Tuesday, May 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊነፃ የዳሌ የትከሻና የጉልበት ቀዶ ሕክምና እየተሰጠ ነው

ነፃ የዳሌ የትከሻና የጉልበት ቀዶ ሕክምና እየተሰጠ ነው

ቀን:

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ የቃጠሎ፣ የድንገተኛና የአደጋ ሕክምና ሆስፒታል (አቤት) ውስጥ የዳሌ፣ የትከሻና የጉልበት ሕመም ላለባቸው ሰዎች ነፃ ሕክምና መስጠት ተጀመረ፡፡

ከነሐሴ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ የአርቶሮስኮፒ ቀዶ ሕክምናውን ያከናወኑት በኢትዮ አሜሪካ ዶክተርስ ግሩፕ አስተባባሪነት ከአሜሪካ የመጡት የዳሌ ንቅለ ተከላና የአርቶሮስኮፒ ቀዶ ሕክምና ቡድኖች ናቸው፡፡

ከነዚህም መካከል የዳሌ ንቅለ ተከላ ሕክምና ቡድን ሕክምናውን ያከናወነው ባለፉት 15 ቀናት ሲሆን፣ የአርቶሮስኮፒክ ቡድን ደግሞ ተመሳሳይ የሆነውን የሕክምና አገልግሎት የሚሰጠው ከነሐሴ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ብቻ ነው፡፡

- Advertisement -

የዳሌ ንቅለ ተከላ ሕክምና ተባባሪ ፕሮፌሰርና የቡድኑ መሪ ክብረት ከበደ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የዳሌ ንቅለ ተከላ ሕክምና የማከናወኑ ሥራ በጣም ውድ የሆኑ መሣሪያዎችን ይጠይቃል፡፡ ሕክምናውንም ለማግኘት 700 ታካሚዎች ተመዝግበው ነበር፡፡ ከነዚህ መካከል ሕክምና የተደረገላቸው የጉዳት መጠኑ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰባቸው ሲሆኑ፣ የቀሩት ወደፊት ሕክምናውን ማግኘት የሚችሉበት እንደሚመቻች ነው ያመለከቱት፡፡

የቡድኖቹ ዋና ዓላማ የአቤት ሆስፒታል የአርትሮስኮፒ ማዕከል እንዲሆን ማድረግ ሲሆን፣ ለዚህም ለአገልግሎት ይዘዋቸው የመጡትንና አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺሕ ብር የሚያወጡ የሕክምና መሣሪያዎችን ለሆስፒታሉ ማበርከታቸውን፣ በቀዶ ሕክምናው ወቅት ለሆስፒታሉ ቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች የዕውቀት ሽግግር መከናወኑን ተባባሪ ፕሮፌሰሩ ገልጸዋል፡፡

ከመሣሪያዎቹም መካከል 500,000 ብር የሚያወጣውና አርትሬስ አርትሮስኮፒክ ታወር የተባለው መሣሪያ እንደሚገኝበት፣ መሣሪያውም በትንንሽ ቀዳዳ ካሜራ አስገብቶ ጉዳት የደረሰበትን ጉልበትን ትከሻን በመለየት ለማከም የሚረዳ መሆኑን አክለዋል፡፡

ሁለቱም የሕክምና ቡድኖች በአትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል የሚገኘውን ክሊኒክ ጎብኝተዋል፡፡ ክሊኒኩን አግባብ ባላቸው ዘመናዊ የሕክምና መሣሪያዎች ለማደራጀት የአርቶሮስኮፒ ቀዶ ሕክምና ቡድኑ ቃል ገብቷል፡፡

የዚሁ ቡድን መሪ ዊሚ ዲዮጌ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ሕክምናውን ለማግኘት 40 ታካሚዎች ተመዝግበዋል፡፡ ከነዚህም መካከል የጉዳት መጠናቸው ልዩ ሙያ የሚፈልግ 23 ታካሚዎች ቅድሚያ ይህም ሆኖ ግን ያለው ችግር በሙሉ ተቃሏል ማለት እንዳልሆነና ሌሎች ሐኪሞች እየተመላለሱ ክፍተቱን እንዲሸፍኑ የሚደረግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአቤት ሆስፒታል ምክትል ሜዲካል ዳይሬክተር ኒውሮሎጂስት አብርሃም ታደለ (ረዳት ፕሮፌሰር) ጉልበት የሚገናኘው በላይኛውና በታችኛው አጥንት ባሉ በሁለት ትላልቅ ጅማቶች መሆኑን ገልጸው፣ በስፖርት እንቅስቃሴ ወቅት መሀል ያሉት ጅማቶች የመቆረጥ አደጋ እንደሚደርስባቸው፣ እነዚህን ጅማቶች ለመስፋት ወይም ለመቀየር ደግሞ አስቸጋሪ እንደሆነ፣ ልዩ ችሎታና መሣሪያም እንደሚጠየቅ አመልከተዋል፡፡

የአለርት ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተርና የአጥንት ሕክምና ስፔሻሊስት ይሄይስ ፈለቀ (ዶ/ር) ቡድኖቹ ከሚያበረክቱት የሕክምና አገልግሎት ሁለት ዕድሎችን ማግኘት እንደሚቻል አመልክተው፣ የመጀመርያው ዕድል በጣም ተፈላጊና ውድ የሆኑ መሣሪያዎችን በነፃ ማግኝት ሲሆን፣ ሁለተኛው ዕድል ደግሞ ወጣት ቀዶ ሐኪሞችን ክህሎታቸውን እንደሚያሳድግና የስፖርትና የዳሌ ሕክምናን ደረጃ ከፍ ማድረጉ ነው ብለዋል፡፡

በአቤት ሆስፒታል የአርቶፔዲክስና የትራዎማ ክፍል ኃላፊና የአርቶፔዲክ ቀዶ ሐኪም ዘገነ ታዬ (ዶ/ር) ወደ ሆስፒታሉ ለሕክምና ከሚመጡት ሕሙማን መካከል አብዛኞቹ ከአደጋ ጋር የተያያዙ እንደመሆናቸው መጠን ቡድኖቹ በሰጡት አገልግሎትና ባበረከቱትም የሕክምና መሣሪያ ዘርፉ የበለጠ እንዲጠናከር ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...