Monday, May 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየአዲስ አበባን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ ከአውሮፓ  አውቶብሶች እንዲገዙና በቴክኖሎጂ የሚመራ የትራንስፖርት ሥምሪት...

የአዲስ አበባን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ ከአውሮፓ  አውቶብሶች እንዲገዙና በቴክኖሎጂ የሚመራ የትራንስፖርት ሥምሪት ተጠንቶ እንዲቀርብ ተወሰነ

ቀን:

ከሦስት ሺሕ በላይ የአውቶብሶች ግዥ እንደሚያስፈልግ ተገምቷል

በቀጣይ የሥራ ዕቅዶች ዙሪያ ሰሞኑን የመከረው የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት አጥጋቢ ውጤት ያልተመዘገበበት ጉዳይ የከተማዋ ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት የትራንስፖርት ችግር መሆኑን በመገምገም፣ ችግሩ በአፋጣኝ መቃለል የሚችልበት መንገድ ተጠንቶ እንዲቀርብ ወሰነ፡፡ በዚህ መሠረት አውሮፓ ሠራሽ አውቶብሶች እንዲገዙ፣ እንዲሁም በቴክኖሎጂ የሚመራ የትራንስፖርት ሥምሪት ለማድረግ ታቅዷል፡፡

የካቢኔውን ስብሰባ የመሩት ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በካቢኔው የተቀናጀ የሥራ አፈጻጸም ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡ ቢሆንም፣ በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ችግር መቅረፍ አለመቻሉንና ነዋሪዎችንም ለምሬት መዳረጉን መናገራቸው ታውቋል፡፡ ችግሩን በአፋጣኝ ለመቅረፍ የሚያስችል ጥናት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲቀርብላቸው መወሰናቸውን፣ የከንቲባው ጽሕፈት ቤት ቃል አቀባይ ወ/ሪት ፌቨን ተሾመ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

የከተማ የትራንስፖርት ፍላጎት የሚመለሰው በአንድ ጊዜ በርካታ ሰዎችን ማጓጓዝ የሚችሉ ዘመናዊ የሕዝብ ማመላለሻዎችን በመጠቀም መሆኑ የበርካታ አገሮች ተሞክሮና ስኬት እደንደሆነ የጠቆሙት ቃል አቀባይዋ፣ በአዲስ አበባ ከተማም የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ በርካታ ሰዎችን በአንድ ጊዜ የሚያጓጉዙ አውቶብሶችን በብዛት፣ እንዲሁም በቴክኖሎጂ የታገዘ ሥምሪት በመጠቀም እንደሆነ ካቢኔው እንደተስማማበት ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት አገልግሎት የሚሰጡ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች በቁጥርም ሆነ በጥራት በቂ አለመሆናቸውን፣ እንዲሁም በኋላቀር የትራንስፖርት ሥርዓት የሚሠማሩ በመሆናቸው ውጤታማ መሆን አለመቻላቸውን በመገምገም፣ ጥናትን መሠረት ያደረገ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲተገበር ካቢኔው ውሳኔ ማሳለፉን ወ/ሪት ፌቨን አስረድተዋል፡፡

በዚህም መሠረት በአሁኑ ወቅት አገልግሎት እየሰጡ በሚገኙት 1,500 አውቶብሶች ችግሩን ማቃለል የሚታሰብ ባለመሆኑ ከሦስት ሺሕ በላይ ተጨማሪ አውቶብሶች በተለያዩ ምዕራፎች እንዲገዙ መወሰኑን የገለጹት ቃል አቀባይዋ፣ አውቶብሶቹ እንደ ከዚህ ቀደሙ በአገር ውስጥ የሚገጣጠሙ ወይም በቻይና የሚመረቱ እንደማይሆኑ አስታውቀዋል፡፡

ይህ የሚሆንበትም ምክንያት የሚገዙት አውቶብሶች ለረጅም ጊዜ የሚያገለግሉና በጥናት ላይ ተመሥርቶ ተግባራዊ ከሚደረገው በቴክኖሎጂ የሚደገፍ ዘመናዊ የሥምሪት ሥነ ሥርዓት ጋር እንዲጣጣሙ ለማድረግ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ከአንድ ማዕከል በመሆን የከተማዋን ወቅታዊ የትራንስፖርት ፍላጎት በማጤን ሥምሪት የሚከናወንበት የቴክኖሎጂ ሥርዓት በአጭር ጊዜ ተጠንቶ እንዲቀርብላቸው፣ ምክትል ከንቲባው ማዘዛቸውንም ቃል አቀባይዋ አክለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ከሳምንት በፊት ባካሄደው ስብሰባው፣ የከተማውን ካቢኔ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡

የሥራ አፈጻጸማቸውን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት ምክትል ከንቲባ ታከለ ካነሷቸው የሥራ ክንውኖች መካከል፣ በ60 ቢሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባው የለገሃር ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር ዝግጅቶች በመፋጠን ላይ መሆናቸውን፣ የከተማዋን ገጽታ በከፍተኛ መጠን እንደሚቀይረው የሚገመተውና በ30 ቢሊዮን ብር ወጪ ግንባታው የተጀመረው “ሸገርን የማስዋብ” ፕሮጀክት ሥራ በፍጥነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ሪፖርት አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም የዓድዋ ጦርነትን ለመዘከር የታቀደው የሙዝየም ፕሮጀክትና ሌሎች የከተማዋን ገጽታ የሚቀይሩ ስድስት ፕሮጀክቶች፣ በ10.7 ቢሊዮን ብር ወጪ ግንባታቸው መጀመሩንም አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...