Monday, June 17, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በመጪው ዓመት 441 ሺሕ ሜትሪክ ቶን በላይ ቡና ሊመረት እንደሚችል የአሜሪካ ትንበያ አመለከተ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

ትንበያው በመንግሥት ከሚጠበቀው 1.1 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በእጅጉ ያነሰ ሆኗል

የመንግሥት ዕቅድ አውጪዎች ስለቡና የማያውቁ ተብለዋል

የአሜሪካ ግብርና መሥሪያ ቤት በግብርና አገልግሎቶች መስክ በየጊዜው ከሚያወጣቸው ሪፖርቶች አንዱ የሆነውና በኢትዮጵያ ቡና ምርትና ፍጆታ ላይ ባተኮረው ትንበያ መሠረት፣ በመጪው ዓመት በኢትዮጵያ የሚመረተው ቡና መጠን ከ440 ሺሕ ቶን እንደማይበልጥ ይፋ አደረገ፡፡

ከዚህ ቀደም በስንዴና በሌሎች የብርዕ ምርቶች ላይ ያተኩር የነበረውና ግሎባል አሊያንስ ኢንፎርሜሽን ኔትወርክ (ጌይን) የተሰኘው ይህ ሪፖርት፣ በመጪው ዓመት በኢትዮጵያ የሚመረተው ቡና መጠን 440 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ወይም 7.4 ሚሊዮን ባለ 60 ኪሎ ግራም ቁምጣ እንደሚመረት ግምቱን አስፍሮ፣ ከዚህ ምርት ውስጥ 240 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ለውጭ ገበያ እንደሚቀርብ አስፍሯል፡፡ ይህም ከፍተኛ ዕመርታ ሊታይበት፣ ምናልባትም አገሪቱ ለውጭ ካቀረበችው መጠን የላቀው ሆኖ ሊመዘገብ እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል፡፡

ባለፈው ዓመት 238 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ ሊቀርብ ስለመቻሉ ግምቶቹን ያጣቀሰው የአሜሪካው የግብርና መሥሪያ ቤት፣ አሜሪካ ከገዛችው መጠን የ11 በመቶውን ድርሻ ሊይዝ የሚችል ቡና ከኢትዮጵያ እንደረቀበላት አመላካች መረጃውን አስፍሯል፡፡ ዓምና አሜሪካ ካከናወነችው የ5.7 ቢሊዮን ዶላር የቡና ምርት ግዥ ውስጥ የኢትዮጵያ ድርሻ የ142 ሚሊዮን ዶላር እንደነበር፣ ከዋና ዋና የኢትዮጵያ ቡና ተቀባይ አገሮች መካከልም አሜሪካ በአራተኛነት ደረጃ እንደምትመደብ ተጠቅሷል፡፡

በዚህ ዓመት ይመረታል ተብሎ የሚጠበቀው ቡና፣ ጥሩ የዝናብ ሥርጭትና አነስተኛ የበሽታ ጫና እንደሚኖር በመገመቱ ከዓምናው የተሻለ ምርት ሊኖር እንደሚችል ይጠበቃል ያለው ሪፖርቱ ገበሬዎችም የተሻሻለ የግብርና ኤክስቴንሽን አግልግሎት ተጠቃሚ በመሆናቸው ጭምር የቡና ምርት መጠንና ግብይት የተሻለ ውጤት ሊታይበት እንደሚችል ተገምቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት ለቡና ምርት የዋለው መሬትም ከ535 ሺሕ ሔክታር መጠነኛ ጭማሪ በማሳየት ወደ 538 ሺሕ ሔክታር እንደሚጨምር ይጠበቃል፡፡ በሔክታር እስከ 82 ቶን ምርት ሊገኝ ይችላል ተብሏል፡፡ በኢትዮጵያ ከሚመረተው ከቡና ከ95 በመቶ በላይ የአነስተኛ ገበሬዎች እንደሚመረት ይታወቃል፡፡

ምንም እንኳ በአሜሪካ ግብርና መሥሪያ ቤት ግምት መሠረት በመጪው ዓመት የሚመረተው ቡና 440 ሺሕ ሜትሪክ ቶን እንደሆነ ቢጠበቅም፣ በመንግሥት ዕቅድ መሠረት ግን 1.1 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን እንደነበር በሁለተኛው የዕድገትና ትራንፎርሜሽን ዕቅድ የሰፈረ ነበር፡፡ ይህንን ዕቅድ በእጅጉ ዝቅ የሚያደርግ ብቻም ሳይሆን፣ እስካሁንም የተመረተው ምርት ከዕቅዱ አኳያ የማይገናኝ እንደነበር ይታያል፡፡

ከዚህ ባሻገር የመንግሥት ዕቅድ አውጪዎች ስለቡና ዘርፍም ሆነ ስለአመራረት ሥርዓቱ፣ ስለቡና ዛፍም ሆነ በጠቅላላው ከቡና የግብርና ሥራ ጋር የተያያዙ ሥራዎች ላይ ዕውቀታቸው ውስንነት የሚታይበትና፣ በእርሻ ማሳ ስለሚከናወን ጉዳይ የማያውቁ ሲል ወርፏቸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች