Monday, June 17, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ጫማ አምራቹ ሁጂያን ግሩፕ የጂማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ለመጠቅለል ተስማማ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

– በጂማ የቡና ማቀነባበሪያ ይገነባል

 

የቻይና ጫማ አምራች ሁጂያን ግሩፕ የጂማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ሙሉ በሙሉ ከመንግሥት በመረከብ ለማስተዳደርና የምርት ሥራዎችን ለማካሄድ የመግባቢያ ስምምነት ፈረመ። ስምምነቱን የሁዋጂያን ተጠሪ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወሪት ሌሊሴ ነሜ ጋር በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አዳራሽ ስምምነቱን ሐሙስ ግንቦት 22 ቀን 2011 ዓ.ም. ፈርመዋል።

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽርና ከጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኦማር ጊሌ ጋር በመሆን ከወራት በፊት ያስመረቁት የጂማ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ በአራት ወራት ውስጥ ሥራ እንደሚጀምር ይጠበቃል።

በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በስምምነቱ ወቅት እንዳሉት፣ የኩባንያው ወደ ጂማ ኡንዱስትሪ ፓርክ መግባት በተለይ በአካባቢው ለሚገኘው የቡና ሀብት ትልቅ ፋይዳ አለው።

የቡና ማቀነባበሪያው ዕቅድ በሁለተኛው የሁጂያን የኢንቨስትመንት ምዕራፍ ተግባራዊ እንሚሆን የገለጹት የኩባንያው ፕሬዚዳንት ዣንግ ሁዋሮግ በስምምነቱ ወቅት እንዳስታወቁት፣ በመጀመሪያው ዓመት ከቻይናና ከሌሎችም አገሮች ኢንቨስተሮችን በማምጣት ከ30 ሔክታር በላይ በሆነ ይዞታ ላይ በተገነባው የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ እንዲያመርቱና ለአገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ ይደረጋል። 

በሁለተኛው ምዕራፍም የቡና ማቀነባበሪያ በመገንባት ለቻይና ገበያ ምርቶቹን እንደሚያቀርብ፣ የቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ማዕከልም እንደሚገነባ አስታውቆ ለጂማና ለአካባቢዋ ወጣቶች ሥልጠና እንደሚሰጥም ገልጸዋል።

ከ60 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገበት የጂማ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ ጫማን ጨምሮ ልዩ ልዩ መገልገያዎች እንደሚመረቱበትና ከዘጠኝ ሺሕ እስከ 12 ሺሕ ለሚደርሱ ወጣቶች የሥራ ዕድል እንደሚፈጠር ወሪት ሌሊሴ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበበ አበባየሁ በበኩላቸው፣ ኩባንያው ከሰባት ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ልምድ ያለው በመሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፓርኩን ወደ ሥራ እንደሚያስገባው እምነታቸውን ገልጸዋል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች