Wednesday, June 19, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ሊጠናቀቅ አንድ ወር በቀረው በጀት ዓመት የወጪ ንግዱ ከ1.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት አስመዘገበ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከ3.9 ዶላር በላይ ገቢ ሲጠበቅ 2.3 ቢሊዮን ተገኝቷል

ጫትና ባህር ዛፍ ትልቅ ገቢ አስገኝተዋል

ከግብርና፣ ከማኑፋክቸሪንግ፣ እንዲሁም ከማዕድን ምርቶች በአጠቃላይ 3.92 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ቢታቀድም በ11 ወራት ሊገኝ የቻለው 2.39 ቢሊዮን ዶላር ወይም 61 በመቶ ብቻ በመሆኑ፣ ከ1.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት የታየበት አፈጻጸም አስመዘገበ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ እንደሚያመለከትው፣ ለዘንድሮ ከታቀደው ገቢ ባሻገር ዓምና በተመሳሳይ ወራት ከተገኘው 2.59 ቢሊዮን ዶላር አኳያም፣ የዚህ ዓመት 11 ወራት የወጪ ንግድ ገቢ አፈጻጸም በ1.97 ቢሊዮን ዶላር ያነሰ ሆኗል፡፡ ለዚህ ደካማ አፈጻጸም ምክንያት ከሆኑት ውስጥ ቡና፣ ኤሌክትሪክ፣ አበባ፣ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ ዓሳ፣ ሻይ ቅጠል፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ እንዲሁም ሥጋ ከታቀደላቸው ክንውን ውስጥ ከ50 እስከ 74 በመቶ የሚሆነውን ብቻ በማስመዝገባቸው ነው፡፡

ከሚኒስቴሩ ሕዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በተገኘው መረጃ መሠረት፣ በ11 ወራት ውስጥ እንደሚገኝ ከታቀደው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ውስጥ ከ50 በመቶ በታች ዝቅተኛ ውጤት ካስመዘገቡ የወጪ ንግድ ምርቶች መካከል ቅመማ ቅመም፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የተፈጥሮ ሙጫና ዕጣን፣ ምግብ፣ መጠጥና ፋርማስዩቲካልስ፣ የሥጋ ተረፈ ምርቶች፣ የቁም እንስሳት፣ ማዕድን፣ የብርዕና የአገዳ ምርቶች ተካተዋል፡፡

በአንፃሩ ከተያዘላቸው ዕቅድ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ የወጪ ምርቶች ተብለው በሚኒስቴሩ የተጠቀሱት፣ ባህር ዛፍና ጫት ናቸው፡፡ ከታቀደው ገቢ ውስጥ ከ75 እስከ 99 በመቶ በማሳካት ከሚጠቀሱት ውስጥም ታንታለም፣ የጥራጥሬ ሰብሎችና የቅባት እህሎች ተካተዋል፡

በግብርና ምርቶች ላይ የአገር ውስጥ መሸጫ ዋጋ ከዓለም አቀፉ ዋጋ ጋር አለመጣጣሙ፣ ላኪዎችም የገቡትን የሽያጭ ስምምነት ለማክበርና ከገበያ ገዝተው ለማሟላት መቸገራቸው የወጪ ንግዱ አንዱ ችግር ሲሆን፣ ምርቶችን ከመሸጫ ዋጋ በታች (under invoice) በማድረግ የሚያስመዘግቡና የሚልኩ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በማዕድን ዘርፍ የተስፋፋው የኮንትሮባንድ ንግድም ለወጪ ንግዱ መዳከም አስተዋጽኦ አድርጓል ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች