Monday, June 17, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉ መስኮችን ሊከልስ ነው

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

በረቂቅ ሕጉ ላይ ምክክር ተካሒዷል

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኢንቨስትመንት አዋጅን ለማሻሻልና ድንጋጌዎችን ለመከለስ በጀመረው እንቅስቃሴ ውስጥ ከሚካተቱት ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለከሉ የኢንቨስትመንት ዘርፎችንና ሌሎችም ክለሳዎች እንደሚደረጉ አስታወቀ፡፡

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽር አቶ አበባው አበባየሁ እንዳስታወቁት፣ በኢንቨስትመንት መስክ እዚህም እዚያም የወጡ ሕጎችንና ለሌሎች ተቋማት በውክልና የተሰጡ ሕጎችን ወደ አንድ ማዕቀፍ ከማምጣት ጀምሮ፣ ዘመናዊ የቁጥጥርና የአስተዳደር ማዕቀፍ ለመዘርጋት የሚያስችሉ ማሻሻያዎችን ያካትታል፡፡

ይህም ሆኖ በተለይ በነባሩ ሕግ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉት ላይ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ ተጠቅሷል፡፡ የፖስታ አገልግሎት፣ የሚዲያ ሥራ፣ የሎጂስቲክስ ዘርፍ፣ የቴሌኮም፣ የባንክ፣ ከ50 ሰዎች በታች የመጫን አቅም ያላቸውን አውሮፕላኖች የሚጠቀም የአቪዬሽን ሥራና ሌሎችም መሰል የኢንቨስትመንት መስኮች ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተፈቀዱ ናቸው፡፡

በአንፃሩ ለመንግሥት ብቻ የተተው ወይም ከመንግሥት ጋር በሽርክና የሚከናወኑ ሥራዎች ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፍና ማሰራጨት ሥራ፣ የፖስታ አገልግሎት ከ50 በላይ ተሳፋሪ የሚጭኑ አውሮፕላኖችን ኦፕሬት ማድረግ ለመንግሥት የተከለሉ ሲሆኑ፣ ከመንግሥት ጋር በሽርክና የሚካሔዱ ከተባሉት ውስጥም የመሣሪያና የጥይት ማምረት ተግባርና የፖስታ አገለግሎት ይጠቀሳሉ፡፡  

እንዲህ ያሉትን የኢንቨስትመንት መስኮች በተለይም ለአገር ውስጥ የተከለሉት ላይ ክለሳ ከማድረግ ባሻገር፣ በኢንቨስትመንት መስክ የተፈቀዱ ማበረታቻዎችና የኢንቨስትመንት መስኮችም ዳግመኛ እንደሚፈተሹና ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር እንዲገናዘቡ እንደሚደረግ ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡ በረቂቅ ሕጉ ላይ ከመንግሥትና ከግሉ ዘርፍ ተዋንያን ጋር በዝግ ውይይት ተደርጓል፡፡ በመጪው ዓመትም ሕጉ ፀድቆ ሊተገበር እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች