Friday, June 2, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የአኩሪ አተር ግብይት እየጨመረ እንደሆነ ምርት ገበያው ገለጸ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በኢትዮጵያ ምርት ገበያ መገብየት የጀመሩት ሁለቱ አዳዲስ ምርቶች የግብይት መጠናቸው ከፍ እያለ መምጣቱንና በተለይ አኩሪ አተር በአራት ወር ውስጥ ብቻ ከ1.29 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ዋጋ መገበያየቱ ተገለጸ፡፡ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በተለይ ከሚያዝያ 22 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በምርት ገበያው መገብየት የጀመረው አኩሪ አተር በሰኔ 2011 ዓ.ም. የግብይት ሒደቱ ከቡና ቀጥሎ ከፍተኛ ግብይት የተፈጸመበት ምርት ሊሆን መቻሉን ነው፡፡

አኩሪ አተር በሰኔ ወር 11,409 ቶን ምርት ለምርት ገበያው ቀርቦ በ177.2 ሚሊዮን ብር መገበያየት ችሏል፡፡ ይህም በወሩ ውስጥ ከተገበያዩ ምርቶች በመጠንና በዋጋ ሁለተኛ ደረጃን እንዲይዝ አድርጎታል፡፡ ምርት ገበያው አኩሪ አተር ማገበያየት ከጀመረበት ሚያዝያ 22 ቀን 2011 ዓ.ም. እስከ ሐምሌ 3 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ በጠቅላላው 92,103 ቶን ምርት በ1.29 ቢሊዮን ብር መገብየት መቻሉ፣ አዲስ ምርቶች በዘመናዊ ግብይት ውስጥ የሚያስገኙትን ጠቀሜታ ያሳያ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በሰኔ 2011 ዓ.ም. በነበሩት 19 የግብይት ቀናት 26,137 ቶን ቡና፣ 11,409 ቶን አኩሪ አተር፣ 5,760 ቶን ሰሊጥ፣ 1,728 ቶን ነጭ ቦሎቄና 40 ቶን ሽምብራ በ2.39 ቢሊዮን ብር አገበያይቷል፡፡

ወደ ምርት ገበያው የግብይት ሥርዓት ታኅሳስ 22 ቀን 2011 ዓ.ም. የገባው ሽምብራ የመጀመርያ ግብይት ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. የተካሄደ ሲሆን፣ በዚህም 400 ኩንታል ሽንብራ ለገበያ ቀርቦ በ772 ሺሕ ብር ግብይቱ ተፈጽሟል፡፡

በሰኔ ወር ቡና የግብይቱን 58 እና 76 በመቶ በግብይት መጠንና ዋጋ ቀዳሚ ሲሆን፣ ለውጭ ገበያ የሚቀርብ ቡና በግብይት መጠንና ዋጋ ተመሳሳይ 62 በመቶ ይዞ ቀዳሚ ሆኗል፡፡ በወሩ 15 ሺሕ ቶን ለውጭ ገበያ የሚቀርብ ያልታጠበ ቡና በ1.07 ቢሊዮን ብር የተገበያየ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ የግብይት መጠኑን የጊምቢ 20 በመቶ፣ የኢሉአባቦራ 18 በመቶ፣ የቄሌም ወለጋና የጂማ 12 በመቶ የቤንች ማጂ ዘጠኝ በመቶ፣ የሐረር ሰባት በመቶ በመያዝ ቀዳሚ መሆናቸውን ምርት ገበያው አስታውቋል፡፡ እንዲሁም 923 ቶን ለውጭ ገበያ የሚቀርብ የታጠበ ቡና በ60.7 ሚሊዮን ብር የተሸጠ ሲሆን፣ የሲዳማ ቡና የግብይቱን 40.6 በመቶ ይዟል፡፡ ለአገር ውስጥ ገበያ የሚቀርብ 5,449 ቶን ቡና በ328.9 ሚሊዮን ብር መገበያቱን የሚያመለክተው ይኸው መረጃ፣ የቡና ግብይት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ22 በመቶና የ18 በመቶ በግብይት መጠንና ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በዚህ ወር 5,760 ቶን ሰሊጥ በ351.66 ሚሊዮን ብር የተገበያየ ሲሆን፣ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀርም የሰሊጥ ግብይት በዋጋ 18 በመቶ ጭማሪ ሲያሳይ በመጠን 11 በመቶ ቀንሷል፡፡

በሌላ በኩል 1,728 ቶን ነጭ ቦሎቄ በ35.54 ሚሊዮን የተሸጠ ሲሆን፣ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር መጠኑ በ24 በመቶ ቢቀንስም፣ በግብይት ዋጋ 1.38 በመቶ ጨምሯል ብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች