Monday, June 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊሳዑዲ ዓረቢያ በቤት ሠራተኛነት የሚሄዱ ኢትዮጵያውያንን ቪዛ ሰረዘች

ሳዑዲ ዓረቢያ በቤት ሠራተኛነት የሚሄዱ ኢትዮጵያውያንን ቪዛ ሰረዘች

ቀን:

ችግሩ አስፈጻሚው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሕጉን ተከትሎ አለመሥራቱ ነው ተብሏል

በቅጥር ሁኔታዎች ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ሳዑዲ ዓረቢያ በቤት ሠራተኛነት የሚሄዱ ኢትዮጵያውያንን ቪዛ መሰረዟ ታወቀ፡፡

ቅጥርን አስመልክቶ በተፈጠረ ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት ቪዛ ተዘጋጅቶላቸው የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች ቪዛ እንዲታገድ ማድረጉን የሳዑዲ ዓረቢያ የሠራተኛ ሚኒስቴር፣ በአገሪቱ ታዋቂ ለሆነው ‹‹ሳዑዲ ጋዜት›› ገልጿል፡፡ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የቤት ሠራተኞችን በሕጋዊ መንገድ ቀጥሮ ለመውሰድ ከኢትዮጵያ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ላይ የተደረሰ ቢሆንም፣ ምልመላው በስምምነታቸው መሠረት ሊካሄድ ባለመቻሉ እንዲቆም ማድረጉንም አክሏል፡፡

- Advertisement -

በሺዎች የሚቆጠሩ የቤት ሠራተኞች ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ እንዲሄዱ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በመፍቀዱ የሚመለከተው ባለሥልጣን ተቋም ቪዛዎችን አዘጋጅቶ ከረመዳን ፍቺ በፊት ለመቀበል ቪዛዎችን ያዘጋጀ ቢሆንም፣ አንድም ኢትዮጵያዊት የቤት ሠራተኛ እስካሁን መሄድ እንዳልቻለች አስታውቋል፡፡

እ.ኤ.አ. ግንቦት 14 ቀን 2019 ከሚኒስቴሩ ኃላፊዎች ጋር በተደረገ ስብሰባ፣ ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች መሥፈርቱን የሚያሟሉ ሠራተኞችን እንደሚመለመሉ የተገለጸለት ቢሆንም፣ ‹‹ሙሳነድ›› የሚባለውን ኤሌክትሮኒክስ መመዝገቢያ ሲስተም መሰረዙን በመስማቱ ኢትዮጵያን ሠራተኛ ከሚልኩ አገሮች ዝርዝር ውስጥ መሠረዙን የሳዑዲ ዓረቢያ የሠራተኞች ሚኒስቴር ለጋዜጣው ገልጿል፡፡ 19 አገሮች የቤት ሠራተኞችን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ እንዲልኩ የሳዑዲ መንግሥት መፍቀዱንና እነሱም ፊሊፒንስ፣ ኒጀር፣ ህንድ፣ ፓኪስታን ባንግላዴሽ፣ ሲሪላንካ፣ ቬትናም፣ ኡጋንዳ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ኢትዮጵያና ሌሎች አገሮች መሆናቸውንም አስታውቋል፡፡

ከሠራተኞች ቅጥር ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ልዩነት በመፈጠሩ ተዘጋጅተው የነበሩ በሺሕ የሚቆጠሩ ቪዛዎች መሰረዛቸውን ጋዜጣው አብራርቷል፡፡ ችግሩ የተፈጠረው በላኪ ኤጀንሲዎች በኩል በተፈጠረ ችግር ሳይሆን፣ አስፈጻሚው ተቋም ማለትም የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አዋጅ ቁጥር 923/2008 ድንጋጌን ተከትሎ አለመሥራቱ መሆኑን የተቋሙ አንዳንድ ኃላፊዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ከወራት በፊት ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ተጉዘው ከሳዑዲ አቻቸው ጋር ተወያይተው እስካሁን ግልጽ ያልሆነ ስምምነት ፈጽመው እንደመጡ ቢገመትም፣ ሥራው ሊጀመር እንዳልተቻለም አክለዋል፡፡

በአዋጁ አንቀጽ 37 የሥራ ውልን በሚመለከት እንደተደነገገው፣ ማንኛውም ኤጀንሲ ሚኒስቴሩ ያወጣውን ሞዴል የሥራ ውል መሠረት በማድረግ አሠሪ፣ ኤጀንሲውና ሠራተኛው የፈረመበትን የሥራ ውልና ሌሎች ሚኒስቴሩ በመመርያ የወሰናቸውን መሥፈርቶች በማሟላት እንዲፀድቅ ማቅረብ አለበት፡፡

የሰነዶቹ ትክክለኛነት በሚመለከተው ሚሲዮን (ኤምባሲ) እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጋገጥ አለበት፡፡ ሁኔታዎች መሟላታቸውን ሚኒስቴሩና ኤምባሲው እንዳረጋገጡ በመመርያው በሚወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ የቀረበውን የሥራ ውል በማፅደቅ እንደሚመዘገብ ተደንግጎ ቢገኝም፣ በሕግ አግባብ እየተሠራ እንዳልሆነም ኃላፊዎቹ ጠቁመዋል፡፡ ሁለቱ አገሮች የሁለትዮሽ ስምምነት ውል ፈጽመውና በፓርላማዎቻቸው አፅድቀው እያለ፣ ሕጉን ተከትሎ ከመተግበር ይልቅ ሕጉን ወደ ጎን በመተው፣ ‹‹ሙሳነድ ሲስተም›› የሚባል የሕግ ድጋፍ የሌለውና ተጠያቂነትን ወደ ጎን ትተው ያለ ሲስተም ለመጠቀም ሩጫ መጀመሩንም ኃላፊዎቹ አክለዋል፡፡

ይኼንን የሚደርጉትና ኃላፊዎችን በማሳሳትና ጊዜያዊ ጥቅም ለመሰብሰብ በሚሮጡ አሥር በማይሞሉ የኤጀንሲዎች ባለቤቶች ገፋፊነት ተግባራዊ ለማድረግ እየተሯሯጡ ቢሆንም፣ አካሄዱ ያስፈራው የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት የሥራ ዕድሉን መሰረዙን ኃላፊዎቹ ጠቁመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሁኔታውን ለማሳወቅም ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ኃላፊዎቹ ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...