Thursday, June 20, 2024

ለክቡር ሚኒስትሩ የቀድሞው ሚኒስትር ስልክ ደወሉላቸው

[ክቡር ሚኒስትሩ ከአንድ ነጋዴ ጋር ተገናኝተው እያወሩ ነው]

 • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • ሥራ እንዴት ነው?
 • የምን ሥራ?
 • ንግዱን ማለቴ ነው፡፡
 • የመቼዎትን ክቡር ሚኒስትር?
 • ምነው ተውክ እንዴ?
 • እናንተ አስተዋችሁኝ እንጂ፡፡
 • ደግሞ እኛ ምን አደረግን?
 • ከዚህ በላይ ምን ታደርጉ ክቡር ሚኒስትር?
 • እንዴት ማለት?
 • እንቅስቃሴውን እኮ ገድላችሁታል፡፡
 • ምን አድርገን?
 • እናንተ ፖለቲካውን ብቻ ይዛችሁ ኢኮኖሚውን እኮ ረስታችሁታል፡፡
 • ከአቅማችን በላይ ሆኖ ነው እባክህ፡፡
 • ለነገሩ ፖለቲካውንስ ቢሆን መቼ ቻላችሁት?
 • ምን ማለት ነው?
 • ይኸው አገሪቱ ከጫፍ እስከ ጫፍ ተወጣጥራ ልትበጣጠስ አይደል እንዴ?
 • . . .
 • ግን በኋላ ብዙ ዋጋ ትከፍላላችሁ፡፡
 • እንዴት?
 • ከፖለቲካው ይልቅ ኢኮኖሚው ላይ ብትሠሩ ያዋጣችኋል፡፡
 • ምን እናድርግ?
 • ክቡር ሚኒስትር ዶላር ከ40 ብር በላይ እንደሚመነዘር ያውቃሉ?
 • ምን እሱን ለእኔ ትነግረኛለህ?
 • ለነገሩ የብላክ ማርኬት ሥራ እንደሚሠሩ ረስቼው ነው፡፡
 • . . .
 • ለማንኛውም ኢኮኖሚው አንዴ ከተበላሸ እንደ ፖለቲካው በቀላሉ መጠገን ያስቸግራል፡፡
 • ለቀባሪው አረዱት ሆነብኝ እኮ የምታወራው ጉዳይ፡፡
 • ነገሩን ማወቅ ሳይሆን መፍትሔ ማምጣቱ ነው የሚጠቅማችሁ፡፡
 • መፍትሔ ከየት ይምጣ?
 • ረሱት እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
 • ምኑን?
 • ክቡር ሚኒስትር መሆንዎትን፡፡
 • አልገባኝም?
 • ቦታው ላይ የተቀመጡት እኮ መፍትሔ አመጣለሁ ብለው ነው፡፡
 • . . .
 • ክቡር ሚኒስትር ሁሉም ባለሀብት እኮ ግራ እየተጋባ ነው፡፡
 • ለምን?
 • ችግሮች በላይ በላይ እየተደራረቡበት ነዋ፡፡
 • የምን ችግር?
 • ይኸው በዚህ በመብራት ፈረቃ ራሱ በርካታ ፋብሪካዎች ሥራ እያቆሙ ነው፡፡
 • ምን ታደርገዋለህ?
 • በዚህ ምክንያት በርካታ ሰዎች ሥራ አልባ ይሆናሉ፡፡
 • ይኼ እኮ በአገር ላይ የመጣ ችግር ነው፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ችግሩንማ ሁሉም ያውቀዋል፡፡
 • እሱን እኮ ነው የምልህ?
 • ከእናንተ የሚጠበቀው ለችግሩ መፍትሔ ማፍለቅ ነው፡፡
 • መፍትሔ ምንጭ አይደል ከየት ይፈልቃል ብለህ ነው?
 • ሥራችሁ እኮ መፍትሔ ማመንጨት ነው፡፡
 • ከየት ይመጣል ስልህ?
 • ካልቻላችሁማ መፍትሔው ሌላ ነው፡፡
 • ምንድነው?
 • መልቀቅ!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከአንድ ተቃዋሚ ጋር ጂም ተገናኝተው እያወሩ ነው]

 • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • እዚህ ደግሞ ምን ታደርጋለህ?
 • ፓርላማ አይደለም እኮ ያለነው፡፡
 • ምን?
 • ያው ተቃዋሚ ፓርላማ እንጂ ጂም እንዳይገባ መቼ አላችሁ?
 • ፓርላማ ያልገባችሁት እኮ ተከልክላችሁ ሳይሆን ስላልተመረጣችሁ ነው፡፡
 • እሱን እንኳን ተውት፡፡
 • አሁን እናንተ ሕዝብ የሚመርጠው ፕሮግራም አላችሁ?
 • ክቡር ሚኒስትር ኢትዮጵያ በዓለማችን ብርቅዬ ከሆነችባቸው አንዱ ነገር ፓርላማችን መሆኑን ረሱት?
 • እንዴት?
 • ከመቶ በላይ ፓርቲዎች ባሉበት አገር አንድ ፓርቲ 100 ፐርሰንት ያሸነፈበት በመሆኑ ነዋ፡፡
 • እናንተ ለነገሩ ከፖለቲካው ቀልዱ ይዋጣላችኋል፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር እናንተ ቀልደኛ ሆናችሁ እኮ ነው እኛን ቀልደኛ ያደረጋችሁን፡፡
 • እንዴት?
 • መቶ በመቶ ፓርላማን ከመቆጣጠር የበለጠ ቀልድ የት አለ ብለው ነው?
 • ለመሆኑ ጂም እንዴት ነው?
 • ሐኪም አዞልኝ እኮ ነው የጀመርኩት ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ተቃዋሚዎችም በአገሪቱ ፖለቲካ ጤናችሁ ይቃወሳል ማለት ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር ፓርላማ ለዓመታት ሳንገባ ፖለቲከኛ መሆናችን በራሱ ስንት በሽታ ነው ያመጣብን፡፡
 • ተስፋ ሳትቆርጡ ከሠራችሁ በሚቀጥለው ምርጫ ፓርላማ ትገቡ ይሆናል፡፡
 • ምናችን ሞኝ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • እንዴት?
 • እናንተን ድጋሚ አምነን ምርጫ ልንወዳደር?
 • አሁን እኮ ለውጥ ላይ ነን፡፡
 • ሁሌም ወሬያችሁ እንደዚህ ነው፣ ችግሩ ድርጊታችሁ ላይ ነው ያለው፡፡
 • በእውነት እመነኝ በሚቀጥለው ምርጫ ዕድል ሊኖራችሁ ይችላል፡፡
 • ኧረ ምን በወጣኝ?
 • ታዲያ ፖለቲካውን ልትተወው?
 • እርግፍ አድርጌ ነዋ፡፡
 • ያስችልሃል ግን?
 • ክቡር ሚኒስትር ተመሳሳይ የሆነ ዘርፍ ውስጥ እቀላቀላለሁ፡፡
 • እኮ ምን ዓይነት?
 • ስፖርት ማዘውተር የጀመርኩትም እኮ ለዚያ ነው፡፡
 • ስፖርትና ፖለቲካን ደግሞ ምን አገኛቸው?
 • ክቡር ሚኒስትር ኢትዮጵያ ውስጥ ስፖርትና ፖለቲካ በጣም ይገናኛሉ፡፡
 • እንዴት?
 • የእግር ኳስ ሜዳዎቻችን እኮ ዋነኛ የፖለቲካ ሐሳብ መንሸራሸሪያ ሜዳዎች ናቸው፡፡
 • . . .
 • እንዲያውም የፖለቲካ ፓርቲዬን አፍርሼ ላቋቁም አስቤያለሁ፡፡
 • ምን?
 • ክለብ፡፡
 • የምን ክለብ?
 • የእግር ኳስ!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከደላላ ወዳጃቸው ጋር ተገናኝተው እያወሩ ነው]

 • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • ከተማዋ እንዴት ናት?
 • ሰሞኑን ብዙ ሰው እያማረረ ነው፡፡
 • ምኑን?
 • በመብራት፣ በውኃና በኢንተርኔት ነዋ፡፡
 • ምን ይደረግ?
 • በተለይ የመብራትና የውኃ ችግር አይጣል ነው፡፡
 • ተፈጥሮ ሲጠምደን ምን ታደርገዋለህ?
 • መቼ ዕለት የሰማሁዋት ቀልድማ አስቃኛለች፡፡
 • የምን ቀልድ?
 • መብራትና ውኃ በጣም ከመጥፋታቸው የተነሳ ብሔራዊ ሎተሪ ቢያካትታቸው ተብሏል፡፡
 • ምን ውስጥ ነው የሚያካትታቸው?
 • የቶምቦላ ዕጣ ውስጥ ነዋ፡፡
 • ሰው ይቀልዳል አይደል?
 • ኑሮን ካልቀለደ እንዴት ይገፋዋል?
 • አገራችን ግን በርካታ ቀልደኞች አሉ ልበል?
 • ክቡር ሚኒስትር መንግሥታችን ቀልደኛ ስለሆነ ቀልደኞችን ስለሚያረታታ ነው እኮ፡፡
 • ምን?
 • ሁሉም ቀልደኛ ነው ለማለት ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ለመሆኑ ባለፈው ላክልኝ ያልኩህን ዶክመንት ላክልኝ?
 • በምን ልላከው ክቡር ሚኒስትር?
 • እንዴት?
 • ኢንተርኔቱስ የት አለ?
 • ኢንተርኔቱስ ጊዜያዊ ችግር ነው፡፡
 • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
 • ያው ተማሪዎች ብሔራዊ ፈተና ላይ ስለሆኑ ነዋ፡፡
 • በነገራችን ላይ ጨዋታን ጨዋታ ያነሰዋል አሉ፡፡
 • የምን ጨዋታ?
 • ክቡር ሚኒስትር በዚህ ፈተና ሰዎች እየከበሩ ነው አሉ፡፡
 • እንዴት?
 • በፊት እናንተ የምታሰርቁት የለውጡ ትግል ፍሬ እንዲያፈራ ነበር፡፡
 • ምን ጥያቄ አለው?
 • አሁን ግን ቢዝነስ ሆኗል አሉ፡፡
 • ቢዝነስ ስትል?
 • በቃ ፈተናው ተሰርቆ ይወጣና ለትምህርት ቤቶች ይሸጣላ፡፡
 • . . .
 • ክቡር ሚኒስትር ሰዎች በዚህ ቢዝነስ እየከበሩ ነው፡፡
 • ይኼ አሁን ምን ቢዝነስ ነው ሥርዓተ አልበኝነት እንጂ፡፡
 • በአገራችን ሥርዓተ አልበኛ ያልሆነ ቢዝነስ የት አለ?
 • እሱስ ልክ ነህ፡፡
 • ባይሆን ክቡር ሚኒስትር እኛ አጋጣሚው እንዳያመልጠን፡፡
 • የምኑ?
 • የፈተናው፡፡
 • ምን እናድርግ ታዲያ?
 • ማስታወቂያ ማስነገር ነዋ፡፡
 • ምን ብለን?
 • ፈተና እንሰርቃለን እናሰርቃለን!

