Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትዋሊያዎቹ በወሳኝ ምዕራፍ ጅምር

ዋሊያዎቹ በወሳኝ ምዕራፍ ጅምር

ቀን:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) በ2010 የውድድር ዓመት ከአኅጉራዊ ሆነ ከዓለም አቀፍ ተሳትፎ ገና በጠዋቱ መሰናበቱን ተከትሎ ብዙዎቹ የቡድኑ ተጫዋቾች ትኩረታቸውን ለአገር ውስጥ ውድድር እንዲያደርጉ አድርጎ ቆይቷል፡፡ ይህ ደግሞ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) በየወሩ ይፋ በሚያደርገው የአገሮች የእግር ኳስ ደረጃ የኢትዮጵያ እግር ኳስ መሻሻል ቀርቶ ቀድሞ የነበረበትን እንኳ ማስጠበቅ ተስኖት በማሽቆልቆል ላይ ይገኛል፡፡

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ካሜሩን በሚቀጥለው ዓመት በምታስተናግደው የአፍሪካ አገሮች በውስጥ ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ የሚሳተፉ ብሔራዊ ቡድኖች የማጣሪያ ውድድሮቻቸውን በማከናወን ላይ ናቸው፡፡ ባለፈው ዓርብ ሐምሌ 20 ቀን 2011 ዓ.ም. የመጀመሪያ ማጣሪያውን ከጅቡቲ አቻው ጋር ጅቡቲ ላይ ያደረገው ብሔራዊ ቡድን በጠባብ ውጤት 1ለ0 አሸንፎ ተመልሷል፡፡ በሜዳው የሚያደርገውን የመልስ ጨዋታ ደግሞ እሑድ ሐምሌ 28 ቀን በድሬዳዋ ስታዲየም አንደሚያከናውን ይጠበቃል፡፡

በቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብርሃቱ እየተዘጋጀ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቡድን፣ ከቻን ማጣሪያ በተጨማሪ ለ2021 የአፍሪካ ዋንጫ እና ለ2022 ኳታር የዓለም ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ የጨዋታ ፕሮግራሙ ታወቋል፡፡ በዚህም መሠረት ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከአይቮሪኮስት ማዳጋስካርና ኒጀር ጋር መደልደሉ የታወቀው ቀደም ብሎ ሲሆን፣ ለዓለም ዋንጫ የመጀመሪያውን ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ደግሞ ከሌሴቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር ከሜዳው ውጪ ጳጉሜን  ቀን ቀን 2011 ዓ.ም. ይጫወታል፡፡

ባለፈው ዓርብ በጅቡቲው ሐሰን ጉሌድ ስታዲየም የሙቀት መጠኑ ከ43 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ተጫውተው ውጤት ይዘው የተመለሱት ዋሊያዎቹ፣ እሑድ ድሬዳዋ ላይ የተሻለ ተንቀሳቅሰው ተጋጣሚያቸውን ጥለው ወደ ተከታዩ ዙር የሚያሳልፋቸውን ውጤት እንደሚያስመዘግቡ የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ አብርሃም ተናግረዋል፡፡ የድሬዳዋው የመልስ ጨዋታ እንደ ብዙዎቹ እምነት ከሆነ አሠልጣኙና የቡድን ስብስባቸው በቀጣይ ስለሚኖረው የዝግጅትና የተፎካካሪነት ዕጣ ምን እንደሚመስል ፍንጭ የሚታይበት እንደሚሆን ከወዲሁ እየተነገረ ይገኛል፡፡

ከሦስት አሠርታት በኋላ ኢትዮጵያና የአፍሪካ ዋንጫ እንደገና የተገናኙት ከሰባት ዓመት በፊት በደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ዋንጫ ነበር፡፡ ቡድኑ ምንም እንኳ በወቅቱ በሻምፒዮናው የነበረው ተሳትፎ አመርቂ ባይሆንም፣ ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፉ ብቻ በቀጣይ ስለሚኖረው የአገሪቱ እግር ኳስ ተነሳሽነትን ለመፍጠር ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል ተብሎ ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት የነበረ መሆኑ ግን አይዘነጋም፡፡ ብዙ የተባለለት የዋሊያዎቹ የወቅቱ እንቅስቃሴ ከአፍሪካ ምርጥ አሥር ቡድኖች አንዱ ሆኖ በትልቁ ለሚጠበቀው የዓለም ዋንጫ የመጨረሻ ጨዋታውን ከምዕራብ አፍሪካዊቷ የእግር ኳስ አገር ናይጀሪያ ጋር ተጫውቶ ከተሸነፈ በኋላ ጉዞው የኋሊት ሆኖ አሁን ላይ ይገኛል፡፡

እንደሚታወቀው የአንድ አገር ብሔራዊ ቡድን መሠረቱ ክለቦች ናቸው፡፡ ይሁንና ብዙዎቹ በተለይም የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች የብሔራዊ ቡድኑን ውድቀት ከቁብ ባለመቁጠር ሙሉ ትኩረታቸውን ለአገር ውስጥ ፉክክር ብቻ በማተኮር ከግብ ጠባቂ ጀምሮ ለጎረቤት አገር ተጨዋቾች ከፍተኛውን በጀት ማዋላቸው የዋሊያዎቹ  ውጤት ከቀን ወደ ቀን ከ‹‹ድጡ ወደ …›› እንዲሆን ትልቁን ድርሻ እንዲይዝ ምክንያት ሆኗል፡፡

ክለቦች ለአንድ የጎረቤት አገር ተጫዋች የዝውውሩን ሳያካትት ወርኃዊ ክፍያ 300,000 መክፈል ጀምረዋል፡፡ ለዚህ ክፍያ የሚመጥኑ ታዳጊዎች ታጥተው ነው ወይ የሚሉ ሙያተኞች ቢኖሩም፣ ክለቦች የ‹‹ውስጥ ጉዳያችን ነው›› በሚል እስካሁን ጠያቂ አላገኙም፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የውጤት ቀውስ የአንድ ሳምንት ጉዳይ እየሆነ ከዓለምም ሆነ ከአፍሪካ ከመጨረሻዎቹ መሪ አንዱ መሆኑን ቀጥሎበታል፡፡

አሠልጣኝ አብርሃምና ቡድናቸው ከፊት ለፊታቸው ጠንካራ ፈተና ይጠብቃቸዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ሙያተኞች የቡድኑን ዋና አሠልጣኝ ጨምሮ አሁን ላይ እነዚህን ችግሮች ደፍሮ በመናገር፣ ክለቦችም ሆኑ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በእግር ኳሱ ጉዳይ ቆም ብለው እንዲያስቡ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል የሚል እምነት አላቸው፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...