“ችግራችንን በጋራ ለመፍታት ቆርጠን ከተነሳን እንደ አጋርና ኢስማኤል ሰላምና ብልፅግናን ማረጋገጥ ከባድ አይሆንብንም”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የ1440ኛ ዓመተ ሒጅራ ዒድ አል አድሃን አስመልክቶ ለሕዝበ ሙስሊሙ ነሐሴ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ፡፡ ችግሮች ሁሉ በአንድ ጀንበር ሊፈቱ እንደማይችሉ ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የአሁኑ ትውልድ ከትናንት ታሪኩ ትምህርት ወስዶ ከሚገኝበት አገራዊ የማንነት ቀውስ አዙሪት የሚወጣበትና ወደ ዕድገትና ወደ ብልፅግና ጎዳና መግባት የሚያስችለውን የቁጭት ስንቅ መሰነቂያ ማድረግ ይኖርበታል ሲሉ አሳስበዋል፡፡