[ለክቡር ሚኒስትሩ የቀድሞው ሚኒስትር ስልክ ደወሉላቸው]

 • ሰላም ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • እናንተ እያላችሁ የምን ሰላም አለ?
 • መቼ ነው እናንተ ጣት መጠቆም የምታቆሙት?
 • ጣት መጠቆሙን እኮ ከእናንተ ነው የተማርነው፡፡
 • ታዲያ ምን አለ አገር ማስተዳደሩንም ከእኛ ብትማሩ ኖሮ?
 • እናንተ እኮ አገር እያስተዳደራችሁ ሳይሆን አገር እየዘረፋችሁ ነበር፡፡
 • ስድቡ ይቆይልዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • እናንተማ ከስድብም በላይ ይገባችሁ ነበር፡፡
 • ምንድነው የሚገባን?
 • እስር ቤት፡፡
 • ለምን ሲባል?
 • አገር ስትዘርፉ ነበራ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር እንደዚያ ከሆነ እናንተም እስር ቤት ነው የሚገባችሁ፡፡
 • ለምን ተብሎ?
 • እናንተም አብራችሁ ስትዘርፉ ነበራ፡፡
 • እኛ ተገደን ነው ስንዘርፍ የነበረው፡፡
 • ማን ነው ያስገደዳችሁ?
 • እናንተ ናችኋ፡፡
 • የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ አሉ፡፡
 • መሳደብ አትችልም፡፡
 • እየተሳደብኩ ሳይሆን ክቡር ሚኒስትር፣ ምን እንደሆናችሁ እየነገርኳችሁ ነው፡፡
 • ለማንኛውም እንተያያለን፡፡
 • ምኑን ነው የምንተያየው ክቡር ሚኒስትር?
 • ጥጋባችሁ እስኪወጣላችሁ ድረስ እናስጨርሳችኋለን፡፡
 • የእኛን ጥጋብ እናስጨርሳለን ብላችሁ ሕዝቡን እንዳትጨርሱት፡፡
 • እንተያያለን አልኩህ እኮ፡፡
 • ምን ልታመጡ?
 • ወንጀለኞችን እየደበቃችሁ መቀጠል አትችሉም፡፡
 • መጀመርያ እናንተም የደበቃችኋቸውን ወንጀለኞች አጋልጡ፡፡
 • . . .
 • ክቡር ሚኒስትር ዝም ብሎ ጣት መጠቆም አያጣዋም፡፡
 • እሱን እንተያያለን፡፡
 • ለማንኛውም በዚህ ለመቀጠል ካሰባችሁ እኛም ወስነናል፡፡
 • ምንድነው የወሰናችሁት?
 • ለመገንጠል!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...

ብሔራዊ ባንክ ጥርስ እያወጣ ይሆን እንዴ?

በአመሐ ኃይለ ማርያም ‹‹Better late than never›› (ከቀረ የዘገየ ይሻላል) የኢትዮጵያ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሐዘን ለመድረስ ጎረቤት ተገኝተው ለቀስተኛው በሙሉ የሚያወራው ነገር አልገባ ብሏቸው ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ባለቤታቸውን ስለጉዳዩ እየጠየቁ ነው] 

ጎረቤታችን ሐዘን ለመድረስ ብሄድ ለቀስተኛው በሙሉ በሹክሹክታ ያወራል። ግን የሚያወሩት ነገር ሊገባኝ አልቻለም። ምንድነው የሚያወሩት? እኔ ምን አውቄ? እንዴት? የሚያወሩትን ምንም አልተሰማሽም? እኔ እንድሰማ የፈለጉ አይመስልም ግን ... ግን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...