Tuesday, May 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊለከፍተኛ ትምህርት ዓለም አቀፍ የአማካሪ ምክር ቤት መቋቋሙ ይፋ ሆነ

ለከፍተኛ ትምህርት ዓለም አቀፍ የአማካሪ ምክር ቤት መቋቋሙ ይፋ ሆነ

ቀን:

በተለያዩ የዓለም ክፍል የሚገኙ 130 ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ምሁራንና ሳይንቲስቶች የከፍተኛ ትምህርትን አቅም ከፍ ለማድረግ የሚያስችል ዓለም አቀፍ የአማካሪ ምክር ቤት መሥርተው ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ሒሩት ወልደማርያም (ፕሮፌሰር) እንደገለጹት፣ ምክር ቤቱ በዓመት ሁለት ጊዜ መድረክ እየፈጠረ የመመካከር፣ የክህሎትና የዕውቀት ሽግግር የሚያደርግ ሲሆን ምሁራኑም ለተወሰነ ጊዜ እየመጡ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ያስተምራሉ፡፡

ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ሳምንት ማገባደጃ በግል ከፍተኛ ትምህርት ዙሪያ ለሁለት ቀናት ያዘጋጀውን መድረክ ሚኒስትሯ ሲከፍቱ እንዳመለከቱት፣ ምሁራኑና ሳይንቲስቶቹ ተማሪው የወደፊት ዓላማ እንዲኖረው ለማድረግ የሚያስችል አነቃቂ ንግግሮች ያደርጋሉ፡፡ ከዚህም ሌላ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶችንም እየሰበሰቡ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማቀርብ ሥራ እንደሚያከናውኑና በአጠቃላይ የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓትን የማገዝና የማዘመን ሥራ እንደሚያከናውኑ ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

እንደሚኒስትሯ አባባል፣ ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም. መካከለኛ ገቢ ያላት አገር እንድትሆን ለማድረግ የሚቻለው የተማረ፣ የሠለጠነና ብቁ የሰው ኃይል ሲኖር ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ሁለት ብቻ የነበሩት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ ወደ 50 ከፍ ሲሉ፣ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደግሞ ከ200 በላይ ደርሰዋል፡፡

ከተጠቀሱት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አራቱ ዩኒቨርሲቲዎች፤ የቀሩት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጆች መሆናቸውን ገልጸው፣ አሁን ካለው የሕዝብና የወጣቶች ብዛት አንጻር ሲታይ በቂ የሆነ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አለ ለማለት እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡

ተቋማቱ አዲስ እንደመሆናቸው መጠን አቅማቸውን ለማጎልበትና ዓለም በከፍተኛ ትምህርት ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ ላይ ቢያንስ ለማቅረብ በከፍተኛ ትምህርት ዙሪያ የሚነጋገር እንደዚሁ ዓይነት ዓለም አቀፍ መድረክ ማዘጋጀት በእጅጉ ወሳኝነት እንዳለው አስረድተዋል፡፡

የቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ወንድወሰን ታምራት (ተባባሪ ፕሮፌሰር)፣ ኢትዮጵያ ላለፉት 20 ዓመታት በግል ከፍተኛ ትምህርት ዘርፉ ሰፊ ተሳትፎና ዕድገት ያሳየች መሆኑን ጠቅሰው፣ በዚህም የተነሳ የግሉ ዘርፍ የአገሪቱን ከፍተኛ ትምህርት 14 በመቶ ያህሉን መሸከም ችሏል ብለዋል፡፡

አገሪቱ በአፍሪካ አኅጉር ካሉት በዘርፉ ወደኋላ የገባች ብትሆንም፣ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተሳትፎ ካሉት ተማሪዎች ቁጥር አኳያ ሲታይ ከአፍሪካ ከቀዳሚዎቹ እንደምትመደብ ገልጸዋል፡፡

ዘርፉ አዲስ እንደመሆኑ፣ ያሉትን ችግሮችና መልካም ተሞክሮዎች በጥናት እያዘጋጀ እንደሚያቀርብ፣ ዩኒቨርሲቲው የተቻለውን ጥረቶች ሁሉ እያደረገ መሆኑን ገልጸው ከጥረቶቹም መካከል አንዱና ዋነኛው ከአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበር ጋር በመተባበር በአኅጉር አቀፍ ደረጃ ያሉትን ልምዶችና ተሞክሮዎች መለዋወጥ የሚያስችል መድረክ መፍጠሩ እንደሚገኝበት አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ከፍተኛ ትምህርት ገና አዲስ እንደመሆኑ ለማደግ ጊዜ፣ መልካም ፖሊሲዎችና ተከታታይ የመንግሥት ድጋፎች እንደሚያስፈልጉት፣ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደግሞ ወደ ተሻለ የጥራት ደረጃ በመሸጋገር ከመንግሥትና ከሕዝብ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ተጠናክረው መሥራት እንደሚኖርባቸው አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...