ዝግጅት የተጨዋቾች ጥሪ ተደርጓል፡፡ ዋናው ብሔራዊ ቡድን ነሐሴ 28 ቀን በባህር ዳር ስታድየም የሌሴቶ አቻውን ሲያስተናግድ፣ በአፍሪካ የውስጥ ሊግ የሚጫወቱ ተጨዋቾች ብቻ በሚሳተፉበት ለቻን ዋንጫ ደግሞ መስከረም 11 ቀን 2012 ዓ.ም. በትግራይ ዓለም አቀፍ ስታድየም ሩዋንዳን ያስተናግዳል፡፡

የዋሊያዎቹና የሉሲዎቹ አኅጉራዊና ዓለም አቀፍ ተሳትፎ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ

 

ሁለቱንም ብሔራዊ ቡድኖች በዋና አሠልጣኝነት በማዘጋጀት ላይ የሚገኙት ኢንስትራክተር አብርሃም መብርሃቱ ለቻን የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከመረጧቸው ተጨዋቾች በተጨማሪ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በግብፅ ሊግ በመጫወት ላይ ለሚገኙት ጥሪ አድርገዋል፡፡ በዚህ መሠረት የተመረጡት በግብ ጠባቂነት ጀማል ጣሰው ከፋሲል፣ ምንተስኖት አሎ ከባህር ዳር፣ ለዓለም ብርሃኑ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ናቸው፡፡

ተከላካዮች፣ አስቻለው ታመነ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ያሬድ ባየ ከፋሲል፣ አንተነህ ተስፋዬ ከድሬዳዋ፣ ረመዳን የሱፍ ከስሁል ሽረ፣ አምሳሉ ጥላሁን ከፋሲል፣ ደስታ ደሙ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲና ዮናስ በርታ ከደቡብ ፖሊስ ሲሆኑ፤ አማካዮች  ጋቶች ፓኖምና ሽመልስ በቀለ ከግብፅ ሊግ፣ አማኑኤል ዮሐንስ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ከነአን ባርክነህ ከአዳማ፣ ሃይረዲን ሸረፋ ከመቐለ፣ ታፈሰ ሰለሞን ከሐዋሳ፣ ሱራፌል ዳኛቸው ከፋሲል፣ አማኑኤል ገብረ ሚካኤል ከመቐለ ከተማ ሆነዋል፡፡ አጥቂዎች ኡመድ ኡኩሪ ከግብፅ ኤልሰማይ፣ ቢኒያም በላይ ከስዊድን ሶሪያንስ፣ አዲስ ግደይ ከሲዳማ፣ ሙጅብ ቃሲም ከፋሲልና መስፍን ታፈሰ ከሐዋሳ ከተማ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በቅርቡ የባህር ዳር ከተማ ክለብ ዋና አሠልጣኝ ሆነው በሄዱት ምክትላቸው ፋሲል ተካልኝ ምትክ ምንን እንደ መረጡ ይፋ ያላደረጉት የዋሊያዎቹ አለቃ ኢንስትራክተር አብርሃም፣ ከውድድር ቅርፅና ይዘት ጋር ተያይዞ በፌዴሬሽኑና በክለቦች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እንደተጠበቀ፣ የተጨዋቾች የክፍያ እርከን ይፋ መሆን ለተጨዋቾቻቸው ሥነ ልቦና አዳጋች መሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡

ለዋና አሠልጣኙ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚናገሩት ከሆነ፣ ወቅታዊ የተጨዋቾች የደመወዝ እርከን ቡድኖቹ ቀጥሎ በሚኖራቸው የአፍሪካና የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አቅማቸውን አውጥተው እንዳይጫወቱ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ ቡድኑ ከሁለት ሳምንት በፊት የጂቡቲ አቻውን በደርሶ መልስ ጨዋታ በጠባብ ውጤት ያሸነፈበት ብቃት ብዙዎቹን ሲያነጋግር ሰንብቷል፡፡ ብዙዎቹ የቡድኑ ተጨዋቾች አሁን ላይ ከደመወዝ እርከን ጋር ተያይዞ ቅሬታ እንዳላቸው ሲናገሩ የሚደመጡ በመሆናቸው ለአሠልጣኙ ተጨማሪ የቤት ሥራ ብቻ ሳይሆን የቡድኑን ቀጣይ ዕጣ ፈንታ እንዳያሳጥረው ሥጋት አለ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...