Saturday, May 18, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየኢቦላ ወረርሽኝ እንዳይከሰት የቅድመ መከላከል ተግባር እየተከናወነ ነው

የኢቦላ ወረርሽኝ እንዳይከሰት የቅድመ መከላከል ተግባር እየተከናወነ ነው

ቀን:

የኮሌራ ወረርሽኝ በአብዛኛው በቁጥጥር ሥር ውሏል

የዓለም ጤና ድርጅት በዴሞክራቲክ ኮንጎ የተከሰተውን የኢቦላ ወረርሽኝ የዓለም የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ብሎ ማወጁን ተከትሎ ወረርሽኙ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ፣ በበሽታው የተያዘ ሰው ቢኖር ለማከም እንዲቻል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸው ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር በየነ ሞገስ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የመከላከሉ ተግባራት ተጠናክሮ የቀጠለው በቦሌ፣ በድሬዳዋ፣ በመቐለና በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ኤርፖርቶች የሰውነት ሙቀት በመለካት፣ የልየታ ሥራ በማከናወንና የለይቶ ማቆያ ማዕከላትን በማቋቋም ነው፡፡

- Advertisement -

ከዚህም ሌላ ከ280 በላይ የሚሆኑ የሕክምና፣ የኅብረተሰብ ጤናና ሌሎች ባለሙያዎችን በማሰማራት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሠራ እንደሚገኝ፣ የዚህ አካል የሆነው የታማሚዎች ሕክምና እና አያያዝ ላይ ዕለታዊ የተግባር ልምምድ በማድረግ ባለሙያዎቹ ራሳቸውን ብቁ እንዲያደርጉ እየተሠራ መሆኑንም አክለዋል፡፡  

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዴሞክራቲክ ኮንጎ በሳምንት ውስጥ 25 ያህል በረራዎች እንደሚያደርግ፣ በዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በዓለም አቀፍ የጤና ደንብ (አይኤችአር 2005) መሠረት ከኮንጎ የሚመጡ ተጓዦችን የሰውነት ሙቀት በመለካት የልየታ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚመጡ መንገደኞች ከበሽታው ነፃ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በኢትዮጵያ በሚቆዩባቸው ጊዜያት እስከ ሦስት ሳምንት ድረስ ባሉበት ቦታ ክትትል ይደረጋል፡፡ በዚህም መሠረት ልየታ ከተሠራባቸው መንገደኞች ውስጥ ለ17,302 እስከ 21 ተከታታይ ቀናት ክትትል ተደርጎላቸዋል፡፡ በአውሮፕላን ማረፊያው በበሽታው የተያዙ መንገደኞች ቢያጋጥሙ ለማከም የሚያስችል ሁለት የለይቶ ማከሚያ ማዕከላት መዘጋጀቱን፣ ከዚህም በተጨማሪ በቦሌ ጨፌ የኢቦላ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል መዘጋጀቱን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ከአየር ትራንስፖርት ከሚገቡ መንገደኞች በተጨማሪ በ18 የየብስ መግቢያና መውጫ ኬላዎች ላይ የሰውነት ሙቀት በመለካት የልየታ ሥራ እየተሠራ ይገኛል፡፡ በጋምቤላ ክልል በልየታው የሥራ ጊዜ በኢቦላ በሽታ የተጠረጠሩ መንገደኞች ሲገኙ፣ ወደ ሕክምና ጣቢያ እስኪወሰዱ ድረስ አምስት የለይቶ ማቆያ ጣቢያዎች እንዲሁም የተሻለ ሕክምና ለመስጠት የሚያስችል የሕክምና ማዕከል በጋምቤላ ከተማ ሆስፒታል ውስጥ እንደተዘጋጀ አመልክተዋል፡፡

የመተላለፊያ መንገዶችም ከበሽታው በተያዙ ሰዎች ደምና ከሰውነት በሚወጡ ፈሳሾች (ሰገራ፣ ሽንት፣ አክታና የወንድ ዘር ፈሳሽ) አማካይነት እንዲሁም በሽተኞቹ የተጠቀሙበትን ቁሳቁሶች (አልጋ፣ ልብስ፣ አንሶላ፣ ጓንት፣ በሕክምና ወቅት የሚለበሱ ልብሶችና ጥቅም ላይ የዋሉ የሕክምና ቁሳቆሶች) ጋር በሚፈጠር ንክኪ ሲሆን ለበሽታው የተጋለጡ ሰዎች ምልክት የሚሳዩበት ጊዜ ከ2 እስከ 21 ቀናት ባሉ ጊዜያት ውስጥ ነው፡፡ ምልክት ያልታየባቸው ሰዎች በሽታውን ባያስተላልፉም፣ አንድ ሰው በበሽታው መያዙን ማረጋገጥ የሚቻለው ግን በላብራቶሪ ምርመራ ብቻ ነው፡፡

ወረርሽኙ ቢከሰት ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው የጤና ባለሙያዎች፣ የቤተሰብ አባላት፣ አስታማሚዎች እንዲሁም በግነዛ ወቅት ከአስከሬኑ ጋር ንክኪ የሚኖራቸው ሰዎች መሆናቸውን በየነ ሞገስ (ዶ/ር) ጠቁመው፣ ከበሽታው የመከላከያ መንገዶች እጅን መታጠብና በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች ከሚወጡ ፈሳሾች ጋር ንክኪ አለማድረግና በኢቦላ በሽታ የሞቱ ሰዎች አስከሬን ከመንካት መቆጠብ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ኢቦላ በዴሞክራቲክ ኮንጎ ከ2014 ጀምሮ የተከሰተ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በሰሜን ኪቩ ከተማ ወረርሽኙ ተቀስቅሶ የብዙ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል፡፡ ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ በበሽታው ከተያዙት 2,659 ሰዎች ውስጥ 1,782 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን ዶክተሩ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ኮሌራን አስመልክተው እንዳብራሩት፣ በኦሮሚያ ክልል በኮሌራ በሽታ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 464 የደረሰ ሲሆን፣ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በቦረና ዞንና በሞያሌ ወረዳ 15፣ በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን በጎሮ ጎቱ ወረዳ 14 በድምሩ በ29 ሰዎች ላይ ተከስቶ አስፈላጊ ሕክምና እየተደረገላቸውም ይገኛል፡፡ በሌሎች ክልሎችና በአብዛኛው ወረርሽኙ በተከሰተባቸው የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች ወረርሽኙ በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት በተከናወኑ የቅድመ መከላከል እንቅስቃሴዎችች የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት በተለያዩ ሚዲያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ብዙ ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው በዓላት ላይ በማስተማር፣ ኅብረተሰቡ በወሰዳቸው የጥንቃቄ ተግባራት እንዲሁም በተሰጡ የጤና ድጋፎች ክትባትን ጨምሮ ወረርሽኙ ሊቀንስ ችሏል፡፡ ይሁንና ማኅበረሰቡ በዚህ ሳይዘናጋ አሁንም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