Friday, March 31, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትኢትዮጵያ በሞሮኮ መላ አፍሪካ ጨዋታዎች ከፍተኛ የተባለውን ተሳትፎ ታደርጋለች

ኢትዮጵያ በሞሮኮ መላ አፍሪካ ጨዋታዎች ከፍተኛ የተባለውን ተሳትፎ ታደርጋለች

ቀን:

መንግሥት 60 ሚሊዮን ብር በጀት ፈቅዷል

ሰሜን አፍሪካዊቷ ሞሮኮ በምታስተናግደው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በተሳትፎም ሆነ በበጀት ከፍተኛ የተባለውን ተሳትፎ ታደርጋለች፡፡ ከነሐሴ 13 እስከ 26 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ በሞሮኮ ራባት በሚካሄደው 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ ኢትዮጵያ 188 አትሌቶችን ታሳተፋለች፡፡ የቡድኑ የመጀመርያ ልዑክ ባለፈው ቅዳሜ ነሐሴ 11 ቀን ወደ ስፍራው ያመራ ሲሆን፣ ሁለተኛው ልዑክ ደግሞ ነሐሴ 16 ቀን ተጠቃሎ እንደሚጓዝ ተነግሯል፡፡

54 የአፍሪካ አገሮች የሚታደሙበትና ሰኞ ነሐሴ 13 ቀን በንጉሥ ሞሌይ አብደላህ ስታዲየም በይፋ የሚጀመረው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች 18 የስፖርት ዓይነቶች 6,000 ስፖርተኞች ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በውድድሩ አትሌቲክስን ጨምሮ በሌሎችም ስፖርቶች ጠንካራ ተሳትፎ እንደሚያደርግ የሚጠበቀው የኢትዮጵያ ቡድን በአኅጉር ደረጃ ለሚደረጉ ተሳትፎዎች በዓይነቱ የመጀመርያ የተባለውን 60 ሚሊዮን ብር በጀት እንደተያዘለት ተነግሯል፡፡ ቡድኑ ነሐሴ 7 ቀን በአዲስ አበባ ሒልተን አሸኛኘት የተደረገለት መሆኑ ይታወሳል፡፡

በአሸኛኘት ፕሮግራሙ የስፖርት ኮሚሽነር አቶ ርስቱ ይርዳው፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር) እንዲሁም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ደራርቱ ቱሉና ሌሎችም የመንግሥት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት  አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር)፣ ቡድኑ መንግሥት ከወትሮው በተለየ ካደረገለት የበጀት ድጋፍ ጀምሮ ከፍተኛ ዝግጅትና ክትትልና ሲደረግለት የቆየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ደራርቱ ቱሉ በበኩሏ፣ ‹‹ኢትዮጵያን ለመወከል በመታደላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ፤›› ብላ የአንድ ቡድን ውጤታማነት የሚለካው በሚያስመዘግበው ሜዳሊያ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ማንነት የተላበሰ ስፖርታዊ ጨዋነት ሲታከልበት መሆኑን ጭምር አክላለች፡፡ በተጨማሪም ከሃያ ዓመታት በፊት ዕድሉን አግኝታ እንደነበር ተናግራ ስሜቱ ምን እንደሚመስል ልምድና ተሞክሮዋን አካፍላለች፡፡

‹‹በዚህ መላ አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ ስትካፈሉ አገራችሁን ወክላችሁ ስለሆነ፣ ከፊት የሕዝባችሁን ስሜት በማስቀደም የቡድን መንፈስ በማጠናከር፣ ኢትዮጵያዊ ዲሲፕሊን ጠብቃችሁ በውጤት ጭምር የተሻላችሁ በመሆን አገራችሁን እንደምታኮሩ እምነቱ አለኝ፤›› በማለት መልዕክታቸውን ያስተላፉት ደግሞ የስፖርት ኮሚሽነር አቶ ርስቱ ይርዳው ናቸው፡፡

ከአምስት አሠርታት በፊት እ.ኤ.አ. በ1965 በኮንጎ ብራዛቪል አስተናጋጅነት አንድ ብሎ የጀመረው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ለፓን አፍሪካኒዝም መቀንቀን መነሻ ስለመሆኑ ጭምር ይነገራል፡፡ ኢትዮጵያ ከተሳተፈችባቸው ትልቁን ውጤት ባለፈው  በኮንጎ ብራዛቪል በተከናወነው 11ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ሲሆን ስድስት የወርቅ፣ አምስት የብርና ስድስት የነሐስ በድምሩ 17 ሜዳሊያዎችን ያስመዘገበችበት ይጠቅሳል፡፡

በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ታሪክ ኢትዮጵያ የመጀመርያውን የነሐስ ሜዳሊያ በኮንጎ ብራዛቪል የመጀመርያው ጨዋታ ላይ ያገኘው ማሞ ወልዴ ሲሆን ውጤቱም በ5,000 ሜትር የተመዘገበ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መንግሥት ለዝግጅቱ የበጀተውን 60 ሚሊዮን ብር አስመልክቶ እስካሁን 38 ሚሊዮን ብር መለቀቁ ከዚህ ውስጥ 25 ሚሊዮኑ በውድድሩ ለሚሳተፉ ፌዴሬሽኖች መከፋፈሉና ቀሪው 13 ሚሊዮን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ካዝና ገብቶ ለሆቴልና ትራንስፖርት አገልግሎት መዋሉን የኦሊምፒክ ኮሚቴው ዋና ጸሐፊ አቶ ታምራት በቀለ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ቀሪው 22 ሚሊዮን ብር ቀጥሎ እንደሚገባ ይጠበቃልም ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...