Saturday, June 22, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ከ40 በላይ የቻይና የሕክምና ቁሳቁስ አምራቾች በኢትዮጵያ እንዲያመርቱ የተጠየቁበት ፎረም

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከቻይና የሔናን ግዛት የተውጣጡ ከ40 በላይ ኩባንያዎች በአዲስ አበባ ተገኝተው፣ ስለምርቶቻቸውና ስለፍላጎቶቻቸው ገለጻ አቅርበዋል፡፡ ከ60 በላይ የኢትዮጵያ የሕክምናው ዘርፍ ተዋናዮች፣ የመድኃኒት አምራቾችና አስመጪዎች እንዲሁም የመንግሥት ባለሥልጣናትና የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች በተሳተፉበት የቻይና ኢትዮጵያ የንግድና ኢንቨስትመት ፎረም ላይ፣ የሔናን የሕክምና ቁሳቁሶች ንግድ ማኅበር ተወካዮች ስለኢትዮጵያ ብሎም ስለሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጉዟቸው አብራርተዋል፡፡

የሔናን የንግድ ልዑካንን የመሩትና የግዛቷ የቻይና አፍሪካ የንግድ ማኅበር ተወካይ ሚስተር ዊሊያም ዉ ያንግ፣ የንግድ ምክር ቤቱ አባላት ከ60 በላይ አገሮች ጋር ግንኙነት እንዲመሠርቱ እገዛ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሩዋንዳና ኡጋንዳ የጉብኝታቸው መዳረሻዎች እንደነበሩና፣ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝትም በአገሪቱ ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችና የገበያ ዕድሎች ለመረዳት ብሎም የንግድ ግንኙነት ለመመሥረት የታሰበበት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ጸሐፊ አምባሳደር ደዋኖ ከድር በበኩላቸው፣ መንግሥት የውጭ ባለሀብቶች ከአገር ውስጥ አምራቾችና ነጋዴዎች ጋር በመጣመር መሥራት እንዲችሉ ድጋፍ እንደሚሰጥ፣ ከአገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር አብሮ መሥራቱም የውጭ ኩባንያዎች ሲገቡ ሊገጥማቸውን የሚችለውን ውጣውረድ እንደሚያቃልልላቸው በመግለጽ ቻይናውያኑ አምራቹን ዘርፍ እንዲቀላቀሉ ጠይቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቅ ገበያ ነች ያሉት አምባሳደር ደዋኖ፣ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለምታስተዳደር አገር የሚውለው የመድኃኒት ፍጆታ በአገር ውስጥ ቢመረት፣ ብሎም ለውጭ ገበያ ቢቀርብ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንደሚኖረው በማብራራት ቻይናውያኑ ፋብሪካዎቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ እንዲያመጡ ጠይቀዋል፡፡

ምንም እንኳ የኢትዮጵያ የመድኃኒት ኢንዱስትሪ አሁን የሚገኝበት አቅም በ450 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ኢኮኖሚያዊ ዋጋና እሴት እንዳለው ቢጠቀስም፣ እ.ኤ.አ. በ2025 ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደሚያድግ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች